General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
#ጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሁለት አቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ጀመረ

ነሐሴ፤26 ቀን 2013 ዓ.ም

ጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሁለት አቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ጀምሯል፡፡

ኮሌጁ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የሚገኙ ሁለት የአቅመ ደካማ ቤቶችን ነው ማደስ የጀመረው፡፡

በአንደኛው ቤት ላይ ሶስት አባወራዎች አራት በአራት በሆነና በእንጨት በተሰራ ቆጥ 13 ቤተሰቦች አንድ ላይ ይኖራሉ፡፡

ኑሮአቸውን በደባልነት የሚመሩትና በቀን ስራ የሚተዳደሩት ወይዘሮ አይንዓለም ማሞ በሰጡት አስተያየት ቤቱ ከ20 ዓመታት በላይ ዕድሳት ሳይደረግለት መቆየቱንና ኮሌጁ ችግራቸውን ተገንዝቦ ቤቱን አፍርሶ ለመስራት ወደ ስራ በመግባቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


በቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የተገኙት የጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን
ኮሌጁ ከሚሰጠው መደበኛ ስልጠና በተጨማሪ በማህበረሰብ አገልግሎት የአካባቢውን ነዋሪ ኑሮ ለማሻሻል የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ሀገር ከሚያፈርሱ አካላት ጋር አትተባበሩ ያሉት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ቶላ ከበጎ ስራ ጎን መቆም ያስፈልጋል ሲሉ ኮሌጁ እያከናወነ ያለውን ተግባር አድንቀዋል፡፡፡

ኮሌጁ በቀጣይ ለክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ገበያ ተኮር የአጭር ጊዜ ስልጠና እንደሚሰጥ ዋና ዲኑ ጠቁመዋል፡፡

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዙሪያ በመረጃ የበለፀገ ማህበረሰብ ለመፍጠር ሁሌም እንተጋለን!
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር በጄነራል ዊንጌት ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ግንቦት 27 ቀን ፤ 2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ 14ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክንያት በማድረግ ከሚያከናውናቸው ሁነቶች አንዱ የሆነው <<ሙያና ክህሎት ለዘላቂ ልማት>>በሚል መሪ ቃል ሲያካሂድ የቆየው የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ከተማ አቀፍ ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
በማጠቃለያ ውድድሩ በክላስተር ደረጃ በተካሄደው ውድድር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የተውጣጡ ምሁራን ደግሞ በዳኝነት ተሳትፈ ውበታል።
በዚህ መሰረት #ጄኔራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ #ተግባረ-ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ንፋስ ስልክፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል ።
በማጠቃለያ ውድድሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ #አቶ መክብብ ወልደሃና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች በስልጠና ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች እና በማህበረሰቡ የሚስተዋሉ ችግሮችን በጥናት በመለየት እና ችግሮቹ በዘላቂነት እንዲፈቱ ለማድረግ ተግባራዊ ጥናትና ምርምሮች ድርሻቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
#አቶ መክብብ ወልደሃና አያይዘውም ቢሮው በተግባራዊ ጥናትና ምርምር የተገኙ ግኝቶችን በተግባር ለመለወጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።
🏆72👍2👎1