General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
https://youtu.be/3KnstGeVto0
Students are not registering, I observe that, most of new trainees are thinking as the registration is done by only making Application form in last weeks,
So notifying them is good! may if it makes more clear more full detailed registration videos is here, it is good there them
ለሁሉም የቀን አዲስ ገቢ ሰልጣኞች

ከ16/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የስልጠና ልብስ(ጋወንና ቱታ) ሳይለብሱ ወደ ግቢም ሆነ ወደ ስልጠና ክፍል መግባት የማይቻል መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተገለፀው መሰረት አዘጋጅታችሁ በመልበስ የምትመጡ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
በዚህ ሳምንት

አርብ፡- ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

ከሀገረ ጀርመን የመጡ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ ጉብኘት አደረጉ!!

በሀገረ ጀርመን የኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ዘርፍ ላይ የሚሰሩ የልዑካን ቡድን አባላት ከትናነት በስተያ በኮሌጁ ጉብኘት አድርገዋል።

የልዑካኑ ጉብኝት መሰረታዊ ዓላማ ጀርመን በአሁኑ ሰዓት በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ባጋጠማት የሰለጠነ የሰው ሃበት እጥረት ምክኒያት በሙያው ብቁ የሆኑ ዜጎችን ከሀገራችን በመመልመል ለመቅጠር እቅድ በመያዟ ኮሌጃችን እንደ አንድና ዋነኛ ብቁ የሰው ሃይል መገኛ ተቋም በመያዙ ነው።

በዚህም በመጀመሪያው ዙር ምልከታና ውይይት ኮሌጁ ዘመኑ በደረሰበት የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደረጃና የአስተሳሰብ ምጥቀት ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ያለው ቁሳዊና ሰብዓዊ ግብዓት ምን ይመስላል የሚለውን ማሳየትና ማስጎብኘት ተችሏል።

ይህ እቅድ ስምምምነት ላይ ተደርሶ ወደ ትግበራ ከተገባ የጀርመንና የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር ባሻገር ቀጣይ ዓለማቀፋዊ የስራ ትስስር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰው ሃብት ልማት ትብብር እና መሰል ሀገራዊ ትሩፋቶች ላይ የሚኖረው ዕድል ላቅ ያለ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡

ቀጣይ በዚሁ ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ንግግሮችና የመግባቢያ ስምምነቶች እንደሚኖሩ የሚጠበቅ ሲሆን ወደ ትግበራ ሲገባ ለሰልጣኞች ቋንቋን ጨምሮ ከጀርመን ሀገር የስራ ባህል ነባራዊ ሁኒታ ጋር የሚያያዙ የተለያዩ ስልጠናዎች እንደሚሰጣቸውም ይጠበቃል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
በዚህ ሳምንት

አርብ፡- ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

ለኮሌጁ ሴት ሰራተኞች ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጁ ለሴት ሰራተኞች በስርዓት ጾታ ላይ ያተኮረ የ5 ቀናት የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፡፡

በኮሌጁ ለሚገኙ ሴት ሰራተኞች ከህዳር 2 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ/ም ቆይታ የነበረው ሴቶችን ማጎልበት /woman empowerment/ ላይ ያተኮረ የስርዓተ ፆታ ስልጠና በባለሙያ ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናው ሴቶች ላይ ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ ማህበራዊ እና ባህላዊ ሁነቶች ተጠብቀው ያለባቸውን ልዩ ልዩ ኃላፊነት በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ነው ተብሏል፡፡

ስልጠናው በስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ እና በልዩ ልዩ ምልከታ ጥናት መሰረት መካሄዱን የኮሌጁ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን ቢሮ አሳውቆናል፡፡

የዘርፉ ምክትል ዲን የሆኑት አቶ ሰባሁዲን ሁሴን በስልጠናው ላይ ተገኝተው ኮሌጃችን አሁን ላይ እያመጣ ላለው ስርነቀላዊና እምርታዊ ለውጥ የእያንዳንዱ ሰራተኛ አሻራ ያረፈበት ነው።

ለዚህ ፈጣንና ቀጣይነት ላለው ተቋማዊ ዕድገት ደግሞ የሴቶችን ሁለንትናዊ አቅም ማሳደግ ወሳኝ በመሆኑ ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለግል ህይወታችሁም ሆነ ለተቋማዊ ስራችሁ ለውጥ የምታመጡበት ሊሆን ይገባል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ለሁሉም የቀን አዲስ ገቢ ሰልጣኞች

ከ16/03/2017 ዓ.ም ጀምሮ የስልጠና ልብስ(ጋወንና ቱታ) ሳይለብሱ ወደ ግቢም ሆነ ወደ ስልጠና ክፍል መግባት የማይቻል መሆኑን አውቃችሁ ከላይ በተገለፀው መሰረት አዘጋጅታችሁ በመልበስ የምትመጡ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንድትዘጋጁ እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
በዚህ ሳምንት

አርብ፡- ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ.ም

ለአዲስ ገቢ የቀን ሰልጣኞች የ3 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ!!

ለአዲስ ገቢ የቀን ሰልጣኞች ከህዳር 4 እስከ ህዳር 6 ቀን 2017 ዓ/ም የቆየ የ3 ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ።

ሰልጣኞች ወደ መረጡት የሙያ መስክ ስልጠና ከመግባታቸው በፊት ራዕይ ነድፈው እና ዓላማ ቀርጸው የሙያ ክህሎታቸውን በብቃትና በትጋት ለማሳደግ የሚረዳቸውን አዎንታዊ ምልከታ ለማስረጽ ታቅዶ መሆኑን ከስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ ሰምተናል።

ይህን መሰል ስልጠና ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች አስቀድሞ የመስጠት ልምድ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተደረገ ሲሆን ሰልጣኞች ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ እይታቸው እንዲጎለብት፣ እንደ ተቋም ምልከታ ማህበራዊ እና ስነ ልቦናዊ ለውጥ ለማምጣት፣ የበቃና የነቃ ሙያተኛ ለመፈጠር እንደሚረዳ ተገልጿል።

ኮሌጁ በአሁኑ ሰዓት በሁሉም የሙያ መስኮችና የስልጠና እርከኖች በአጠቃላይ 4310 አዲስ ገቢ ሰልጣኞችን የተቀበለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 1950ዎቹ በቀኑ የስልጠና መርሃ ግብር የሚሳተፉ ናቸው።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››