General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Forwarded from General Wingate Students Channel (E l i a z 🌙 ኤ ል ያ ዝ | Элиаз)
በጀነራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ውስጥ የገና በዓልን በማስመልከት ለ2ተኛ ዙር የደም ልገሳ ፕርግራም ተካሄደ። ከኢትዮጵያ ደም ባንክ እና ከጀኔራል ዊንጌት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሰልጣኝ ካውንስል ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀው የደም ልገሳ ፕሮግራም በኮሌጃችን ግቢ ውስጥ ያሉት የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ ሰልጣኞች እንዲሁም በግቢ ውስጥ ያሉ ማህበረሰዎች ተሳትፈውበታል ። ይህ ፕሮግራም ቀጣይነት ያለው ስለሆነ ከዚህ በኋላ ላሉት ፕሮግራሞችም ድጋፋችሁ አይለየን በአሁኑ የደም ልገሳ የተሳተፋችሁ በሙሉ እናመሰግናለን። መልካም በዓል።

የሰልጣኝ ካውንስል
14👍6
ቅዳሜ፥- ታህሳስ 27 ቀን 2016 ዓ∙ም

‹‹አትፍሩ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡›› ሉቃ 2፡11

ለኮሌጃችን የክርስትና እምነት ተከታይ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን። መልካም በዓል ይሁንላችሁ፡፡

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
70👍19😢5🙏3🏆2
🙏6026👍12👎5😢5👌3
Forwarded from @Ebiko
👍72🙏2
Forwarded from fikir
👍63
ሐሙስ:- ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም

የድርጅትንም ሆነ የሀገርን ሀብት ከሚያሳጡ አንዱና ዋናው ሙስና ነው፡፡ ከሙስና ጋር ተያይዞ የሚነሳው ደግሞ አንዱ የጥቅም ግጭት ነው፡፡

በዛሪው ሀተታችን ስለ ጥቅም ግጭት የተውሰነ እናውሳ፡፡ የጥቅም ግጭት ምንድነው?

የጥቅም ግጭት የመወሰን ስልጣን/ሃላፊነት/ ያለው ሰው የግል ጥቅም ከመንግስታዊ ስራ ወይም ኃላፊነት ጋር በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ የሚጋጭ ወይም ግጭት ሊፈጥር የሚችል ሁኔታ ነው፡፡
የጥቅም ግጭት በአንድ ተቋም ውስጥ ያለ ኃላፊነት በግል ህይዎት፣ ማህበራዊ ትስስር እና ጥቅም ላይ ባለ ፍላጎት ተፅዕኖ ዉስጥ የሚወድቅበት ሁኔታ ነው፡፡

ለጥቅም ግጭት መከሰት መንስኤው አንድ ግለሰብ ሁኔታውን እያወቀ ወይም እየተገነዘበ የመወሰን ስልጣኑን ለግል ወይም ለድርጅት ጥቅም ለመጠቀም እድል ሲኖረው ነው። ሙስና የሚፈጠረው ግለሰቡ ያገኘውን ዕድል ተጠቅሞ ቦታውን ለግል ጥቅም ሲጠቀምበት ነው።

የጥቅም ግጭት ሙስና እንዲከሰት መልካም አጋጣሚዎችን ወይም ለሙስና መከሰት ምቹ መንገድን የሚፈጥር ሲሆን፣ የጥቅም ግጭት በራሱ ሙስና አለመሆኑ ነዉ፡፡ ባጭሩ የጥቅም ግጭት ለሙስና መከሰት መንገድ ጠራጊ ነዉ፡፡

የጥቅም ግጭት አይነቶች
1. ተጨባጭ የጥቅም ግጭት /actual or real conflict of interest/፡- ተጨባጭ የጥቅም ግጭት የሚፈጠረዉ የመንግስት ባለስልጣን ኃላፊነቱን እየተወጣ ሳለ ያለ ተፅዕኖ ወይም ያለአድሎ የመወሰን ኃላፊነቱን የሚፈታተን ሁኔታ ወይም ክሰተት በተጨባጭ/በትክክል ሲያጋጥመዉ
2. . ተጋላጭ/እምቅ/ የጥቅም ግጭት/potential conflict of interest/፡- ተጋላጭ የጥቅም ግጭት በተጨባጭ ያላጋጠመ ነገር ግን ወደፊት ሊያጋጥም የሚችል እድል ያለዉ ሁኔታ ወይም ክስተት ነዉ፡፡
3. ተገማች/ተጠርጣሪ የጥቅም ግጭት /perceived conflict of interest/፡- ግንዛቤያዊ የጥቅም ግጭት የዉሳኔ አሰጣጦችን ከተጽዕኖ ነጻ መሆን የሚጋፉ ሁኔታዎች መኖራቸዉን ሃላፊነት የወለዳቸዉ ጥቅሞች ይኖራሉ የሚያስብል ጥርጣሬዎችን የሚፈጥሩ ሁኔታዎች ናቸዉ፡፡

