እሁድ:- ግንቦት 3 ቀን 2017 ዓ.ም
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት ውድድር ኮሌጁ 3 ሜዲያሊያዎችን አገኘ!!
በሀገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር በአሰልጣኞችና ሰልጣኞች ውድድር ውጤት ኮሌጁ 3 ሜዲያሊያዎችን አግኝቷል።
ዘንድሮ "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል ከሚያዚያ 27 እስከ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው 4ኛው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ሰልጣኞች በተለያየ ክህሎት አሰልጣኞች ደግሞ በጥናትና ምርምር ኮሌጁ ሜዲያሊያዎችን እንዲያገኝ አድርገዋል።
የኮሌጁ አሰልጣኞች ''የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ሰልጣኞች በስልጠና መጨረሻ ዓመት ላይ በሚሰሯቸው ፕሮጀክቶች እና ድህረ ልምምዶች ላይ የሰልጣኞችን ልል ክህሎት እንዴት ማሳደግ ይቻላል?›› በሚል ርዕስ የተሰራው ጥናት 2ኛ ደረጃን ይዞ የብር ሜዲያሊያ እና የ400ሺ ብር ሽልማት አስገኝቷል።
በሰልጣኝ የክህሎት ፉክክር ደግሞ በጋርመንት ፕሮዳክሽን የወርቅ ሜዲያሊያ ና የ500ሺ ብር ሽልማት እንዲሁም ከኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት በስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ሙያ የነሐስ ሜዲያሊያና የ300ሺ ብር ሽልማት ተበርክቷል።
በተያያዘ ዜና በ12 ክልሎችና በ2 ከተማ አስተዳደሮች በተካሄደው የክህሎት ውድድር ድምር ውጤት የአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር አንደኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ረቡዕ:- ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ∙ም
ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደረገ!!
በተለያየ ዘርፍ ለተሰማሩ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች የቴክኖሎጂ ሽግግር ተደረገ፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና የኮሌጁ ዲኖች በተገኙበት 15 ከሚሆኑ የአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ባለቤቶች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
የመድረኩ መሰረታዊ ዓላማ በኮሌጁ የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን ለማሸጋገር እና በተቋሙ የሚገኙ የተለያዩ ዘመናዊ ማሽነሪዎችን ተጠቅሞ አዳዲስ ምርቶችን በጋራ ለማምረት በሚቻልበት ሂደት ላይ ምክክር ለማድረግ ነው፡፡
የኢንዱስትሪዎቹ ባለቤቶችም የተሰሩ ቴክኖሎጂዎችን እና በኮሌጁ ያሉ ማሽኖችን ጎብኝተው ቴክኖሎጆዎችን አሸጋግረው ለማብዛት እንዲሁም ማሽነሪዎችን በመጠቀም በጋራ የማልማት ስራ ለማከናወን መግባባት ተችሏል፡፡
የተቋሙ ስልጠናዎች የገበያውን ቅበላ መሰረት ያደረገ እንዲሆኑ ለማስቻል በአጫጭርም ሆነ በመደበኛ መርሃ ግብሮች የሚሰጡ ስልጠናዎች በጋራ እየተገመገሙ መሰጠት እንዳለባቸው ውይይት ተደርጓል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

አርብ:- ግንቦት 8 ቀን 2017 ዓ.ም
ከተመራቂ ሰልጣኞች ጋር ውይይት ተካሄደ!!
ከ2017 ዓ.ም ተመራቂ ሰልጣኞች ጋር በስልጠና ማጠናቀቂያ ሂደት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
ከተመራቂ ሰልጣኞች ጋር በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ስለ ስልጠና ማጠናቀቂያ፣ ስለ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምዘና እና ከምረቃ በኋላ ስለሚደረገው የስራ ትስስር ሂደት ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ቀሪ ስልጠናዎችን እስከ ግንቦት 30 በማጠናቀቅ ከሰኔ 1ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በተቋም ደረጃ የተዘጋጀውን ምዘና፣ በአዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ የተዘጋጀውን ሞደል ፈተና እና በሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማዕከል የተቀረፀውን ምዘና ተፈትኖ በማለፍ የመመረቂያ ቀናቸውን እንዲጠባበቁ ተነግሯል።
ኮሌጁ በዚህ ዓመት በ3ቱም የስልጠና መርሃ ግብር ላይ የሚገኙ 1531 ሰልጣኞችን ለማስመረቅ ዕቅድ ይዟል።
በመጨረሻም ከእጩ ምሩቃን የተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ከመድረኩ ምላሽና የማጠቃለያ ሀሳቦች ተሰጥቶባቸው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።

የዳግማዊ ምኒልክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎች በኮሌጁ የሚሰጠውን የሙያ ስልጠና ጎበኙ!!
የዘመናዊ ትምህርት ችቦ የተለኮሰበት ተቋም ነው በሚባለው ዳግማዊ ምኒልክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እየተማሩ የሚገኙ ሴት ተማሪዎች በኮሌጁ እየተሰጠ ያለውን የሙያ ስልጠና በዛሬው ዕለት ምልከታ አድርገዋል።
ጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የ9ኛ እና የ10 ክፍል እንዲሁም ከ11ኛ እና ከ12ኛ ክፍል ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ዘርፍ የተውጣጡ ሴት ተማሪዎች እንደሆነ ተነግሯል።
ስለኮሌጁ ታሪካዊ ዳራና እየተሰጡ ስላሉ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች በኮሌጅ ባለሙያዎች ገለፃ ተደርጎላቸው የኮሌጁን አጠቃላይ ስነ ምህዳርና የማሰልጠኛ ወርክሾፖችን እንዲጎበኙ ተደርጓል።
በዕለቱ 150 የሚሆኑ ሴት ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የሀሁ ጆብስ ዲጂታል ጆብ ማቺንግ ድርጅት አካል የሆነውና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ 4 የመንግስት 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ፣ የምህንድስና እና የሒሳብ ትምህርቶች ላይ አቅም ለማሳደግ እየሰራ የሚገኘው ስቴም ኢዱኬሽን ፎር ኢምፓወርመንት ፕሮጀክት ከኮሌጁ ስራ ትስስር እና ምክር አገልግሎት የስራ ክፍል ጋር በመተባበር ነው።
የጉብኝቱ መሠረታዊ ዓላማ ሴት ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጎልበትና ለቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው ተብሏል።
ፕሮጀክቱ ዳግማዊ ምኒልክ 2ኛ ደረጃን ጨምሮ ደጃዝማች ወንድራድ፣ ኮከበ ፅባህ እና ተስፋ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ እየሰራ ሲሆን ከዚህ በፊት የደ/ ወንድራድ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሴት ተማሪዎችም በተመሳሳይ ጉብኝት አድርገዋል።