General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ለኮሌጁ አሰልጣኞች በሙሉ
በ2016 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኞች የሙያ ምዘና /COC/ በከተማ ደረጃ እንደሚሰጥ የስራና ክህሎት ቢሮ አሳውቆናል ስለሆነም ሁሉም የኮሌጃችን አሰልጣኞች አሁን ተመድባችሁ በምታሰለጥኑበት ሙያ እንዲሁም አሁን በደረሳችሁበት የትምህርት ደረጃ ሁላችሁም ለምዘናው አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን
የምዘናው ሁኔታ
ተ.ቁ የትምህርት ደረጃ ሲኦሲ የሚመዘንበት ምርመራ
1 A Level 5 Holistic
2 B Level 4 Holistic

የምዘና ጊዜው ሲገለጽ የምናሳውቅ ይሆናል

ኮሌጁ
👍33😢31
በድጋሚ ለማሳሰብ
Ammas yaadachiisuuf
To remind again
👍8😢3
NEW Registrees of 2016.xlsx
186.7 KB
በ2016 ዓ.ም በኮሌጁ በቀን፤በማታ እና በዊኬንድ ለመሰልጠን ያመለከታችሁ ተማሪዎች የደረሳችሁን የሙያ ምደባ በዚህ ኤክሴል እየገባችሁ እንድትመለከቱ እያሳወቅን ከቀን ወደ ማታና ዊኬንድ እንዲሁም ከICT,AUTOMOTIVE & BUSINEES ፊልዶች ወደ ሌሎች ፊልዶች ቅያሪ የጠየቃችሁ በዚህ ዝርዝር ላይ ያልተቀየረ ከሆነ ወደ ጠየቃቿቸው ሙያዎች እና ፕሮግራም ገብታችሁ ስልጠና እንድትጀምሩ እያሳወቅን ወደ ICT,AUTOMOTIVE & BUSINEES ፊልዶች በቀን(regular) ቅያሪ የጠየቃችሁ ግን ቅያሬው ስለማይቻል በደረሳችሁ ሙያ ብቻ ገብታችሁ እንድትሰለጥኑ እናሳውቃለን፡፡
ከ2014 ዓ.ም በፊት ጨርሳችሁ በonline ሳይሆን በhard copy የተመዘገባችሁ የ 12ኛ እና የድግሪ ወይም ማስተርስ ጨራሾች ብቻ ስማችሁ በዚህ ዝርዝር ስላልተካተተ በ1ኛ ምርጫችሁ በወጣው ፕሮግራም መሰረት ገብታችሁ እንድትሰለጥኑ እያሳወቅን ዲፕሎማ ወይም ሌቨል ተመራቂ ሆናችሁ የተመዘገባችሁ ምዝገባችሁ ተቀባይነት ስላላገኘ መሰልጠን የማትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከዚህ ውጪ የተለየ ጥያቄ ያለው ካለ ማክሰኞ(09/04/2016ዓ.ም) ከሰዓት 8፡00 ላይ በአካል ቀርቦ ሊያናግረን የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
👍29😢8
በኮሌጁ Application ሞልታችሁ የሙያ ድልድል የተደረገላችሁ Registration ለመጨረስ የሚከተሉትን ቅደም ተከተል እና ማብራርያ ተጠቀሙ፡፡ በመጀመርያ ደረጃ Registration ከመጀመራችሁ በፊት (የ8ኛ ክፍል ካርድ፡የ12ኛ ክፍል ዉጤት ዶክሜንት፡የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪብት፡ጉርድ ፎቶ እና ክፍያ የፈፀማቹበትን ደረሰኝ ፎቶ አንስታችሁ በሶፍት ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቹዋል)
1. ይህንን http://gwptc.sims.aatvetb.edu.et ድህረገፅ በብራውዘራቹ ላይ ይፃፉ ወይም ክሊክ ያድርጉ
2. በመቀጠል ከሚመጡላቹ አመራጮች ዉስጥ Registration የሚለውን ይጫኑ
3. በመቀጠል Application ID እና ምዝገባ ያካሄዳቹበትን ስልክ ቁጥር 9 ብለው በመጀመር ያስገቡ ከዛም Go ይበሉት
4. በመቀጠል የሚፈለጉትን መረጃዎች በባዶ ቦታዎቹ ይሙሉ upload የሚደረጉትን upload ያድርጉ
5. መረጃዉን ስትሞሉ Date of Commencement በሚለው ቦታ 1ኛ ክፍል የገባቹበትን አመተ ምህረት ያስገቡ
6. DOB በሚለው ቦታ ደግሞ የትውልድ አመትን ያስገቡ
7. የክፍያ ደረሰኝ የጠፋበትን ሰልጣኝ ካለ ከላይ ያያዝነውን ስም የሌለው ደረሰኝ ይጠቀም
8. በመጨረሻም statement of Applicant የሚለውን ራይት በማድረግ Apply የሚለው Active ሲሆን Apply ይበሉት ያኔ Registration አጠናቀዋል ማለት ነው:: payment የሚለው ችግር ስለተፈታ online registration መጨረስ ትችላላችሁ::
👍141
NEW Registrees of 2016 Edited.xlsx
185.3 KB
በ2016 ዓ.ም በኮሌጁ በቀን፤በማታ እና በዊኬንድ ለመሰልጠን ያመለከታችሁ ተማሪዎች የደረሳችሁን የሙያ ምደባ በዚህ ኤክሴል እየገባችሁ እንድትመለከቱ እያሳወቅን ከቀን ወደ ማታና ዊኬንድ እንዲሁም ከICT,AUTOMOTIVE & BUSINEES ፊልዶች ወደ ሌሎች ፊልዶች ቅያሪ የጠየቃችሁ በዚህ ዝርዝር ላይ ያልተቀየረ ከሆነ ወደ ጠየቃቿቸው ሙያዎች እና ፕሮግራም ገብታችሁ ስልጠና እንድትጀምሩ እያሳወቅን ወደ ICT,AUTOMOTIVE & BUSINEES ፊልዶች በቀን(regular) ቅያሪ የጠየቃችሁ ግን ቅያሬው ስለማይቻል በደረሳችሁ ሙያ ብቻ ገብታችሁ እንድትሰለጥኑ እናሳውቃለን፡፡
ከ2014 ዓ.ም በፊት ጨርሳችሁ በonline ሳይሆን በhard copy የተመዘገባችሁ የ 12ኛ እና የድግሪ ወይም ማስተርስ ጨራሾች ብቻ ስማችሁ በዚህ ዝርዝር ስላልተካተተ በ1ኛ ምርጫችሁ በወጣው ፕሮግራም መሰረት ገብታችሁ እንድትሰለጥኑ እያሳወቅን ዲፕሎማ ወይም ሌቨል ተመራቂ ሆናችሁ የተመዘገባችሁ ምዝገባችሁ ተቀባይነት ስላላገኘ መሰልጠን የማትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ከዚህ ውጪ የተለየ ጥያቄ ያለው ካለ ማክሰኞ(09/04/2016ዓ.ም) ከሰዓት 8፡00 ላይ በአካል ቀርቦ ሊያናግረን የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
👍30
ሰኞ፡- ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ለወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡

የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም መስጠት ተጀመረ፡፡

ኮሌጁ በዚህ ዙር እንዲያሰለጥን ከተሰጠው 740 ሰልጣኞች መካከል 350ዎቹ በዛሬው ዕለት ተገኝተው መጀመራቸው ታውቋል፡፡ በስልጠናው ላይ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የመጡ ወጣቶች ስልጠናውን መቀላቀላቸው ተገልጿል፡፡

በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ተገኝተው ‹‹ወጣትና ትኩስ አምራች ኃይል እንደመሆናችሁ መጠን አሁን ላይ ለምታገኙት ተራ ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ባገኛችሁት ስልጠና ላይ ተመርኩዛችሁ ነገ ላይ የምታፈሩትን ትልቅ ሀብት ማለም ይገባችኋል›› ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡ ዲኑ አክለውም ‹‹የእኛ ኃላፊነት ስልጠናውን በአግባቡ መስጠት ነው፡፡ እናንተም እንደማንኛውም ሰልጣኝ በኮሌጁ በምታደርጉት ቆይታ የሰልጣኝ ዲሲፕሊን ሊኖራችሁ ይገባል፡፡›› ብለዋል፡፡

ወጣቶቹ በቆታቸው መሰረታዊ የህይወት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የስራ ዝግጁነት ብቃቶችን እንዲጨብጡ እና የህይወት ልምዳቸውን እንዲያጎለብቱ ታልሞ ሲሆን ከ10 ቀናት ስልጠና በኋላ ለ6 ወራት ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስራ ልምምድ ተብሏል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍131👏1
ሰኞ፡- ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም

ኮሌጁ ከቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ስልጠናን በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ኃላፊዎች ባለፈው አርብ ታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝት እና የስራ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ባሻገር የ2 ዓመት የስራ እቅድ በጋራ ማቀድ ተችሏል፡፡

ከዚህ በፊት 11 የቻይና የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የመጡ የስራ ሃላፊዎች በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝትና የስራ ውይይት መደረጉን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍26