ሐሙስ፡- መስከረም 9 ቀን 2016 ዓ.ም
#ማስታወቂያ
ለኮሌጃችን የውስጥ ሰራተኞች እና ለውጪ የተቋማችን አጋር ማኅበረሰብ በሙሉ
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋማዊዩ የግል ኢንተርፕራይዝ ያደለባቸውን 9 #በሬዎች በከፍተኛ ጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለመሸጥ አቅዷል፡፡
ስለሆነም በተዘጋጀው ጥቂት የመሸጫ ቀናት ውስጥ ፈጥነው በመምጣት የመረጡትን ሰንጋ በበሬዎቹ ፎቶ ላይ በተለጠፈው የዋጋ ዝርዝር መሰረት ከፍለው መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ስንገልጽልዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡
ለመስቀል በዓል፣ ለተለያዩ ዝግጅቶች ወይም የስጋ አምርዎቶን ቁርጥ ለማድረግ ካሰቡ ወደየትም አይሂዱ፤ የስጋ ፍላግዎቶን ለማርካት እኛ ጋር ኑ አስር ጊዜ ለክተው አንድ ጊዜ ይመርጡናል እንጂ አያወዳድሩንም ይላል የኮሌጁ ተቋማዊዩ የግል ኢንተርፕራይዝ፡፡
ቀንበር ያልተጫነባቸውና ጅራፍ ያላረፈባቸው የእርድ ቅልብ ሰንጋዎቻችንን መርጠው ለመግዛት ከፈለጉ
#አድራሻ፡- ቦታ - ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ
ስልክ - 0991824160
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

👍16👎4
ማክሰኞ:- መስከረም 14 ቀን 2017 ዓ.ም
የኮሌጁ የስነ ምግባርና ፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት እቅድ ውይይት ተደረገበት!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስነ ምግባርና ፀረሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት የ 2017 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ትናንት መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በተያዘው በጀት ዓመት ትኩረት አድርጎ የሚሰራቸውን የክትትልና የግንዛቤ ስራዎችን የሚያሳይ እቅድ የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት አቅርቦ አወያይቷል፡፡
በዕለቱ ለውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ የተቋማት ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ም/ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን ሲሆኑ ም/ዲኑ በንግግራቸው በ2017 በጀት ዓመት ዳይሬክቶሬቱ መልካም አስተዳደር የበለጠ እንዲሰፍን እና የሙስናና ብልሹ አሰራር እሳቢዎችና ተግባራት እንዳይፈጸሙ ለመከላከል በትኩረት ለመስራት ያግዘው ዘንድ እቅዱን ለባለድርሻ አካላት ማሳወቁ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡::
በወቅቱ የስራ ክፍሉን እቅድ ለተሳታፊዎች ያቀረቡት ደግሞ የኮሌጁ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት አቦነህ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሯ ከእቅድ ውይይት ባሻገር እንደ ከተማ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚከናወነውን የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ተግባር ገለፃ በመስጠት ቀጣይ ሁሉም ሰራተኞች በተዘጋጀው ቅጽ መሰረት የሀብታቸውን መጠን የሚሞሉበትን ሂደት አሳውቀዋል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍9❤1