Forwarded from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
በአሽከርካሪነት ወደ ውጪ ሃገራት ለሥራ መሰማራት ለምትፈልጉ ዜጎች መልካም ዜና!
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በለማው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ለሥራ ስምሪት የተመዘገባችሁ በአሽከርካሪነት ሥራ ወደ ውጪ ሃገራት ለመሰማራት የሚጠበቅባችሁን ስልጠናና የምዘና ፈተና በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት(TI) ስር በሚገኘው የአሸከርካሪ ማሰልጠኛ እና በሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ ባለው ምሳሌ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ ስልጠናችሁን ወስዳችሁ የምዘና ፈተና (COC) መጨረስ ትችላላችሁ፡፡
በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት (E-LMIS) ላይ ያልተመዘገባችሁ እና በሹፍርና ሥራ ወደ ውጪ ሃገራት መሰማራት የምትፈልጉ በዚህ የድህረገጽ አድራሻ https://lmis.gov.et ሲስተም ላይ በመመዝገብና የባዮሜትሪክስ መረጃ በመሥጠት ሥልጠና እና የምዘና ፈተና መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አድራሻ;-
📌 የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት(TI) - ላምበረት የሥራና ክህሎት ሚንስቴር ዋናው መስሪያ ቤት አጠገብ
📌 ምሳሌ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ - ኮተቤ ሃና ማሪያም አካባቢ የሚገኘው
ሰላም ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ውስጥ
ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መረጃ
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ዋትስአፕ፡- https://whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et

👍11❤2
Forwarded from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
#የስልጠና ጥሪ
በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በተንከባካቢ ነርስነት፣ በነርስነት፣ በምግብ አብሳይነት እና በመሳሰሉ ሙያዎች መሰማራት ለምትፈልጉ ዜጎች
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለምቶ ተግባራዊ በተደረገው የኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(E-LMIS) ተመዝግባችሁ በውጪ ሃገር የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ በኢትዮጵያ ቱሪዝም ማሰልጠኛ (TTI) ተመዝግባችሁ ስልጠናውን መጀመር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
አድራሻ:-
ሜክሲኮ ቡናናሻይ እና ገነት ሆቴል
P.O.Box: 4350 Addis Ababa, Ethiopia
ስልክ :(+251)11 530 81 21/26
+251 11 551 94 18
Website: tti.edu.et

👍13❤2🏆1
ማክሰኞ፡- ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ እንደ ክላስተር ግምገማዊ ስልጠና ለአሰልጣኞች ተሰጠ!!
በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ለሚገኙ አሰልጣኞች በዛሬው ዕለት ግምገማዊ ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የቀረበ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት እንደ ከተማ የተዘጋጀ ነው፡፡
የግምገማዊ ስልጠናው መሠረታዊ ዓላማ አዲስ ዕይታና አዲስ አስተሳሰብ ያለዉ ምርታማ ሰራተኛን ለመፍጠር ፣ ለሃገር ዘላቂ ሰላምና ዕድገት የሚተጋ ሀገር ወዳድ ዜጋን ለመፍጠር እንዲሁም ከትርክት የዘለለ በምክንያት እና በእውነት የሚያምን አሰልጣኝን ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡
መድረኩ የመወያያ ሰነድ በማቅረብ እና የቡድን ውይይት በማድረግ ሲካሄድ የዋለ ሲሆን የቢሮ ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ እና የኮሌጆች አመራሮች የቡድኑን ውይይት መርተውታል፡፡
ለአሰልጣኞች እየተሰጠ ያለው ግምገማዊ ስልጠና ነገ ረቡዕ የሚጠናቀቅ ሲሆን ቀጣይ ቀናት ደግሞ ለአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሚሰጥ ተገልጿል፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍6🏆2❤1
ረቡዕ፡- ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
በነገው ዕለት ለምትመረቁ የኮሌጃችን ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለምረቃ በዓል ቀናችሁ በሰላም አደረሳችሁ!!
ውድ ተመራቂዎች
በብዙ ትጋት እና የዓላማ ፅናት ተጎዛችሁ በናፍቆት ስትጠብቁት ለቆያችሁት የምረቃ ቀናችሁ እንኳን በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ይቺ ዕለት ለእናንተ እና የስራ ፍሬያችሁን ለማየት ጓጉተው ቀን ከለሊት ብዙ ዋጋ ለከፈሉ ቤተሰቦቻችሁ እንዲሁም የእናንተን እንቁ ሙያ በጉጉት ለምትጠብቀው ውድ ሀገራችሁ ጭምር ልዩ ቀን ናት፡፡
እናንተ የምትገኙበት የወጣትነት ዕድሜ እና አሁን የቀሰማችሁት ሙያ ተደምሮ በሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ሀገራዊ ሰላም መስፈን ላይ የሚያመጣው አዎንታዊ ተፅዕኖ ትልቅ በመሆኑ ይህንን ተገንዝባችሁ ባገኛችሁት እውቀት፣ ባዳበራችሁት ክህሎት እና ባካበታችሁት በጎ አመለካከት ከራሳችሁ እና ከቤተሰቦቻችሁ ባሻገር የሀገርን ዕድገት እና ሰላም በሚያመጡ ተግባራት ላይ ልትተጎ ይገባል፡፡
ውድ ተመራቂዎች
ይህ የመጀመሪያው ምዕራፍ ስለሆነ ቀጣይ ወደ ስራው ዓለም ከመቀላቀላችሁ ባሻገር ሙያችሁን እያሻሻላችሁ እና የህይወት ጉዞ ደረጃችሁን እየሳደጋችሁ ለላቀው እና ለበለጠው ተልዕኮ ጭምር እንድትዘጋጁ በአንክሮት እንመክራለን፡፡
በመጨረሻም ከልጅነት እስከ ወጣትነት በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች አልፋችሁ እና ተፈላጊውን ሙያ ቀስማችሁ የወጣችሁ በመሆኑ በሀገር ላይ ያሉ መራራ ጣዕምን የሚያጣፍጡ ቅመሞች መሆናችሁን በመገንዘብ በሙሉ እምነት የፀና እና በተግባር የተገለጠ መክሊታችሁን በብዙ እጥፍ እንድታተርፉበት እየገለጽን በጉዛችሁ ሁሉ መልኳሙ ዕድል እና በጎው ስኬት እንዲገጥማችሁ እንመኛለን፡፡
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አካዳሚክ ኮሚሽን

