General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
11ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በክላስተር ደረጃ ተካሄደ፡፡
---------------------------------------------

መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በክላስተር ደረጃ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በጋራ በመሆን ሙያ ሀብት ነው በሚል መሪ ቃል ተካሄዷል፡፡

የኮሌጁ ዋና ዲን #አቶ_መለስ_ይመር በመድረክ የመክፈቻ ንግግር ወቅት እንዳሉት ይህ አንጋፋ ኮሌጅ ከጎኑ የአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅና የኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅን በክላስተር አደረጃጀት በመያዝ ብቁ፣ ተነሳሽነት ያለው፣ በራሱ የሚተማመን፣ ተወዳዳሪ የሆነና በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል በብዛትና በጥራት ለኢንዱስትሪው የማቅረብ ተግባር እያከናወኑ ሲሆን የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግና ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል እንዲፈጥሩ ለማስቻል በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢንተርፕራይዞች የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ቴክኖሎጂ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