ሰኞ:- ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ∙ም
ከ3ሺ 300 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞች በ2 ሳምንት ተመዘገቡ!!
ኮሌጁ የ2017 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን ከጥቅም 15 ቀን 2017 ዓ∙ም ጀምሮ በበየነ መረብ /online/ እና በሀርድ ኮፒ ለ2 ሳምንታት የመዘገበ ሲሆን በዚህም 3365 የሚሆኑ አዳዲስ ሰልጣኞችን መዝግቧል።
ኮሌጁ አሁን ላይ በISO 9001:2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፤ የስልጠና ጥራቱን ለማሳደግ ከግዙፍ አገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በትብብር መስራቱ እና ባለው ተቋማዊ ዘርፈ ብዙ ፋሲሊቲዎች ለስልጠና ጥራቱ ትኩረት መስጠቱ ተመራጭነቱን ይበልጥ ስላሰፋው ከፍተኛ ተመዝጋቢ ካላቸው የመዲናችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ ተርታ ይሰለፋል።
ውድ አዳዲስ ተመዝጋቢዎች! በመሉ እምነት እኛን ተማምናችሁ መርጣችሁን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።
የምዝገባ ቀናትን በተመከለተ ምንም እንኳን እስከ ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ለማጠናቀቅ ቢታቀድም በተለያየ ምክኒያት ምዝገባቸውን ላላጠናቀቁ አመልካቾች ተጨማሪ 4 ቀናት ዕድል ተመቻችቷል።
ስለሆነም እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ባሉበት ሆነው በበየነ መረብ /online/ ወይም በኮሌጁ በአካል በመገኘት መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን ስናበስርዎት በታላቅ ደስታ ነው።
የሙያ ምርጫን በተመለከተ በማታና በቅዳሜና እሁድ ለምትሰለጥኑ በፍላጎታችሁ የምትስተናገዱ ሲሆን ለቀን አመልካቾች ደግሞ ከቢዝነስ፣ ከአይሲቲ፣ ከአውቶሞቲቭ እና ከፉሽን ዲዛይን ዲፓርትመንቶች ውጪ ባሉ ሙያዎች እንደ ምርጫችሁ ትስተናገዳላችሁ።
ስለሆነም በተቀመጡበት ቀሪ ቀናት ፈጥነው እንዲመዘገቡ እየመከርን ከዚያ በኋላ የመመዝገቢያ ሰንደቁ /ሊንኩ/ የሚዘጋ መሆኑን እንገልፃለን።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

Forwarded from General Wingate Polytechnic college-Official channel

ውድ ተመዝጋቢዎች
Registration ላይ
DOB(Date of Birth) ስታስገቡ በሀበሻ እንዲሁም Date of commencement(1ኛ ክፍል የገባቹበት ዓ.ም) በሀበሻ ይሁን
የቤት ቁጥር የሌላቹ New በሉት::

Forwarded from K-Raj 🌍 AB
https://youtu.be/3KnstGeVto0
Students are not registering, I observe that, most of new trainees are thinking as the registration is done by only making Application form in last weeks,
So notifying them is good! may if it makes more clear more full detailed registration videos is here, it is good there them

ሰኞ፡- ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ለአዲስ ተመዝጋቢ የቀን ሰልጣኞች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተካሄደ!!
በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2017 ዓ.ም ላይ ሙያዊ ስልጠናቸውን ለመከታተል ላመለከቱ አዳዲስ የቀን ሰልጣኞች በዛሬ ዕለት የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተዘጋጀላቸው፡፡
በዚህ መድረክ ላይም በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ለመከታተል ያመለከቱ አዳዲስ ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ የኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ አድማሱ በቀለ በቦታው በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ምክትል ዲኑ በመልዕክታቸው እኛን መርጣችሁ ስለመጣችሁ እናመሰግናለን፤ ኮሌጃችንንም በመምረጣችሁ ዕድለኞች ናችሁ፡፡ ተግታችሁ ከሰለጠናችሁ ደግሞ የስራ ገበያው ኢንዱስትሪዎች የምረቃ ቀናችሁን ሳይጠብቁ ቀድመው ሊወስዷችሁ በራቸው ክፍት ነው ብለዋቸዋል፡፡
የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብሩን ምክኒያት በማድረግ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስሙ የጎላው ሰርከስ ዊንጌት ልዩ ልዩ አዝናኝ ትርኢቶችን በማቅረብ ታዳሚዎችን ያስደመመ ሲሆን ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት ዲፓርትመንት ደግሞ በሰልጣኞች የተሰሩ የፋሽን ዲዛይኖችን መድረክ ላይ በማሳየት ስልጠናቸውን የማስተዋወቅ ስራ አከናውነዋል፡፡
አሁኑ ላይ በሶስቱም የስልጠና መርሃ ግብር ማለትም በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜና እሁድ 4045 የሚሆኑ አዳዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች በኮሌጁ ገብተው ለመሰልጠን ያመለከቱ ሲሆን በቀኑ የስልጠና ጊዜ ለመከታተል ያመለከቱ አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ላይ መደበኛ ስልጠናቸውን እንደሚጀምሩ ታውቋል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››