General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ቅዳሜ፡- ታህሳስ 26 ቀን 2017 ዓ.ም

               #ማስታወቂያ

  ለኮሌጃችን የውስጥ ሰራተኞች እና  ለውጪ የተቋማችን አጋር  ማኅበረሰብ በሙሉ

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋማዊዩ የግል ኢንተርፕራይዝ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓል ያደለባቸውን ምርጥ #በሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለመሸጥ እንሆ ይላል፡፡

ስለሆነም በተዘጋጀው ጥቂት የመሸጫ ቀናት ውስጥ ፈጥነው በመምጣት የመረጡትን ሰንጋ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት የሚችሉ መሆኑን ስንገልጽልዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡

ዝም ብሎ በሬ አለ በሬ ብሎ ዝምም አለ። የእኛዎቹ በሬ ብሎ ዝም ናቸው ይላል ጀነራል ዊንጌት የግል ኢንተርፕራይዝ።

እንደ ስማችን ዊን_ጌት የሆኑ ሰንጋዎችንን መርጠው ለመግዛት ከፈለጉ ይምጡ ለበዓል ይሸምቱ ተብላችኋል።

#አድራሻ፡-   ቦታ - ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ
             ስልክ - 0991824160

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሰኞ፡- ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ/ም                                                                                            
‹አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡›› ሉቃ 2፡11

ለኮሌጃችን የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡

                   የጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ማክሰኞ፡- ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

የአሰልጣኞች ኢንዱስትሪ አታችመንት ቆይታ ግምገማ ተደረገ!!

ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሄደው የነበሩ አሰልጣኞች የአታችመንት ቆይታ ግምገማ ዛሬ ጥር 6 ቀን 2017 ዓ.ም
ተደረገ።

የአሰልጣኞች ኢንዱስትሪ አታችመንት ዓላማ አሰልጣኞቹ በጽንሰ ሀሳብ የሚያውቁትን ሙያ በኢንዱስትሪዎች ካዩት የስራ ባህል፣ ልምድ፣ ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ እና ከአዳዲስ አስራር ስርዓት አንጻር ሰልጣኞቻቸውን ከገሀዱ የስራ ዓለም ጋር በተግባር አገናኝተው ስልጠና እንዲሰጡ ታቅዶ ነው።

በዚህ የኢንዱስትሪ አታችመንት ላይ ከ3 ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ 9 አሰልጣኞች በተለያየ ምርት እና አገልግሎት በሚሰጡ 7 ኢንዱስትሪዎች ለአንድ ወር ያህል ቆይታ ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን አብዛኛዎቹ /7ቱ/ የቴክስታይ ሌዘር ጋርመንት ዲፓርትመንት አሰልጣኞች ናቸው፡፡

አሰልጣኞቹ በቆይታቸው ያገኙትን ልምድና ለኢንዱስትሪው ያስተላለፉትን እውቀት በስፋት ገለፃ አድርገዋል፡፡

የአታችመንቱ መርሃ ግብር የአሰልጣኞችን አቅም ከማጎልበት አንጻር ከሚከወኑ ተግባራት አንዱ ሲሆን አሰልጣኞች የስራ ገበያውን ስርዓት በአካል ልምድ ቀስመው እና ስልጠናውን ከነባራዊ የኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር አዛምደው እንዲተገብሩ ቀጣይም ይህንን ስራ በስፋት ለማከናወን ዕቅድ መያዙን የኮሌጁ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ አሳውቋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ቅዳሜ:- ጥር 10 ቀን 2017 ዓ.ም
                                               
‹ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከዮርዳኖስ ወደ ገሊላ መጣ፡፡›› ማቴ 3፥13

ለኮሌጃችን የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና የተቋማችን አጋሮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የፍቅር ይሆንላችሁ ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡

 የጀነራል  ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ማክሰኞ፡- ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም

የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2017 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ጥር 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የግማሽ ዓመቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት የኮሌጁ ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በግማሽ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን ረገድ እምርታዊ ለውጥ ያሳዬ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀሪው ግማሽ ዓመት ከስልጠና ሂደት፣ ከግብዓት አቅርቦት፣ ከውስጥ አሰራር፣ ከተቋማዊ ልማት እና ከማህበራዊ አግልግሎት አንፃር ቢስተካከሉ ያሏቸውን ገንቢ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ቅዳሜ፡- ጥር 17 ቀን 2017 ዓ.ም

     የአይደያ ባንክ /የሀሳብ ማቆር/ ማሰባሰብ ውይይት ተደረገ!!

