General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ይህ ከታች ያለው የ youtube ቻናል በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች የተከፈተ ሲሆን አላማው በTVET ዘርፍ ላይ እየተተገበሩ ያሉ የሚተገበሩ እና መተግበር ስለሚገባቸው አዳዲስ እይታዎች፣ስልጠናዎች እና የአዲሱን ምዘናን(Model COC) በተመለከተ መረጃዎች እና ስልጠናዎች በስፋት እና በጥራት የሚለቀቅበት በመሆኑ Subscribe አድርገው ቤተሰብ በመሆን በብዙ ያትርፉ።

https://m.youtube.com/@TvetInsight
👍211
አርብ፡- ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

               ማስታወቂያ

  ለኮሌጃችን ሠራተኞች በሙሉ

ነገ ቅዳሜ ማለትም ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም የሪፎርም ቀን ሲሆን ዕለቱ ''ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት'' በሚል መሪ ቃል ሁሉም የአዲስ አበባ አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ለተገልጋዮች መደበኛ አገልግሎት ይሰጣሉ።

ስለሆነም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሁላችሁም የኮሌጃችን ሠራተኞች በነገው ዕለት በመደበኛ ስራችሁ ተገኝታችሁ ስራችሁን እንዲትሰሩ እያሳወቅን የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎትም መኖሩን እንገልፃለን።

ማሳሰቢያ፦ አገልግሎቱ እንደመደበኛው ሰዓት ሲሆን የሰዓት ፊርማውም በጣት አሻራ መሆኑን እንጠቁማለን።

    የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
👍5👎32🏆2
አርብ:- ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ.ም

የመሻገር ቀን

ዛሬ የመሻገር ቀንን ምክኒያት በማድረግ ‹‹የመሻገር ጥረቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች›› በሚል መሪ ሐሳብ ጳጉሜ 1 ቀንን በትጋት እየሰራን እናስባለን፡፡

መሻገር ከትናንት ወደ ነገ፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከወንዙ ባሻገር ወደ ሌላኛው መንደር፣ ከአንድ ዘመን ወደ ሌላ፣ ከመጥፎ ወደ ጥሩ፣ ከድካም ወደ እረፍት፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ወዘተ ነው፡፡

እኛ እንደ ተቋም ባሳለፍነው ጊዜ በርካታ ድንቅና ብርቅ የሆኖ እምርታዊና መሰረታዊ ለውጦችን በማምጣት የላቀ ስኬት አስመዝግበናል፡፡ እነዚህ ተግባራት ደግሞ እንደ ኮሌጅ ለመሻገር ጓጉተን ለመድረስ ቸኩለን ያስመዘገብናቸው አስደናቂ ውጤቶች ናቸው፡፡

ሁላችንም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነን ለመሻገር በሩቅ ያቀድናቸውን ጭምር በቅርብ ማጠናቀቅ ችለናል፡፡ ለዚህ ስኬት ደግሞ የሁሉም አካል ርብርብ እና ቀና አመለካከት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ይህም ይቻላል የሚለውን አቅም አሳይቶናል፡፡

ያለፈው ጊዜ ውጤታማነታችን ለቀጣይ እቅዳችን ስንቅ ለጉዟችን ደግሞ ትጥቅ ስለሆነ መጪው ጊዜ እንደ ግልም ሆነ እንደተቋም የመሻገር ይሆንልን ዘንድ መልካም ምኞታችንን እንገልፃን፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍94
ቅዳሜ:-  ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም

       የሪፎርም ቀን

የኮሌጁ ሠራተኞች የሪፎርም ቀንን ምክንያት በማድረግ ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት በሚል ቃል ዛሬ ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በትጋት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል።

             ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍10👎21
ማክሰኞ፡- ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኮሌጃችን ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለ2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!!

አዲስ ዓመትን በአዲስ ህልም፣ በአዲስ ራዕይ፣ በአዲስ ተስፋ እና በአዲስ መንፈስ ለመቀበል የምንሻው በመሆኑ ዘመኑ የሰላም፣ የአንድነት፣ የፍቅር እና የዕድገት ይሆንላችሁ ዘንድ በጎ ምኞታችን ነው።
                                                                                     
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍2511