የጥቅም ግጭት ለመከላከል የተደነገገ/የወጣ አዋጅ /ፖሊሲ/ ደንብ
1987 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት፣ አዋጅ ቁጥር 544/2007 የተባበሩት መንግስታት የፀረ ሙስና ኮንቬንሽን ማፅደቂያ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 545/2007 የአፍሪካ ህብረት የሙስና መከላከያ እና መዋጊያ ኮንቬንሽን ማፅደቂያ፣ አዋጅ ቁጥር 668/2002 የሃብት ማሳወቅና ምዝገባ አዋጅ፣ አዋጅ ቁጥር 1236/2013 የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ማሻሻያ አዋጅ፣ በ1996 ዓ.ም ወጥቶ ስራ ላይ የዋለው የወንጀል ህግ፣ የተሻሻለው የሙስና ወንጀል ህግ አዋጅ/881

የጥቅም ግጭትን የመከላከልና የማስተዳደር ዘዴዎች ምንድን ናቸው?
ግንዛቤ መፍጠር፣ ህግ ማውጣት/ማሻሻል/፣ የአደረጃጀት ለውጥ ማካሄድ፣ ተደራራቢ ስልጣኖችን ማስቀረት፣ የጥቅም ግጭት በተፈጠረባቸው ጉዳዮች ላይ ከተሳትፎ እንዲታገድ ማድረግ /restrict/) ፣ የጥቅም ግጭት ጉዳዮችን በገለልተኛ አካል እንዲታይ ማድረግ፣ መመሪያዎችን ማውጣት ወይም በሌሎች ደንቦችና መመሪያዎች ውስጥ በማካተት የጥቅም ግጭትን መቆጣጠር ናቸው፡፡ ምንጭ:- የፌደራል የስነምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን

በኮሌጁ ስነ ምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
👍93👎1
ሐሙስ፡- ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም

የ2016 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2016 በጀት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬ ጥር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የግማሽ ዓመቱን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በሁሉም ዳይሬክተሮች የራሳቸውን የስራ ክፍል አፈፃፀም ለታዳሚዎች አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ሪፖርት መረጃ መሰረት በግማሽ ዓመቱ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከማሟላት አንፃር፣ የተቋሙን መሰረተ ልማት ከማስተካከል አኳያ እና ሁሉም አካል በየዘርፉ ተነሳሽነት እና ቅንጅት ፈጥሮ ስራዎችን ከመከወን ረገድ እምርታዊ ለውጥ ያሳዬ እና ስኬታማ እንደነበር ተገልጿል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ የተገኙት ተሳታፊዎችም በቀሪው ግማሽ ዓመት ከስልጠና ሂደት፣ ከግብዓት አቅርቦት፣ ከውስጥ አሰራር፣ ከተቋማዊ ልማት እና ከማህበራዊ አግልግሎት አንፃር ቢስተካከሉ ያሏቸውን ገንቢ አስተያየቶች ሰጥተዋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍73👏1👌1
የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የተገልጋይ አስተያየት ማቅረብያ ፎርም
General Wingate Polytechnic College
User feedback form ወይም የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfwOsDFZhaRhaXxvyOx_yxGRr6yAoZKhP3c978BPM-UT1L8nA/viewform?usp=pp_url
👍62👎1
Forwarded from fikir
👍5
ቅዳሜ፡- ጥር 4 ቀን 2016 ዓ.ም

ዜና ስፓርት

የኮሌጁ እግር ኳስ ቡድን ተጋጣሚውን 3ለ1 አሸነፈ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የእግር ኳስ ቡድን ከአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አቻው ጋር ተጋጥሞ 3ለ1 በማሸነፍ የድል ባለቤት ሆነ።

በሁለተኛ ዲቪዚዮን ምድብ ሐ ላይ ተደልድለው ዛሬ ውድድራቸውን በጀነራል ዊንጌት የእግር ኳስ ሜዳ ያካሄዱት ሁለቱ ቡድኖች ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ጨዋታ ያደረጉ ሲሆን በመጨረሻም በብርቱዎቹ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የእግር ኳስ ቡድን 3ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በተያያዘ ዜና በዛሬው ዕለት በርካታ የከተማይቱ ልዩ ልዩ የእግር ኳስ ቡድኖች በተለያዩ ሜዳዎች ከአቻዎቻቸው ጋር ውድድሮችን አካሂደዋል።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍23🏆132🙏2