👍21
Wednesday: August 21, 2024
Happy graduation day to all the trainees of our college who are graduating tomorrow!
Dear graduates
Wish you all the best for your long-awaited graduation day with a lot of hard work and determination.
This day is a special day for you and your families who have paid a lot of sacrifice day and night to see the fruits of your work, and also for your dear country, which is eagerly waiting for your precious career.
Your young age and the profession you have now taken together have a great positive impact on the country's economic growth and national peace, so you should realize this with the knowledge you have acquired, the skills you have developed and the positive attitude you have accumulated in activities that bring the country's growth and peace beyond yourself and your families.
Dear graduates
Since this is the first phase, we strongly recommend that you prepare for the next and better mission while improving your career and raising your level of life journey.
Finally, since you have gone through various education classes from childhood to youth, and have slowly emerged into a desirable profession, realizing that you are the spice that sweetens the bitter taste of the country, we wish you to gain many folds of your strong and practical talent, and we wish you good luck and good success in all your journeys.
General Wingate Polytechnic College Academic Commission

👍7🏆5
በነገው ዕለት ለምትመረቁ የኮሌጃችን ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለምረቃ በዓል ቀናችሁ በሰላም አደረሳችሁ!
በነገው እለት ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ ሚወስዱ ባስ ሚነሱባቸው ቦታ እና አስተባባሪዎች
አስኮ
ይሳቅ ሰይፉ +251 98 526 5461
አብርሃም እሸቱ +251 97 372 6272
ማፉዝ ወግአየው +251967452450
አየርጠና
ፍሮምሲስ ዮሃንስ +251924898428
ዮናስ ሰለሞን +251 91 355 2815
ሃብታሙ 093 294 0553
ዊንጌት
እስቲፋኖስ ዘውዱ +251 91 138 0537
ቃልአብ የማነ +251973412760
ሮባ ኢተፋ +251 96 135 8978

👍3
ለውድ ተመራቂዎች በድጋሚ
ነገ ሐሙስ(16/12/16ዓ.ም) የምረቃ ፕሮግራማችሁ በሚሊኒዬም አዳራሽ መሆኑ ይታወቃል። ቀኑ የስራ ቀን በመሆኑ መንገድ መዘጋጋት ስለሚኖር ይዘዋችሁ የሚሄዱት መኪኖች ከ12:30 በኋላ ስማይጠብቋቹ 12:00 በመገኘት ትራንስፓርቱን እንድትጠቀሙ እያሳወቅን በግል የምትሄዱ ከ1:30 ተኩል በኋላ ወደ አዳራሹ መግባት ስለማይቻል እንደደረሳችሁ ቶሎ በመግባት ከመድረኩ ፊትለፊት ባለው ወንበሮች እንድትቀመጡ እናሳውቃለን
ኮሌጁ

👍15👎5
ረቡዕ፡- ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለኮሌጃችን አስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች በሙሉ
ለኮሌጃችን አስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች ሐሙስ እና አርብ ይሰጣል የተባለው የ2 ቀን ግምገማዊ ስልጠና ነገ ሐሙስ የኮሌጁ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ ስርዓት ስለሆነ ስልጠናው አርብ እና ቅዳሜ ማለትም ነሐሴ 17 እና 18 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ሁሉም የዘርፉ ሰራተኞች በተቀያሬው ቀናት ሰዓት አክብራችሁ እንዲትገኙ እናሳውቃለን፡፡
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

👍3👎1
ረቡዕ፡- ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ እንደ ክላስተር ለአሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ግምገማዊ ስልጠና ተጠናቀቀ!!
በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር ለሚገኙ አሰልጣኞች ሲሰጥ የነበረው ግምገማዊ ስልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቆ ማጠቃለያ ተሰጠ፡፡
ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ቃል የቀረበ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ አማካኝነት እንደ ከተማ የተዘጋጀ ነበር፡፡
አዲስ ዕይታና አዲስ አስተሳሰብ ያለዉ ምርታማ ሰራተኛን፣ ለሃገር ዘላቂ ሰላምና ዕድገት የሚተጋ ሀገር ወዳድ ዜጋን እንዲሁም ከትርክት የዘለለ በምክንያት እና በእውነት የሚያምን አሰልጣኝን ለመፍጠር ነው የተባለለት ግምገማዊ ስልጠና የመወያያ ሰነድ በማቅረብ እና በተለያየ ደረጃ ላይ በሚገኙ አመራር አካላት የቡድን ውይይት በማድረግ ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው ዕለት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ተጠናቋል፡፡

👍10❤1🏆1