General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ፡- ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም

የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ!!

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2016 ዓ.ም ላይ ለመሰልጠን ያመለከቱ አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ጀመሩ፡፡

በዚህ የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኮሌጁ ዲኖች በመድረኩ ተገኝተው ለአዳዲስ ሰልጣኞች ስለ ስልጠና አሰጣጡ ሂደት እና በስልጠና ሂደቱ ማድረግ የሚገባቸውን የስልጠና ዲሲፕሊን አስገንዝበዋል፡፡

በዚህ የስልጠና በጀት ዓመት ከ3300 በላይ መደበኛ አዳዲስ ሰልጣኞች በ3ቱም የስልጠና መርሃ ግብራት ለመሰልጠን ያመለከቱ ሲሆን ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በሁለት እጥፍ መጨመሩ ታውቋል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍3411👏4🏆3
Forwarded from Ambachew Gets Su
👍153
ሐሙስ:- ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም

ለአዳዲስ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ተሰጠ!!

በኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል ለአዳዲስ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የ3 ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ 90 የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከአራቱ የድጋፍ ማዕቀፎች መካከል ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝ እና ስለኢንተርፕርነር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በዚህ ስልጠና ላይ የተሳተፉት ከኮሌጁ ሙያዊ ድጋፍ ለማግኘት በ2016 ዓ.ም ወደ ኮሌጁ የመጡ አዲስ ኢንተርፕራይዞች ሲሆኑ በንግድ እና አገልግሎት ዘርፍ የተደራጁ መሆናቸው ታውቋል፡፡

አሁን ላይ በተለያየ ዘርፍ የተደራጁ 510 የሚሆኑ ነባር እና አዲስ ኢንተርፕራይዞች በኮለጁ ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍115🏆1
በኮሌጁ Application ሞልታችሁ የሙያ ድልድል የተደረገላችሁ Registration ለመጨረስ የሚከተሉትን ቅደም ተከተል እና ማብራርያ ተጠቀሙ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ Registration ከመጀመራችሁ በፊት (የ8ኛ ክፍል ካርድ፡የ12ኛ ክፍል ዉጤት ዶክሜንት፡የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪብት፡ጉርድ ፎቶ እና ክፍያ የፈፀማቹበትን ደረሰኝ ፎቶ አንስታችሁ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቹዋል)
1. ይህንን http://gwptc.sims.aatvetb.edu.et ድህረገፅ በብራውዘራቹ ላይ ይፃፉ ወይም ክሊክ ያድርጉ
2. በመቀጠል ከሚመጡላቹ አመራጮች ዉስጥ Registration የሚለውን ይጫኑ
3. በመቀጠል Application ID እና ምዝገባ ያካሄዳቹበትን ስልክ ቁጥር 9 ብለው በመጀመር ያስገቡ ከዛም Go ይበሉት
4. በመቀጠል የሚፈለጉትን መረጃዎች በባዶ ቦታዎቹ ይሙሉ upload የሚደረጉትን upload ያድርጉ
5. መረጃዉን ስትሞሉ Date of Commencement በሚለው ቦታ 1ኛ ክፍል የገባቹበትን አመተ ምህረት ያስገቡ
6. DOB በሚለው ቦታ ደግሞ የትውልድ አመትን ያስገቡ
7. የክፍያ ደረሰኝ የጠፋበትን ሰልጣኝ ካለ ከላይ ያያዝነውን ስም የሌለው ደረሰኝ ይጠቀም
8. በመጨረሻም statement of Applicant የሚለውን ራይት በማድረግ Apply የሚለው Active ሲሆን Apply ይበሉት ያኔ Registration አጠናቀዋል ማለት ነው:: payment የሚለው ችግር ስለተፈታ online registration መጨረስ ትችላላችሁ::
👍103👎2🏆2👌1
Registerd Trainees gwptc.xlsx
75.2 KB
ስም ዝርዝራችሁ በዚህ ኤክሴል Excel ከተጠቀሰው ሰልጣኞች በስተቀር እስካሁን ሌሎቻችሁ REGISTRATION አላካሄዳቹም ስለሆንም ከላይ ስም ዝርዝራችሁ በዚህ ኤክሴል Excel የሌለ ሰልጣኞች ከላይ የተጠቀሰውን የ REGISTRATION Procedure በመከተል በስልካችሁ ወይም INTERNET CAFE በመሄድ በፍጥነት REGISTRATION እንድታጠናቅቁ እያሳወቅን ይህንን ካልፈፀማችሁ ቦታው ለሌላ አዲስ ተመዝጋቢ ተላልፎ የሚሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
👍31👎116🙏5👌5🏆3👏1
Registration ለማድረግ ደረሰኝ አጥታችሁ እንደተቸገራችሁ እየገለፃችሁ ያላችሁ ሰልጣኞች ይህንን ደረሰኝ ተጠቀሙ
👍7
ሰኞ:- ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ስር በሚገኘው Industrial Electrical/ Electronic Control Technology የሙያ መስክ በማታው /Extension/ እና በቅዳሜ እና እሁድ /Weekend/ መርሃ ግብር በ2016 በጅት ዓመት ለመሰልጠን የተመዘገባችሁ አዲስ ሰልጣኞች በሙሉ ረቡዕ ማለትም ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ከሰዓት 12፡00 ላይ በዲፓርትመንቱ ለአስቸኳይ ጉዳይ ስልተፈለጋችሁ በእለቱ የስልጠና ክፍሉ በሚገኝበት ቦታ ህንፃ /እየታደሰ የሚገኘው ካፍተሪ ባለበት ህንፃ/ እንዲትገኙ እናሳውቃለን፡፡

የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ስልጠና ክፍል
👍197🏆1