General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ጀነራል ዊንጌት በዚህ ሳምንት

በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመጀመርያ የሆነ ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በኮሌጁ የኤ.አይ(AI) ክበብ አቋቋመ።

በክበብ ምስረታ ላይ የ የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ጨምሮ ሌሎች የኢኒስቲቲዩቱ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የክበቡ መመስረት በኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን የሚደግፍ ይሆናል ።

በተያያዘም ኮሌጁ ከUNESCO-UNEVOC ጋር ስምምነት ፈፅሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን አላማውም በዲጅታላይዜሽን እና ቲቬት ግሪንንግ ኮሌጁን ቀዳሚና ተምሳሌት ማድረግ ሲሆን የመጀመርያ ዙር    የአቅም ግንባታ እና ጋፕ ልየታ የዩኔስኮ ዩኔቮክልዑካን በተገኙበት ተከናውኖዋል።
👍148👎1
    ዜና ሽልማት

እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላቹ!!!

ኮሌጁ በ2016 ዓ.ም አጠቃላይ ስራ አፈፃፀም ከሁሉም ኮሌጆች 1ኛ በመውጣት ከክቡር በም/ል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት የቢሮ ሀላፊ አቶ ጥራቱ በየነ የ1ኛነት ሽልማቱን የተረከበ ሲሆን በተጨማሪም የዴስክቶፕ እና የፕሪንተር ስጦታም ተበርክቶለታል።

ይህ ውጤት እንዲመጣ የለፋችሁ የኮሌጁ ማህበረሰብ በድጋሜ እንኳን ደስ አላቹ!!!

"ለላቀ አገልግሎት የመረጃ ጥራት"
👏37👍156👎3