General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ቅዳሜ:- ሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ተካሄደ!!

በኮሌጅ ደረጃ የአሰልጣኞች፣ የሰልጣኞች እና የአንቀሳቃሾች ክህሎት ውድድር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተካሄደ።

የክህሎት ውድድር የተደረገባቸው ዲፓርንመንቶች ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሪክሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ፣ ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት፣ ሜታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ እና ውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡

በዚህ ውድድር 23 አሰልጣኞች በ14 ሙያዎች፣ 32 ሰልጣኞች በ9 ዘርፎች እና 1 አንቀሳቃሽ ደግሞ በ1 የሙያ መስክ በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ተካሂዷል፡፡

ውድድሩ የያዛቸው ሙያዎች ከሜታል ቴክኖሎጂ በመካኒክስ፣ በማሽኒንግና በዌልዲንግ፤ ከኤሌክትሪክሲቲ እና ኤሌክትሮኒክስ በቢውልዲንግ ኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽና በኢንዱስትሪያል ኤሌክትረካል ማሽን ዲራይቭ፤ ከኮንስትራክሽን በሳኒተሪ ኢንስታሌሽንና በታይሊንግ፤ ከቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት በአድቫንስድ አፓረል ፕሮዳክሽን፣ በቴክስታይል ኬሚካል ፕሮዳክሽንና በሌዘር ፕሮዳክሽን፤ ከውድ ወርክ ቴክኖሎጂ በፈርኒቸር ሚኪንግ፤ ከአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ በአውቶ ኤሌክትረካል ወርክና በአውቶ ኢንጂን ሰርቪስ እና ከኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ደግሞ በዳታ ቤዝ አድሚኒስትሬሽን እና በሃርድ ዌርና ኔትወርኪንግ ሰርቪስ ነው፡፡

ውድድሩ በትናንት ዕለት የሰልጣኞች እና የአንቀሳቃሾች ሲካሄድ ዛሬ ደግሞ የአሰልጣኞቹ ተደርጓል፡፡ ከሁሉም ዘርፎች 1ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ቀጣይ በክላስተር ደረጃ በሚደረገው ፊልሚያ ይሳተፋሉ፡፡

አሰልጣኞች የሚወዳደሩት በደረጃ 4 ሲሆን ሰልጣኞች እና አንቀሳቃሾች ደግሞ በደጃ 3 እንደሚመዘኑ ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍6
ያሬድ አበበ የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቀድሞ ሰልጣኝ የነበረ ሲሆን አባቱ አቶ አበበ አያሌው ደግሞ የኮሌጃችን ሠራተኛ ናቸው።

ስለሆነም ዛሬ በዋልታ ቴሌቪዥን 9:00 ጀምሮ በሚቀርበው ደሞ አዲስ በተሰኘ የሙዚቃ ባለ ተሰጥኦ ውድድር በ8970 - B1 ላይ ቴክስት በማድረግ እናበረታታው።

ስለተሳትፏችሁ ከወዲሁ እናመሰግናለን።
👍33👎63
ቤት በመደራጀት ለመገንባት ለተመዘገባቹ አሰልጣኞች

ነገ መክሰኞ(08/08/16) ከሰዓት 8:00 አዲሱ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን።
👍2
ማክሰኞ:- ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተሞክሮ የማስፋት መድረክ ተካሄደ!!

በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን ቢሮ ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ተሞክሮ የማስፋት መድረክ ተካሄደ፡፡

በቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ምክትል ዲን ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ በ4ቱ የድጋፍ አግባቦች ተጠቅመው ውጤታማ የሆኑ 2 ኢንተርፕራይዞች ላይ ተሞክሮ በመቀመር ሌሎች አንቀሳቃሾችም ልምዱን ተጋርተው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ዛሬ ሚያዚያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከበርካታ ኢንተርፕራይዞች ለመጡ አንቀሳቃሾች ተሞክሮውን የማስፋት ስራ ተሰርቷል፡፡

