General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ረቡዕ፦ ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም

የስልጠና ማስታወቂያ

ኮሌጃችን ከመደበኛው የስልጠና ፕሮግራም ባሻገር ለአጫጭር ስልጠና ፈላጊዎች በአዲስ መልኩ አማራጭ ይዞ መጥቷል።

ይኸውም በ10 የስልጠና ዘርፎች ስር በሚገኙ 53 ሙያዎች አጫጭር ስልጠናዎችን ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።

ስለሆነም በአጭር ቀናት ሰልጥነው ረጅሙን የህይወት ጉዞ የሚሰሩበት ሙያ ይቅሰሙ።

በዚህ ስልጠና ለመማር ፍቃደኝነት ብቻ እንጂ የመግቢያ ነጥብ፣ የትምህርት ደረጃ እና መሰል መስፈርቶች አያግድዎትም።

ሁል ጊዜ ምዝገባ፣ ሁል ጊዜ ስልጠና አለ።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍27
ሐሙስ:- ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም 

         ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ስልጠና ተሰጠ!!  

በኮሌጅ የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኩል ለኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከህዳር 18 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የ3 ቀናት ስልጠና ተሰጠ፡፡  

ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 9 ወረዳዎች ለተውጣጡ 140 የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የቢዝነስ አመራር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን ይዘቱም ስለንግድ ፈጠራ አመራር ክሂሎት፣ በሚሰጡት አገልግሎት ወይም በሚያቀርቡት ምርት ላይ የሚጠበቅባቸው የውድድር ብቃት፣ ስለ ኢንተርፕርነር፣ ስለ ቴክኖሎጂ ፅንሰ ሀሳብ እና መሰል ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ቀርቧል።

የስልጠና ፍላጎት ጥያቄ የመጣው ከራሳቸው ከአንቀሳቃሾቹ  መሆኑም ተገልጿል፡፡

የቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ በኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ አገልግሎት ዘርፍ የጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማትን ችግር ለይቶ እና ፍላጎታቸውን መሰረት አድርጎ በአራቱ የድጋፍ አግባቦች ማለትም የቴክኒካል ክህሎት፣ የስራ ፈጣሪነት ክህሎት፣ የምርጥ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና የጥራትና ምርታማነት ማሻሻያ /ካይዘን/ አቅም ግንባታ አማካኝነት እግዛ ያደርጋል፡፡

አሁን ላይ 510 የሚሆኑ ነባር እና አዲስ ኢንተርፕራይዞች  በኮለጁ ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

           ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍20
ቅዳሜ:- ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ∙ም

2ሺ የሚደርሱ አዳዲስ ሰልጣኞች በ2 ሳምንት ተመዘገቡ!!

ኮሌጁ የ2016 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን ከህዳር 10 ቀን 2016 ዓ∙ም ጀምሮ በበየነ መረብ /online/ እና በሀርድ ኮፒ ለ2 ሳምንታት የመዘገበ ሲሆን በዚህም 2 ሺ የሚደርሱ አዳዲስ ሰልጣኞችን መመዝገቡ ታውቋል።

ኮሌጁ አሁን ላይ ባለው ዘርፈ ብዙ ፋሲሊቲዎችን ማሟላቱ እና ለስልጠና ጥራቱ ትኩረት መስጠቱ ተመራጭነቱን ይበልጥ ስላሰፋው ከፍተኛ ተመዝጋቢ ካላቸው የመዲናችን ቴክኒክና ሙያ ተቋማት ውስጥ የመጀመሪያውን ረድፍ ይዟል።

ውድ ተመዝጋቢዎች! በመሉ እምነት እኛን ተማምናችሁ መርጣችሁን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን።

የአሁኑ ቅዳሜና እሁድ በበየነ መረብ መመዝገቢያ ሰንደቁ ላይ ምዝገባ ለማከናወን ሞክራችሁ ሲስተሙ እንዳስቸገራችሁ የገለፃችሁልን ብዙዎች ናችሁ። እውነታችሁን ነው የቀረቡ መረጃዎችን አስተካክለን የተጨማሪ ዙር ምዝገባ ሰኞ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በዲጂታል ስርዓቱ ስለምናቀጥል በትዕግስት እንዲትጠባበቁን እንገልፃለን።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምዝገባችሁን ያካሄዳችሁ አዳዲስ ሰልጣኞች የስልጠና ገለፃ /Training orentation/ ስላለ ሰኞ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ከጧቱ 2:30 በኮሌጁ እንድትገኙ እናሳውቃለን።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍37
ጀነራል_ዊንጌት_ፖለተኮ_በ2016_አመልክተው_ሙያ_የተደለደሉ.xlsx
119.3 KB
በ 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ለመሰልጠን በቀን በማታ እና በዊኬንድ ለመሰልጠን የተመዘገባችሁ ሰልጣኞች የተመደባቹባቸውን ሙያዎች የሚከተለውን ኤክሴል ከፍታቹ ተመለከቱ።
👍40
ለonline registration ይሄንን ደረሰኝ ተጠቀሙ
👍9
Forwarded from admasu Ye Abiye Lij
👍13👎1
ሰኞ፡- ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ለአዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ!!

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2016 ዓ.ም ስልጠና ለመከታተል ላመለከቱ አዳዲስ ሰልጣኞች የግንዛቤ መስጫ መድረክ ዛሬ ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም ተካሄደ፡፡

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ በበጀት ዓመቱ በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ለመከታተል ያመለከቱ አዳዲስ ሰልጣኞች በዕለቱ ተገኝተዋል፡፡

በወቅቱ የኮሌጁ ዲኖች እና የስልጠና ዘርፍ ተጠሪዎች በቦታው ተገኝተው የስልጠናውን ሂደት በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ የስልጠና ሂደት ገለፃ ላይ የሁሉም ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ተገኝተው ስለ ዲፓርትመንታቸው ምንነት፣ በዲፓርትመንቱ ስር ስለሚሰጡ የስልጠና መስኮች፣ እያንዳንዳቸው የስልጠና መስኮች በገበያው ላይ ያለው የስራ ፍላጎት፣ ስልጠናው የሚፈጀው የጊዜ ቆይታ እና መዳረሻቸው የት እንደሆነ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

አንዳንድ ዲፓርትመንቶች ደግሞ በሰልጣኞች የተሰሩ ምርቶችን መድረክ ላይ በማሳየት አዲስ ተመዝጋቢ ሰልጣኞች የስልጠና ክፍሉን እንዲቀላቀሉ የማስተዋወቅ እና የመቀስቀስ ስራ አከናውነዋል፡፡

አሁን ላይ አዳዲስ ሰልጣኞች ሌላ አማራጭ ፈልገው ዲፓርትመንት መቀየር ቢሹ መስተናገድ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ነገር ግን Accounting & finance, Automotive elecetric & electronics, Automotive mechanics, Biulding electrical installation /BEI/, Fashion Designing, Hard ware & Networking Service, Marketing & Sales management, Secretarial & office administration እና web design & data base administration ባሉ 9 የስልጠና መስኮች ላይ ከስልጠና ግብዓት እና ከአሰልጣኝ መጠን አንፃር ከበቂ በላይ ስልተመዘገበባቸው ለመደበኛው የቀን ተማሪዎች አማራጭ ለመቀየር የማይስተናገድባቸው እንደሆኑ ተገልጿል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍29😢3