አርብ:- ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ስር በሚገኙ ሁለት የሙያ መስኮች ማለትም Industrial Electrical/ Electronic Control Technology እና Electrical Power System Technology በማታው /Extension/ እና በቅዳሜ እና እሁድ /Weekend/ መርሃ ግብር በ2016 በጅት ዓመት ለመሰልጠን የተመዘገባችሁ አዲስ ሰልጣኞች ከሰልጣኝ ቁጥር ማነስ ጋር በተያያዘ ሁላችሁም ወደ ቅዳሜ እና እሁድ የስልጠና መርሃ ግብር እንዲትከታተሉ በጋራ ተወስኗል፡፡ እንዲሁም Electrical Power System Technology ላይ የተመዘገባችሁ ወደ Industrial Electrical/ Electronic Control Technology ሙያ ተቀላቅላችሁ እንዲሰለጥኑ እድል ተመቻችቶላችኋል፡፡
ስለሆነም ስልጠናው ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ላይ ስለሚጀምር ሁላችሁም በእለቱ ተገኝታችሁ ስልጠናችሁን እንዲትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡
የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ስልጠና ክፍል

👍19❤4
አርብ:- ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
በሜታል ማኑፋከቸሪንግ ዲፓርትመንት ስር በሚገኙ የሙያ መስኮች ማለትም Aluminum work, Machining እና Mechanics የሙያ መስኮች በማታው /Extension/ እና በቅዳሜ እና እሁድ /Weekend/ መርሃ ግብር በ2016 በጅት ዓመት ለመሰልጠን የተመዘገባችሁ አዲስ ሰልጣኞች በሙሉ በስልጠና አሰጣጡ እና አጀማመር ዙሪያ የሚደረግ አስቸኳይ እና አጭር ውይይት ስላለ ሁላችሁም ነገ ቅዳሜ ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 3፡00 ላይ የዲፓርትመንቱ ወርክ ሾፕ በሚገኝበት አካባቢ /በተለምዶ ገርጂ በሚባለው አካባቢ/ እንዲትገኙ እናሳውቃለን፡፡
የሜታል ማኑፋከቸሪንግ ስልጠና ክፍል

👍3👏2❤1
አርብ:- ታህሳስ 19 ቀን 2016 ዓ.ም
ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ ለሚያደርጉ አሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ!!
በኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል ኢንተርፕራይዞችን ድጋፍ ለሚያደርጉ አሰልጣኞች የ5 ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡
በካይዘን እና በኢንተርፕርነር ፍልስፍና እና አተገባበር ዙሪያ ትኩረት ያደረገ ስልጠና በስራ ክፍሉ የተሰጠ ሲሆን ዓላማውም አሁን ላይ ለሚገኙ ኢንተርፕራይዞች ደረጃውን የመጠና እና ዘመኑን የዋጅ የድጋፍ ስልት እንዲተገበር ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ኮሌጁ በ4ቱ የድጋፍ አግባቦች መሰረት እንደየ ክፍተት ድጋፍ የሚደርግላቸው 510 የሚሆኑ ነባር እና አዲስ ኢንተርፕራይዞች አሉ።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

👍10🏆2❤1
Forwarded from General Wingate Polytechnic college-Official channel
ሰኞ:- ታህሳስ 22 ቀን 2016 ዓ.ም
ማስታወቂያ
በሜታል ማኑፋከቸሪንግ ዲፓርትመንት ስር በሚገኙ የሙያ መስኮች ማለትም Aluminum work, Machining እና Mechanics የሙያ መስኮች በማታው /Extension/ የስልጠና መርሃ ግብር ያመለከታችሁ አዲስ ሰልጣኞቻችን ከሰልጣኝ ቁጥር ጋር በተያያዘ ከቅዳሜ እና እሁድ /Weekend/ የስልጠና ፕሮግራም ሰልጣኞች ጋር ተቀላቅላችሁ እንድትሰለጥኑ ተወስኗል።
ስለሆነም በሁለቱም የስልጠና ፕሮግራም የተመዘገባችሁ አዲስ አመልካቾች Weekend ላይ መጥታችሁ ስልጠናችሁን እንዲትከታተሉ እየጠቆምን በተገለፁት ሙያዎች የ2016 አዲስ ሰልጣኞች ስልጠና Extension ፕሮግራም የሌለ መሆኑን እናሳውቃለን።

👍18🙏3
አርብ:- ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሄደ!!
መጪውን የገና /የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት/ በዓል ምክንያት በማድረግ ዝቅተኛ የደመወዝ መጠን ላላቸው የኮሌጁ ሰራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡
ኮሌጁ ከ400 ሺ ብር በላይ ወጪ አድርጎ ከ6ሺ ብር በታች ደመወዝ ለሚከፈላቸው 200 ሰራተኞች የዓይነት ስጦታ በማበርከት ለበዓሉ እንኳን አደረሳችሁ ብሏል፡፡
የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ በኑሮ ውድነቱ ምክንያት ጫና ላይ ላሉ የስራ ባልደረቦች የመተሳሰብ እና የመረዳዳት ባህል ለማጠናከር እና የአንዱን ችግር ሌላዉ እንዲጋራ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁ ከዚህም በፊት በነበሩ በዓላት አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ለሆኑ ሰራተኞች የበዓል መዋያ ድጎማ ሲያደርግ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

❤20👍9👏5👎1
አርብ:- ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም
የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ!!
የሁሉም ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዘርፍ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማ በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ታህሳስ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡
የግምገማ መድረኩ ዝግጅት እና አስተባባሪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ሲሆን በዕለቱ በሁሉም ኮሌጆች ያሉ የዘርፉ ምክትል ዲኖች እና የቢሮው የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ ላይ የሁሉም ኮሌጆች የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲኖች እንደ ዘርፍ የተቋሞቻቸውን የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም አቅርበው ሀሳብ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም የዘርፉን ስራ አፈፃፀም በስራ ክፍሉ ም/ዲን በአቶ ደሜ መርሻ አማካኝነት ቀርቧል፡፡

👍9❤5