በኮሌጁ የኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት አሰልጣኞች ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም የአይደያ ባንክ ማሰባሰብ ውይይት ተካሄደ፡፡

በስልጠና ዘርፉ ቀጣይ ላይ የሚተገበሩ አዳዲስ ሀሳቦችን በማሰባሰብና ወደ ተግባር በመቀየር ተቋሙ የሚጠበቅበትን ተከታታይ ለውጥ የማምጣት ኃላፊነት እንዲወጡ ለማድረግ የተካሄደ ሲሆን መድረኩን የመሩት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡

ከዚህ በፊት በኮሌጁ ላሉና በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ አንዳንድ ቢሮች የዕድሳትና የማዘን ስራዎችን በመስራት ረገድ የዲፓርትመንቱ አሰልጣኞች ሚና የላቀ መሆኑ ተገልፆ ቀጣይም ይህ ተግባር ተጠናክሮ እንዲሰራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚመጡ በርካታ ተቋማት በኮሌጁ ያለውን እምርታዊ ለውጥ ልምድ ለመውሰድ የሚመጡት ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አሻራ ያረፈበት ስኬት ሲሆን ወደ ፊትም የተሰበሰቡ ሀሳቦች በጥራት እንደሚተገበሩ እንተጋለን ተብሏል፡፡

የውይይት መድረኩ የተካሄደው በአስደማሚ ሁኔታ በታደሰው የኮንፈረስ ክፍል ሲሆን የዲን ቢሮ ጽ/ቤትን ጨምሮ የኮንፈረስ ሩሙ ውበትን እንዲጎናፀፍ ያደረጉት የኮንስትራክሽን፣ የውድ ወርክ፣ የኤሌክትሪክሲቲ፣ የጋርመንት እና ሌሎች ዘርፍ አሰልጣኞች የየድርሻቸውን በየሙያቸው ማበርከታቸው ታውቋል፡፡   

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ቅዳሜ፡- የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም

ኮሌጁ የሰራተኞች የአንድነት ቀን በዓል አከበረ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰራተኞች የአንድነት ቀን /Get together/ በዓልን ዛሬ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በእንጦጦ ፓርክ ፍሬሽ ኮርነር ኪችን አከበረ።

በዕለቱ የኮሌጅ ሰራተኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የጋራ ማዕድ መካፈል መርሃ ግብር የተከናወነ ሲሆን በኮሌጁ ዲን በአቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት ዝግጅቱን በማስመልከት መልዕክት ተላልፏል። የኮሌጁ ዲን በመልዕክታቸው <<የዛሬው ዝግጅት ተቋማችን ሁሉን አቀፍ ስኬት እንዲጎናጸፍ የሁሉም ሰራተኛ አበርክቶ የጎላ በመሆኑ ስላደረጋቸሁት ሁሉ ለማመስገን የተዘጋጀ ሲሆን ቀጣይም ዊንጌትን በጋራ ስኬቱን ለማሰቀጠል ቃል የምንገባበት ነው>> ብለዋል።

በዝግጅቱ የተለያየ ዓይነት የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን በኮሌጁ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና አሁን ላይ በጡረታ ለተሰናበቱ ባለውለታዎች፣ በኮሌጁ አመራር ለነበሩና በመሪነት ወደ ሌላ ተቋም ለተዛወሩ፣ በ2016 ዓ.ም ምርጥ ቴክኖሎጂ ለሰሩ አሰልጣኞች፣ በክህሎት ውድድር አሸናፊ ለነበሩ አሰልጣኞች እንዲሁም ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምር ላደረጉ አሰልጣኞች የሰርተፊኬት እና የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዕለቱ በዝግጅቱ ላይ የታደሙት የኮሌጁ ሰራተኞች በፕሮግራሙ መደሰታቸውን ገልጸው የዚህ ዓይነት መርሃ ግብር ከተዝናኖት ባሻገር የስራና የእርስ በእርስ ማህበራዊ ትስስርን ያጠናክራል ብለዋል።

በመጨረሻም የጋራ ማዕድ መርሃ ግብሩ ዝግጅት መስተንግዶ ተከናውኖ ልዩ ልዩ ሽልማት እና አዝናኝ ጨዋታ መርሃ ግብር ተደርጎ የዝግጅቱ ፍጻሜ ሆናል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት»