ሐሙስ:- ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
ለሴት ሰለጣኞች የተለያዩ የስልጠና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ!!
በኮሌጁ ለሚሰለጥኑ እና ከ4 ዲፓርትመንቶች ማለትም ከኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒከስ፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከሜታል ማኑፋክቸሪንግ እና ከአውቶሞቲቭ ዲፓርትመንቶች ለተውጣጡ 36 መደበኛ ሴት ሰለጣኞች በኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት ጽ/ቤት አማካኝነት ዛሬ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የተለያዩ የስልጠና መገልገያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደረገላቸው::
በዕለቱ የተሰጠው ድጋፍ የEASTRIP ፕሮጀክት የስርዓተ ፆታን ጉዳይ ለማስረፅ የሚያደርገው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ አካል እንዲሁም ሴት ሰልጣኞች ሃርድ ስኪል በሚባሉ ሙያዎች ያላቸውን ተሳትፎ ለማበረታታት የተደረገ የድጋፍ ስራ መሆኑ ተነግሯል፡፡
በድጋፍ መርሃ ግብር ላይ የEASTRIP ፕሮጀክት ሰራተኞች እና የኮሌጁ ምክትል ዲኖች ተገኝተው ስጦታውን አበርክተዋል፡፡ ሁሉም የመርሃ ግብሩ ታዳሚዎች ለሰልጣኞቹ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ቀጣይም ኮሌጁ እናንተን በማንኛውም መንገድ ለማበረታትት ዝግጁ ነው እናንተም ራሳችሁን እንደ ሌሎች ተምሳሌት የሆኑ ሴት ባለሙያዎች ራሳችሁን አብቁ ለኮሌጃችንም የወደ ፊት ሰልጣኞች አምባሳደር እንዲትሆኑ እናሳስባለን ያሉት የኮሌጁ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ሰባሁዲን ናቸው፡፡ በሌላ በኩል በኮሌጁ የEASTRIP ፕሮጀክት ጽ/ቤት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጀማል ሀሰን በበኩላቸው ሃርድ ስኪል ስልጠና ለሴት ሰልጣኝ ከባድ ሙያ ነው የሚባለውን ዘርፍ በይቻላል መንፈስ መርጣችሁ ቀጣይ ራሳችሁ የስራ ባለቤት ለመሆን እና ሀገራችሁን በዘርፉ ለማገልገል በማቀዳችሁ በርቱ ለማለት ያዘጋጀነው ነው ብለዋል፡፡
በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሰጡ የድጋፍ ዓይነቶች ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ሲሆን እነሱም ቱታ፣ ገዋን፣ የጥንቃቄ ጫማ፣ የስራ መነጽር፣ ግላፍ፣ ሄልሜት እና የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ይገኙበታል፡፡
ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ከዚህ በፊትም ለሴት ሰልጣኞች ማበረታቻ እንዲሆን ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን እና የገንዘብ ድጋፎችን እንዳደረገ አይዘነጋም፡፡
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍8❤1
ሐሙስ:- ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ ዘመናዊ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ ሊሰራ ነው!!
በኮሌጁ ዋና በር መግቢያ ላይ የሚገኘው ትንሹ የእግር ኳስ ሜዳ ጊዜውን የመጠነና ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ የእግር ኳስ ማዘውተሪያ ሊገነባ ነው::
ግንባታው ፉት ፒች ሃላ/የተ/የግ ድርጅት በተሰኘ ኩባንያ የሚፈጸም ሲሆን የስራው አጠቃላይ ወጪ 20 ሚሊዮን ብር ታቅዶለታል። ማህበረሰባዊ የግል አጋሮች ተሳትፎ /Public Private Partnership participation/ በሚለው መርህ መሰረት ኮሌጁ ከግል አልሚዎች ጋር በመተባበር ይህንን መሰረተ ልማት ለመገንባት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ስራው 4 ዘመናዊ የእግር ኳስ መለማመጃ ሜዳ እንዲሆን ታስቦ ወደ ትግበራ የተገባ ሲሆን ሙሉ ፋሲሊቲዎች የተሟሉለት ማዘውተሪያ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ይደረጋል መባሉን ሰምተናል።
ሜዳው አርቲፊሻል ሳር ማልበስን ጨምሮ ልዩ ልዩ ግብዓትን በማሟላት የተቋሙን አጠቃላይ ገጽታ የሚቀይር ስራ እንደሚሰራ ከስምምነት ሰንዱ ማረጋግጥ ችለናል።
ስራው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ በማህበረስብ አገልገሎት ዘርፍ የአካባቢው ወጣቶች በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ፣ የኮሌጁ ተቋማዊ ገጽታ ማራኪ እንዲሆን፣ የኮሌጁ የውስጥ ገቢ እንዲያድግ፣ ለተለያዩ የጤና ስፖርት ቡድኖችና ለኮሌጁ ማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቀስቃሴ እንዲያደርጉ ወዘተ ያገለግላል ያሉን በኮሌጁ የተቋማት ልማትና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ ሰባሁዲን ሁሴን ናቸው።
የመጀመሪያው ሜዳ በ2 ወራት ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ወደ ስራ ለመግባት ዛሬ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነቱ ተፈርሟል።

👍8👏4
አርብ:- ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም
የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከተቋማዊ ስነ ምግባር ትግበራ ጋር የተያያዘ ጥናት እያደረግሁ ነው አለ!!
የኮሌጁ የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት ከተቋማዊ መልካም አስተዳደር ጋር በተያያዘ ጥናት እያደረገ መሆኑን ያሳወቀው ከኮሌጁ ለተወጣጡ ባለሙዎች የጽሑፍ እና የቃለ መጠይቆችን አዘጋጅቶ ገለፃ ባቀረበበት ሰዓት ነው።
ዳይሬክቶሬቱ ከተለያየ ክፍል የተውጣጡ አጥኚ ቡድን በማቋቋም ከመልካም አስተዳደር፣ ከግብዓት አጠቃቀም፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ከስራ ግልጽነት አኳያ በተለያዩ የስራ ክፍሎች የሚታዩ ክፍተቶች እና በጎ እንቅስቃሴዎችን በጥናት ለመመለስ ነው ብሏል፡፡
የጥናት ሰነዱ ዝግጅት ቡድን የሚመራው በስራ ክፍሉ ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት አቦነህ ሲሆን የዳሰሳ ጥናቱ በተለያዩ የስራ ክፍሎች ከስራ ክፍሉ ባህርይ እና ከአፈፃፀም መመሪያ አንፃር የሚመለከት ጥያቄ ለጥናት ተሳታፊዎች በማቅረብ ነው።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍8