General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
የሞዴል COC ምዘና ተጀመረ

በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 ዓ.ም  827 ተመራቂ ሰልጣኞች የሞዴል COCን በዛሬው ዕለት(08/11/16 ዓ.ም) የጀመሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት በሁሉም ሙያዎች የተግባር ምዘና ተሰጥቷል። ነገና ተነጓድያ ከደረጃ 3 በላይ ላሉ ተመራቂዎችበ On line የታገዘ የtheory ምዘና የሚቀጥል ሲሆን አላማው ለሀገር አቀፍ ምዘና ከመቅረባቸው በፊት ለዝግጅት እና እውቀትና ክህሎታቸውን ለመፈተሽ እና በዛም ላይ ተሞርክዞ የክህሎት ክፍተትን ለመሙላት መሆኑን ከኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ሰምተናል።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍104👏2
ማስታወቂያ ለተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ

የባይንደር ብር ያላስገባችሁ ሰልጣኞች ከመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ጋር በዚህ ሳምንት በቅጣት 450 ብር እንድታስገቡ እናሳስባለን። የምርቃት ቀኑ የደረሰ ስለሆነ ባይንደር ባለማግኘታችሁ ለሚፈጠረው መስተጓጎል ራሳችሁ ሀላፊነቱን እንደምትወስዱ እናሳስባለን። እንዲሁም ከዛሬ በኋላ የመፅሄት 650 ብር አንቀበልም!

የመፅሄት ብር የከፈላችሁ ሰልጣኝ ተመራቂዎች የመፅሄት ፎቶ ለመነሳት አርብ በ 12 እና ቅዳሜ በ13 ከቀኑ 5:00 ላይ እንድትገኙ። በዕለቱ መገኘት ላልቻላችሁ ሀላፊነቱን አንወስድም።
👍18👎9
ማሳሰቢያ ለተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ

የባይንደር 350 ብር የከፈላችሁ ሰልጣኞች የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ይዛችሁ ሰኞ ማለትም 22-11-2016 መታችሁ ባይንደር እንድትወስዱ::
450 የከፈላችሁ ደሞ ማክሰኞ ማለትም 23-11-2016 መታችሁ ከአሮጌው አዳራሽ በላይ ያለው የተማሪ መማክርት ቢሮ መጣችሁ ከጠዋት 3:00 ሰዓት ጀምሮ እንድትወስዱ

ማሳሰቢያ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ከባንክ አውጥታችሁ በእጃችሁ ይዛችሁ እንድት መጡ screen shot አንቀበልም
👍10
መልካም ዜና !
43,500 የመንግስት የሥራ ቅጥር ለሥራ ፈላጊዎች

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት በኢትዮጵያ የገጠርና የከተማ ቀበሌዎች ውስጥ የግብርና ናሙና ቆጠራ ያከናውናል፡

፡ስለሆነም በቀበሌው የሚሰማሩ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የሚያሟሉ መረጃ ሰብሳቢዎችን አወዳድሮ በኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል  በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት(ሌበር ማርኬት ፖርታል- E-LMIS) በመጠቀም ከመላ የሀገሪቱ ክፍሎች 43,500 ሰራተኛ ይፈለጋል።

ስለሆነም በዚህ የሥራ እድል ተጠቃሚ ለመሆን lmis.gov.et ብላችሁ በመመዝገብ አቅራቢያችሁ ባለ አንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ የባዮሜትሪክስ መረጃ በመስጠት የሰራተኛነት መለያ ቁጥር ይዛችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የሥራ መደቡ መጠሪያ፡- የስታቲስቲክስ መረጃ ሰብሳቢ 1
ብዛት፡- 43,500
ፆታ ፡- ጾታ አይለይም  
የሥራ መደቡ ዓላማ ፡-ጥራቱን የጠበቀ የገጠር/ከተማ የቤተሰብ/ባለይዞታ የግብርና መረጃ መሰብሰብ እና ወደ ሰርቨር መላክ
አሁኑኑ ሊንኩን ይጫኑና ይመዝገቡ: https://lmis.gov.et
👍93
እሁድ፡- ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ በኢንዱስትሪ ዘርፍ የአቢሲኒያ ሽልማት ዛሬ ይቀበላል!!

የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአቢሲኒያ ሽልማት እህት ኩባንያ ከሆነው አቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት ካዛንችስ በሚገኘው በኢንተርሌግዠሪ /የቀድሞው ኢንተርኮንቲኔንታል /ሆቴል በኢንዱስትሪ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓመቱ ምርጥ የመንግስት ተቋም ተብሎ ይሸለማል።

በዚህ ታላቅ የእውቅና መድረክ ላይ ኮሌጁ እንደ ተቋም ከሚሰጠው ሽልማት ባሻገር ኮሌጁ ለደረሰበት ስኬት በልዩ ሁኔታ የላቀ አበርክቶ የነበራቸው 13 አመራርና ባለሙያዎች እውቅና እንደሚቸራቸው ይጠበቃል።

ዝግጅቱ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ እንዲሁም በሀገሬ ቴሌቪዥን ደግሞ ከቀኑ 10፡00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል መባሉን ሰምተናል።

የአቢሲኒያ ሽልማት ድርጅት ዋና ዓላማ ትጉኃንን በመሸለም የምርትና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል የበኩሉን አስተዋፅአ ማድረግ ነው ተብሏል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍13👏4🏆31
እሁድ፡- ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ በአቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪው ዘርፍ  የዓመቱ ምርጥ ተሸላሚ ሆነ!!

የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአቢሲኒያ ሽልማት እህት ኩባንያ ከሆነው አቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓመቱ ምርጥ የመንግስት ተቋም ተብሎ ተሸለመ።

ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ኮሌጁ እንደ ተቋም ከተሰጠው ሽልማት ባሻገር ተቋሙ ለደረሰበት ስኬት በልዩ ሁኔታ የላቀ አበርክቶ የነበራቸው 13 አመራር አካላት እና ባለሙያዎች ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።

የሽልማት ድርጅቱ አቢሲኒያ ከፍተኛ የክብር ሽልማት ፣ አቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት እና ወርልድ ከላስ የጥራት ሽልማት የሚባሉ 3 አበየት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ኮሌጁ ያገኘው በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተበረከተውን ሀገር አቀፍ ሽልማት ነው፡፡

ድርጅቱ በግል እና በመንግስት  ተቋማት ላሉ ለምርት እና ለአገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች፣ ለአነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ ለትምህርትና ለጤና ጥበቃ ድርጅቶች፣ ለስነ ጥበብና ለስፖርት ዘርፍ፣ ለፋሽን ኢንደስትሪ፣ ለመገናኛ ብዙሀን እና ለመሳሰሉት የሙያ ዘርፎች ሰራተኞች፣ የስራ መሪዎች እና ተቋማት የዕውቅና ሽልማት ይሰጣል።   

አቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት ጥራት ያለውን ምርት እና አገልግሎት ለማኅበረሰቡ ለማቅረብ የላቀ ስራ በመስራት እና ዘመናዊ አሰራርን በመከተል በሀገራችን ሁለንተናዊ ስልጣኔ እና ዕድገት እንዲመጣ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን እና ተቋማትን ለመፍጠር ራዕይ አድርጎ የተሠረተው ድርጅት ነው፡፡

       ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍17🏆153👌2👎1
የምረቃ ቀን ለውጥ

ከተማ አስተዳደሩ የምረቃ ቀን ለውጥ ስላደረገ ውድ የ2016 ዓ.ም ተመራቂዎች ቀኑን እስክናሳውቃቹ ጋዎንና ባይንደር እንዲሁም መፅሔታቹን እየወሰዳቹ በትዕግስት እንድጠብቁን እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
😢40👎398👍8