እሁድ፡- ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
እጅግ ያሳዝናል!!
ዜና እረፍት!!!!!
የኮሌጃችን የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ የነበረቺው አሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ህይወቷ በድንገት አለፈ፡፡
አሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ባጋጠማት ድንገተኛ ህመም በየካቲት 12 ሆስፒታል በህክምና ስትረዳ ቆይታ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ልትለይ ችላለች፡፡
አሰልጣኝ ትደነቅ በአካውንቲንግ ኤንድ ፋይናንስ ሙያ ተመርቃ የካቲት 1 ቀን 2012 ዓ/ም ኮሌጃችንን በመቀላቀል ህይወቷ በሞት እስካለፈችበት ድረስ የቢዝነስ ዲፓርትመንት አሰልጣኝ ነበረች፡፡
አሰልጣኝ ትደነቅ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ ልጅ እናትም ነበረች፡፡
የአሰልጣኝ ትደነቅ ምስክር ሰርዓተ ቀብር ነገ ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 6፡00 ላይ በቦሌ አራብሳ ቅ/ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን መካነ መቃብር የሚፈፀም መሆኑን እየገለጽን ለእርሷ እረፍተ ነፍስን ለቤተሰበቿ፣ ለኮሌጁ ማህበረሰብ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ ደግሞ መጽናናትን እንመኛለን፡፡

😢115👍12❤8🙏6
Forwarded from Am
Nege yemijemirew siltena bota block 58 sihon sime zirzirachu ይሄ new
👍2👌1
ቅዳሜ፡- ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም
የ1980 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ ሰልጣኞች ከ36 ዓመት በኋላ በኮሌጁ ተገናኙ!!
ብዙዎቹ የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ዘርፍ ተማሪዎች የነበሩ የቀድሞዎቹ የ1980 ዓ/ም ተመራቂ ሰልጣኞች ከ36 ዓመታት በኋላ ዛሬ ነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ተገናኝተዋል።
በቀድሞው ጀነራል ዊንጌት ኮንስትራክሽንና ሙያ ት/ቤት በአሁኑ ደግሞ ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ3 ዓመት የሙያ ስልጠናቸውን 1980 ዓ/ም ላይ አጠናቀው ህይወት በመራቻቸው ጎዳን የተበተኑት የቀድሞዎቹ ተማሪዎች ወደ ኋላ 36 ዓመታትን ቆጥረውና ከተለያዩ ክፍለ ዓለማት ተጠራርተው የወጣትነት ት/ቤታቸውን እንደ መሰብሰቢያ ጥላ በመቁጠር በዛሬው ዕለት ተገናኝተዋል።
ያ የወጣትነት ዕድሜ ልዩ ትዝታ እንደ ማግኔት ስቦ አንድ ላይ ያሰባሰባቸው የቀድሞዎቹ ተማሪዎች በብዙ የህይወት ውጣ ውረድ ተፍትነውና በብዙ የዓለማችን ክፍሎች ተበትነው ዛሬ ላይ መሰባሰብ ሲችሉ በተማሪነት የነበራቸውን ትውስታና ገጠመኝ ለማወጋት ችለዋል።
አንዳንዶቹ ከአገር ውጪ ሆነው ርቀት ገድቧቸው፣ አንዳዶቹ ደግሞ እርፍተ ዘመን ገትቷቸው ሌሎቹም በልዩ ልዩ ምክኒያቶች በዕለቱ ባይገኙም በልቦና መንፈስ ተቃቅፈና ሃሳብ ለሃሳብ ተናበው ተገናኝተዋል።
በዛሬው ዕለት የተሰበሰቡት የቀድሞዎቹ ተማሪዎቹ ብቻ ሳይሆኑ የዚያን ጊዜ የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ዘርፍ መምህራን የነበሩት ባለ አሻራ አዛውንቶች ጭምር ተገኝተዋል። በህይወት የሌሉ አሰልጣኞች ደግሞ በቤተሰቦቻቸው ተውክለው ስብስቡን ወደ ቀረበ ቤተሰብነት አሳድገውታል።
በዛሬው ታሪካዊ ግንኙነት የነበሩ ሁነቶች የልጅነት ፎቶዎችን በመመልከት ከ36 ዓመት በኋላ ያለው አካላዊ ለውጥን ማነጻጸር፣ በህይወት ያሉን የሚኖሩበት ቦታ፣ ስራና ቤተሰባዊ ሁኔታ ማብራራት፣ ለቀድሞ መምህራንና ቤተሰቦቻቸው እወቅና እና ሽልማት ማበርከት፣ በአካል ያልተገኙትን ቀጣይ ለማፈላለግ ምክረ ሃሳብ ማካሄድ፣ በተለያየ ችግር ላይ ለሚገኙ ጓደኞቻቸው በልዩ ልዩ ማህበራዊ ድጋፍ መድረስ፣ ተቋሙ አሁን የደረሰበትን ደረጃ ለማየት ወርክሾፖችን መጎብኘት እና ለቀድሞው ት/ቤታችን ምን አይነት አሻራ እናስቀምጥ የሚሉት ይገኙበታል።
የቀድሞዎቹ የጀነራል ዊንጌት ተማሪዎች በውይይታቸው ቀጣይ የኤሌክትሪክ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ዲፓርትመንት የ1980 ምሩቃን በማስባሰብ ቤተሰብ ለማድረግ እንዳቀዱ ተገልጿል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍24🙏2🏆1