General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
እሁድ:- ግንቦት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ለውጦችና በተፈጠሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ወይይት ተካሄደ!!

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦችና በተከሰቱ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮሌጁ አሰልጣኞች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል፡፡

"የበቃ አሰልጣኝ ክህሎት የጨበጠ ወጣት ለሀገር ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለውን ውይይት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ #ጥራቱ #በየነ ከማዕከል በገለፃ አቅረበዋል።

ክቡር አቶ ጥራቱ በገለፃቸው እንደ ሀገር የመጡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የወጪ ግንኙነት ፖሊሲና ዲፕሎማሲ ስኬቶችን እንዲሁም ሀገራዊ ለውጡን የፈተኑ ውስጣዊና ወጫዊ ተግዳሮቶችን አብራርተዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም ብቁ ባለሙያ በማፍራትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ለሀገራዊ ብልፅግና ያላቸው ሚና ትልቅ መሆኑን አውስተዋል፡፡ በገለፃው የመዲናቱ ኮሌጆች ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ በጥንካሬና በክፍተት ማሳየት ተችሏል፡፡

በቀረበው ገለፃ መሰረት ከኮሌጁ አሰልጣኞች የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች እየተነሱ ሲሆን የውይይት መድረኩን በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ #አቶ #መሀመድ #ልጋኒ እና የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ #መለሰ #ይግዛው እየመሩት ይገኛሉ፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ረቡዕ:- ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም

ለአሰልጣኞችና ለኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የሶላር ስልጠና ተሰጠ!!

ለኮሌጁ ኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክ አሰልጣኞችና ከኢንዱስትሪዎች ለተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች የሶላር ክህሎት አቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በኔዘርላንድ ከሚገኝ እና የሶላር ክህሎት ስልጠናን በበጎ ፈቃደኝነት ከሚሰጠው PUM ከሚባለው ድርጅት ጋር በመተባበር ለ8 የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች እና ለ11 የኮሌጁ አሰልጣኞች በዛሬው ዕለት ተግባራዊ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

የፅንሰ ሀሳብ ትምህርቱ ከዚህ በፊት በበየነ መረብ በሳምንት 3 ጊዜ ለ24 የቀናት የተሰጠ ሲሆን የተግባር ስልጠናው ደግሞ በአካል ዛሬ ተጀምሮ ለ7 ቀን ይሰጣል።

የስልጠናው ዓላማ የግሪን ኢኮኖሚ አካል የሆነውን ታዳሽ ኃይል ለመጠቀም የሚያስችል ክህሎትን ለማዳበር ሲሆን ይዘቱም የሶላር ኃይልን በመጠቀም የቤት ውስጥ መብራት ፍጆታ፣ የመንገድ ዳር ብርሃን ዝርጋታና የከርሰምድር ውሃ ጉልበታ ለመከወን የሚያስችልበት አቅም ለማሳደግ ነው ተብሏል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
አርብ:- ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

የኮሌጁ ሜታል ማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት የዶሮ ኬጂዎችን እያመረተ ነው!!

የኮሌጁ ሜታል ማኑፋክቸሪንግ ዲፓርትመንት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር ለሚገኙ ወረዳዎች አገልግሎት የሚውል የዶሮ ኬጂዎችን በማምረት ላይ ይገኛል፡፡

ዲፓርትመንቱ እያንዳንዳቸው 50 ዶሮዎችን የሚይዙ 48 ኬጂዎች እና 100 ዶሮዎችን ማስተናገድ የሚችሉ 24 የዶሮ ኪጂዎችን በጥራት አምርቶ ለማስረከብ እየተጋ ነው፡፡

እየተሰሩ ያሉ ኬጂዎች ለእንቅላል ጣይ ዶሮዎች መኖሪያ አገልግሎት  እንደሚውሉ የተገለጸ ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤቶች የከተማ ግብርና ውጤት በሆኑት የሌማት ትሩፋት ስራዎች ላይ አጠናክረው እንዲሰሩ ያግዛል መባሉን ሰምተናል፡፡

ዲፓርትመንቱ ከዚህ በፊት ለከተማይቱ ኮሪደር ልማት አገልግሎት የሚውሉ የኮንቲነር ሱቆችን ጨምሮ የተለያዩ የብረታ ብረት ምርት ውጤቶችን በጥራትና በፍጥነት ሰርቶ አስረክቧል፡፡     

የስልጠና ዘርፉ በኮሌጁ በአካባቢያዊ የመልማት ፀጋ ልየታም ከተመሩጡ 5 ዲፓርትመንቶች መካከል አንዱ መሆኑ አይዘነጋም፡፡ 

   ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
አርብ:- ግንቦት 15 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ የተቋሙን የውሃ ፍላጎት ምላሽ የሰጠ የከርሰ ምድር ውሃ አስቆፈረ!!

  ለኮሌጁ የውሃ እጥረት  ሙሉ በሙሉ ምላሽ የሚሰጥና ለአካባቢውም ማህበረሰብ መትረፍ የሚችል የከርሰ ምድር ውሃ ቁፋሮው ተጠናቆ በዛሬ ዕለት ውሃው መውጣት ጀምሯል፡፡

ቁፋሮው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የተደረገ ሲሆን 282 ሜትር ወይም ከሩብ ኪሎ ሜትር በላይ ጥልቀት እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

ጉድጓዱ ዲስቻርጅ የማድረግ አቅሙ ሲገመት በሰከንድ ከ10 ሊትር በላይ ውሃ መስጠት እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

በዘርፉ ባለሙያዎች የላብራቶሬ ትንተና ተሰጥቶበት እና ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች ተከናውነውለት በቅርብ ጊዜ በሙሉ አቅም ወደ አገልግሎት ይገባል መባሉን ሰምተናል፡፡

በተያያዘ የውሃ ዜና የኮሌጁ የፕላምቢንግ ሙያ አሰልጣኞች ወደ 3 ኪሎ ሜትር የሚጠጋ የግቢውን አጠቃላይ የውሃ መስመር ሙሉ በሙሉ በአዲስና አሁን ላይ በሚገኝው የውሃ መስመር ቴክኖሎጂ /ከብረት ወደ ፕላስቲክ/ በመቀየር የውሃ ስርጭት መጠንና ጥራት እንዲሻሻል አድርገዋል፡፡
 
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››