General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
እሁድ፡- ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ በአቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪው ዘርፍ  የዓመቱ ምርጥ ተሸላሚ ሆነ!!

የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአቢሲኒያ ሽልማት እህት ኩባንያ ከሆነው አቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት በኢንዱስትሪ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የዓመቱ ምርጥ የመንግስት ተቋም ተብሎ ተሸለመ።

ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል በተካሄደው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ ኮሌጁ እንደ ተቋም ከተሰጠው ሽልማት ባሻገር ተቋሙ ለደረሰበት ስኬት በልዩ ሁኔታ የላቀ አበርክቶ የነበራቸው 13 አመራር አካላት እና ባለሙያዎች ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል።

የሽልማት ድርጅቱ አቢሲኒያ ከፍተኛ የክብር ሽልማት ፣ አቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት እና ወርልድ ከላስ የጥራት ሽልማት የሚባሉ 3 አበየት ዘርፎች ያሉት ሲሆን ኮሌጁ ያገኘው በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዘንድሮ ለ2ኛ ጊዜ የተበረከተውን ሀገር አቀፍ ሽልማት ነው፡፡

ድርጅቱ በግል እና በመንግስት  ተቋማት ላሉ ለምርት እና ለአገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች፣ ለአነስተኛ ንግድ ተቋማት፣ ለትምህርትና ለጤና ጥበቃ ድርጅቶች፣ ለስነ ጥበብና ለስፖርት ዘርፍ፣ ለፋሽን ኢንደስትሪ፣ ለመገናኛ ብዙሀን እና ለመሳሰሉት የሙያ ዘርፎች ሰራተኞች፣ የስራ መሪዎች እና ተቋማት የዕውቅና ሽልማት ይሰጣል።   

አቢሲኒያ የሽልማት ድርጅት ጥራት ያለውን ምርት እና አገልግሎት ለማኅበረሰቡ ለማቅረብ የላቀ ስራ በመስራት እና ዘመናዊ አሰራርን በመከተል በሀገራችን ሁለንተናዊ ስልጣኔ እና ዕድገት እንዲመጣ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን እና ተቋማትን ለመፍጠር ራዕይ አድርጎ የተሠረተው ድርጅት ነው፡፡

       ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍17🏆153👌2👎1
የምረቃ ቀን ለውጥ

ከተማ አስተዳደሩ የምረቃ ቀን ለውጥ ስላደረገ ውድ የ2016 ዓ.ም ተመራቂዎች ቀኑን እስክናሳውቃቹ ጋዎንና ባይንደር እንዲሁም መፅሔታቹን እየወሰዳቹ በትዕግስት እንድጠብቁን እናሳውቃለን።

ኮሌጁ
😢40👎398👍8
ጀነራል ዊንጌት በዚህ ሳምንት

በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የመጀመርያ የሆነ ኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር በኮሌጁ የኤ.አይ(AI) ክበብ አቋቋመ።

በክበብ ምስረታ ላይ የ የኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ይታገሱ ደሳለኝ ጨምሮ ሌሎች የኢኒስቲቲዩቱ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የክበቡ መመስረት በኮሌጁ የመማር ማስተማር ሂደትን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ የዲጂታላይዜሽን ስራዎችን የሚደግፍ ይሆናል ።

በተያያዘም ኮሌጁ ከUNESCO-UNEVOC ጋር ስምምነት ፈፅሞ ወደ ስራ የገባ ሲሆን አላማውም በዲጅታላይዜሽን እና ቲቬት ግሪንንግ ኮሌጁን ቀዳሚና ተምሳሌት ማድረግ ሲሆን የመጀመርያ ዙር    የአቅም ግንባታ እና ጋፕ ልየታ የዩኔስኮ ዩኔቮክልዑካን በተገኙበት ተከናውኖዋል።
👍148👎1