ተሞክሮ የተቀመረባቸው 2ቱ ኢንተርፕራይዞች ዮዲት፣ ሳሙኤል እና ጓደኞቻቸው በቴራዞን ምርት የተሰማሩ እና ግዛቴ፣ ብርሃኔና ጓደኞቻቸው በብረታ ብረት ስራ ላይ የሚገኙ መሆናቸው ተገልጿል፡፡ በዚህ መድረክ ላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ስር የሚገኙ 143 የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችና የክፍለ ከተማው ባለ ድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

በዚህ መድረክ ላይ የተገኙ አንቀሳቃሾችም በቀረበው ሰነድ እጅግ ተደስተው ቀጣይ እንደየ ስራ ዘርፋቸው ባህርይ በማጣጣም ይህንን ልምድ ለኢንተርፕራይዞቻቸው ለውጥ እንደሚጠቀሙበት ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የክህሎት ክፍተት አለብኝ ላሉ አንቀሳቃሾች በፍላጎታቸው መሰረት ከነገ ጀምሮ ልዩ ልዩ ስልጠና ለመስጠት እቅድ መያዙን ሰምተናል፡፡

ኮሌጁ በ3 ክፍለ ከተሞች ማለትም በአዲስ ከተማ፣ በጉለሌ እና በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተሞች ከ500 በላይ ለሆኑ ኢንተርፕራይዞች ልዩ ልዩ ድጋፎችን እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍6
ረቡዕ:- ሚያዚያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

ከተለያዩ የስራ ክፍል ለተውጣጡ ባለሙያዎች በግዢ ስርዓት ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!!

ከተለያዩ የስራ ክፍላት ለተውጣጡ ባለሙያዎች በግዢ ስርዓት ዙሪያ 5 ቀናት ቆይታ የተያዘለት ስልጠና ተሰጠ፡፡

በዚህ ስልጠና የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች፣ የወርክ ሾፕ ባለሙያዎች፣ የጨረታ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት፣ የንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት፣ የዕቅድና በጀት፣ የፋይናንስ፣ የውስጥ ኦዲት ባለሙያዎች እንዲሁም ከግዢ ሂደት ጋር ተያያዥነት ስራ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

ስልጠናው የተሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ቢሮ የግዢ ዳይሬክቶሬት ባለሙያዎች ሲሆን ስለ ግዢ ምንነት፣ የግዢ ስርዓት፣ የግዢ ሂደትና ዓይነት እንዲሁም በግዢ ዕቅድ ትግበራ ላይ የባለ ድርሻ አካላት ሚና ወዘተ በሚሉት ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የዚህ ስልጠና መሰረታዊ ዓላማ ቀጣይ በሚደረገው የግዢ ሂደት ከግዢ ፍላጎት አንስቶ ግዢው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ባለው የጊዜ ዑደት ጥራት ያለው የስልጠና ግብዓት በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳና በሚፈለገው መጠን እንዲፈፀም ባለድርሻ አካላቱ የራሳቸውን ሚና እንዲወጡ ታስቦ መዘጋጀቱን የገለፁልን በኮሌጁ የግዢ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ኤርሚያስ ግርማ ናቸው፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም አሁን ላይ ከስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች ጀምሮ በርካቶቹ አዲስ በመሆናቸው ይህ ስልጠና ለእነዚህ አካላት መሰጠቱ ቀጣይ የግዢ ስርዓቱ በታቀደለት የጊዜ ቀመር እንዲከወንና ከፍላጎት ጋር የተጣጣመ እንዲሆነ ምቹ ሂደት ይፈጥራል፡፡ ብለዋል፡፡

በኮሌጁ ከተመደበው አጠቃላይ በጀት ሶስት አራተኛው ወይም ወደ 75 ፐርሰንት የሚጠጋው ለልዩ ልዩ አገልግሎት በግዢ ስርዓት ወጪ የሚደረግ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍4