ሐሙስ:- ሚያዚያ 9 ቀን 2017 ዓ.ም
የትንሣኤ በዓልን ምክኒያት በማድረግ ኮሌጁ ለተለያዩ አካላት ስጦታ አበረከተ!!
በኮሌጁ ስጦታ ከተበረከተላቸው መካከል የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ የነበረቺውና ከ8 ወር በፊት ህይወቷ ያለፈው የአሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ቤተሰቦች ይገኙበታል። ለእነዚህ ቤተሰቦች ከተቋሙ ሰራተኞች 137ሺ ብር በማሰባሰብ የብርና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል። በዓይነት ተገዝተው ከተሰጡት ውስጥ የተለያዩ አስቤዛዎችን እንዲሁም የሻማ ማምረቻ እና የችብስ መጥበሻ ማሽኖች ይገኙበታል።
ሌላው መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክኒያት በማድረግ ኮሌጁ ከ260ሺ ብር /ከሩብ ሚሊዮን ብር/ በላይ ወጪ የጠየቀ የማዕድ ማጋራትን ያደረገው ደግሞ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች እና ኮሌጁ በየወሩ ድጋፍ እያደረገ ለሚያሳድጋቸው 16 ልጆች ነው።
የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ጫና ላይ ላሉ የስራ ባልደረቦች የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሌላ ዜና የኮሌጁ አጋር ሆኖ 4 ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ በመስራት የተቋሙ ገፅታ እንዲቀየርና የውስጥ ገቢው እንዲያድግ ያደረገው ፉት ፒች ኃላ/የተ/የግ/ ማኅበር ለኮሌጁ የጥበቃ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ይሁናችሁ ብሎ 50ሺ ብር ሰጥቷቸዋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

ረቡዕ:- ሚያዚያ 22 ቀን 2017 ዓ.ም
የሶስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ሰልጣኞች በኮሌጁ የሚሰጠውን ስልጠና አጠናቀቁ!!
ቀድመው የጀመሩት የሶስተኛው ዙር ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ ሰልጣኝ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ስልጠናቸውን አጠናቀው ተመረቁ።
ብቃት የወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና በኮሌጁ የተሰጣቸው ለ12 ቀናት ሲሆን ያጠናቀቁትም ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሁለት ወረዳዎች የተውጣጡት መሆናቸው ተገልጿል።
ጥቂት ቀናትን ዘግይተው ከጉለሌ ክፍለ ከተማ የመጡት ደግሞ በቀጣይ የሚያጠናቅቁ መሆኑ ተነግሯል።
ሰልጣኞች በቆይታቸው የጊዜ አጠቃቀም፣ የተግባቦት ችሎታ፣ የስራ ላይ ደህንነት፣ ወዘተ ያሉትን የክህሎት ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።
የህይወት ክህሎት ስልጠና ያጠናቀቁ ወጣቶች በተለያዩ ተቋማት ለስድስት ወራት የሚቆይ የስራ ላይ ልምምድ ቆይታ እንደሚኖራቸውም ታውቋል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ነገ አርብ ሚያዝያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት ከ12:30 እስከ 1:00 የኮሌጁ አዲስ ዶክመንተሪ በአዲስ ቲቪ ስለሚቀርብ ይከታተላሉ ዘንድ ተጋብዘዋል።
መልካም ቆይታ!
መልካም ቆይታ!
አርብ፡- ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
የ2017 በጀት ዓመት የሦስተኛው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት የሦስተኛው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ሚያዚያ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የሦስተኛውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የኮሌጁ የተቋም ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡
በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በ9 ወሩ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ፣ ተቋማዊ ሪፎርም ከመተግበር ረገድ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን አንፃር እምርታዊ ለውጥ ያሳዬ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀሪው ጊዜና በቀጣይ ዓመት ትኩረት ተሰጥቶ መሟላት ያለባቸው ግብዓቶችና መተግበር የሚኖርባቸው አሰራሮች እንዲሁም ከአካባቢ የመልማት ፀጋና ተከታታይ የሪፎርም ትግበራ ጋር ተያይዞ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው በኮሌጁ ዋና ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ማጠቃለያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ሰኞ፡- ሚያዚያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ዛሬ ተጀመረ።
ለአሸናፊዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል።
ዘንድሮ የሚካሄደው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር " ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች " በሚል ሀሰብ እንደሆነ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታውቋል።
መርሃ ግብሩ ከዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን እስከ ግንቦታ 2 ቀን 2017 ዓ/ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት እየተካሄደ ይቆያል።
ውድድሩ በክህሎት፣ በቴክኖሎጂና ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፎች ነው የሚካሄደው።
በውድድሩም፣ " በሁሉም ክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች በተካሄዱ ተመሳሳይ ውድድሮች አንደኛ ሆነው ያጠናቀቁ የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች፣ የኢንተርፕራይዝ ባለቤቶች ይሳተፋሉ " ተብሏል።
ለውድድሩ አሸናፊዎች የሜዳሊያ፣ የዋንጫና የገንዘብ ሽልማት ይበረከታል።
የውድድሩ ዓላማ የዘርፉን አዲስ እሳቤ መሠረት ያደረገ የአሰልጣኞች፣ የሠልጣኞችና ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ሙያቸውን እንዲያዳብሩ፣ አቅማቸውን እንዳያሳዩ፣ ቴክኖሎጂችን ባለሃብቶችና ኢንተርፕራይዞች ወደ ምርት አገልግሎት እንዲያሸጋግሩ ጭምር ነው።
በ2015 ዓ/ም በ3ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂ የፈጠሩ ተወዳዳሪዎች በ2016 ዓ/ም ከ80 በላይ ቴክኖሎጂዎችን እንዳመረቱ ተነግሯል።
ፕሮግራሙ በ2017 በጀት ዓመት “ስኪል ኢትዮጵያ” በሚል ስያሜ ቀጥሎ፣ በአሁኑ ጊዜም 180 የሚሆኑ የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን አምርተው በማውጣት ሂደት እንደሚገኙ ተመልክቷል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ምንጭ፦ ቲክቫህ ኢትዮጵያ

አርብ:- ግንቦት 1 ቀን 2017 ዓ.ም
የኮሌጁ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በሀገር አቀፍ ደረጃ አሸነፈ!!
በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳድሮ 2ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
ይህ የጥናት ሰነድ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር ላይ መነሳቱ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተጓዘው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ አመርቂ ውጤቶች፣ የይዘትና የአቀራረብ ብቃት ወዘተ በሚሉ መስፈርቶች ተመዝኖ በስልጠና መስክ የሀገርን ችግሮች ከሚፈቱ ቀዳሚ ጥናቶች አንዱ ሆኗል፡፡
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የኮሌጁ አሰልጣኞች ''የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ሰልጣኞች በስልጠና መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕ‹ሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት እንዲት ማሳደግ ይቻላል?›› በሚል ርዕስ የተሰራው ከኮሌጁ ባሻገር የከተማ አስተዳደሩን የሚዲሊያ ባለቤት አድርጎታል፡፡
በዚህ የውድድር ዘርፍ ከ12 ክልሎችና ከ2 ከተማ አስተዳደሮች 14 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነዶች ቀርበው በጀኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የተሰራውና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን የወከለው ጥናት 2ኛ ደረጃን ይዞ ሲያጠናቅቅ የአማራ ክልል 1ኛ ደረጃ የኦሮሚያ ክልል ደግሞ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
4ኛው ሀገር አቀፍ የብቃት ውድድር በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት የተካሄደ ሲሆን ውድድሩም በክህሎት፣ በቴክኖሎጂ እና በተግባራዊ ጥናትና ምርምር ዘርፎች የተደረገ እንደነበር መዘገባችን አይዘነጋም፡፡