General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

ለ27 አሰልጣኞች የተግባራዊ ጥናትና ምርምር አዘገጃጀት ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጁ ለሚገኙ 27 አሰልጣኞች በተግባራዊ ጥናትና ምርምር /አክሽን ሪሰርች/ አሰራር ዙሪያ የ10 ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ስልጠና ዓላማ እንደ ተቋም ያሉ የስራ ክፍተቶችን በጥናትና ምርምር መልስ እየሰጡና የሚስተዋሉ ችግሮችን በራስ አቅም በየጊዜው እየፈቱ ለመሄድ ታቅዶ መሆኑን በኮሌጁ የጥናት፣ ምርምርና ፐብሊኬሽን የስራ ክፍል አስተባባሪዋ ወ/ሮ ምስራቅ ደለሳ ነግረውናል፡፡

ስልጠናው ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ለተውጣጡ አሰልጣኞች የተሰጠ ሲሆን በጽንሰ ሀሳባዊ ገለፃና በተግባር ልምምድ ቀርቧል፡፡

በ2016 ዓ.ም በቴክኒክና ሙያ ሳምንት ቀን በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራው ጥናትና ምርምር ችግር ፈቺነቱ እንደ ከተማ 1ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
የመቁረጫ ነጥብ ይፋ ተደረገ።

የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ዛሬ ይፋ ተደርጓል።

የመቁረጫ ነጥቡ ዝርዝር ከታች ተያይዟል።
የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል።

የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 እና ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 እና ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

⬇️

የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

🟢 የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

🟡 የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

🔴 የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤

° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን
#ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤

° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤

° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤
ማክሰኞ:- ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተውጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ!!

በኢንዱስትሪው የትብብር ስልጠና ላይ የኮሌጁን ሰልጣኞች የተግባር ስልጠና ለሚሰጡ የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የ3 ቀን ስልጠና ተሰጠ፡፡

የስልጠናው መሰረታዊ ዓላማ በኮሌጁ እየሰለጠኑ ለሚገኙ መደበኛ ሰልጣኞች የተግባራዊ ስልጠናን በትብብር በሚሰጡ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች ለሰልጣኞቹ በቂ ግንዛቤ እንዲያስጨብጡ ታቅዶ ነው፡፡

የኢንዱስትሪዎቹ ባለሙያዎች በቆይታቸው በትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ዙሪያ፣ በስልጠና ባህል እና በአሰለጣጠን ስነ ዘዴ ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ሲሆን በዛሬው ዕለት የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸው ተጠናቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"