General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች መመዝገቢያ መመሪያ ቅደምተከተል
1. በመጀመሪያ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በ ብሮዘራችሁ ሰርች ማደረጊያ ላይ መፃፍ (gwptc.sims.aatvetb.edu.et)
2.በመቀጠል በስተግራ ያለውን 3 ነጥብ ይጫኑ
3. በመቀጠል (registration guideline) የሚለውን በመጫን መመሪያውን በሚገባ ማንበብ
4. Application form የሚለውን መምረጥ
5.የተጠየቁትን መረጃዎች በሙሉ በጥንቃቄ እና ሳይዘሉ መሙላት። ስልክ የሚጠይቅበት ቦታ ላይ 09 ያለማለት ይልቅ 9 ብሎ መጀመር
6. በመጨረሻም Apply የሚለውን በመጫን ፎርሙን መጨረስ
8. ከዚያም ሲስተሙ admission ID በ 8465 SMS ይልካል 09 ካላችሁ ግን አይልክም።
9. በ8465 SMS የተላከላችሁን አጭር የፅሑፍ መልዕክት እያሳያችሁ በኮሌጁ registrar በአካል በመገኘት ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለ የትምህርት ማስረጃችሁን እንዲሁም ፎቶግራፍ በhard copy በመያዝ ቀሪ የምዝገባ ሂደታችሁን ታጠናቅቃላችሁ።

ማሳሰብያ:- ከላይ የተጠቀሱትን ቅደም ተከተል በመከተል መመዝገብ የማይችል ተማሪ በአካል ወደ ኮሌጁ ቢመጣ በኮሌጁ ባሉ መዝጋቢዎች ድጋፍ ተደርጎለት መመዝገብ ይችላል
👍15
Forwarded from fikir
👍13
አርብ፡- ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የፀረ ሙስና ቀን በኮሌጁ ተከበረ!!

ዓለም አቀፍ የፀረ ሙስና ቀንን ምክኒያት በማድረግ እንደ ተቋም ዛሬ ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ የፀረ ሙስና ቀን ተከበረ፡፡

በዓለም ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ19ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የፀረ ሙስና ቀን በኮሌጁ የስነምግባር እና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት " ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በህብረት እንታገል" በሚል መሪ ቃል የኮሌጁ ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሯል።

በዓሉ በፀረ ሙስና ትግሉ እየተሰሩ ያሉ ተግባራትን ለማስቀጠል፣ የትውልድ ስነ ምግባር ግንባታን ለማጠናከር፣ የፀረ ሙስና ትግሉን ህዝባዊ መሰረት በማስያዝ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ታቅዶ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ሙስና በስነ ምግባር ውድቀት፣ በቢሮክራሲ መብዛት፣ በተጠያቂነት መጓደል፣ በዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማነስ፣ ባልተማከለ የአሰራር ስርዓት እና መሰል መንስኤዎች የሚከሰት ሲሆን አፈፃፀሙ በጊዜ ሂደት እየሰፋ እና እየረቀቀ በመምጣቱ የሀገርን ሀብት ከዚህ እኩይ ብዝበዛ ለመታደግ መንግስት፣ ቤተሰብ፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ሚዲያዎች፣ የትምህርት ተቋማት እና ቤተ እምነቶች ከፍተኛ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡

በተያያዘ ዜና እንደ ሀገር ለ18ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች በዓል በተመሳሳይ አብሮ ተከብሯል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍14
በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች መመዝገቢያ መመሪያ ቅደምተከተል
1. በመጀመሪያ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በ ብሮዘራችሁ ሰርች ማደረጊያ ላይ መፃፍ (gwptc.sims.aatvetb.edu.et)
2.በመቀጠል በስተግራ ያለውን 3 ነጥብ ይጫኑ
3. በመቀጠል (registration guideline) የሚለውን በመጫን መመሪያውን በሚገባ ማንበብ
4. Application form የሚለውን መምረጥ
5.የተጠየቁትን መረጃዎች በሙሉ በጥንቃቄ እና ሳይዘሉ መሙላት። ስልክ የሚጠይቅበት ቦታ ላይ 09 ያለማለት ይልቅ 9 ብሎ መጀመር
6. በመጨረሻም Apply የሚለውን በመጫን ፎርሙን መጨረስ
8. ከዚያም ሲስተሙ admission ID በ 8465 SMS ይልካል 09 ካላችሁ ግን አይልክም።
9. በ8465 SMS የተላከላችሁን አጭር የፅሑፍ መልዕክት እያሳያችሁ በኮሌጁ registrar በአካል በመገኘት ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለ የትምህርት ማስረጃችሁን እንዲሁም ፎቶግራፍ በhard copy በመያዝ ቀሪ የምዝገባ ሂደታችሁን ታጠናቅቃላችሁ።

ማሳሰብያ:- ከላይ የተጠቀሱትን ቅደም ተከተል በመከተል መመዝገብ የማይችል ተማሪ በአካል ወደ ኮሌጁ ቢመጣ በኮሌጁ ባሉ መዝጋቢዎች ድጋፍ ተደርጎለት መመዝገብ ይችላል
👍10
እሁድ:- ህዳር 16 ቀን 2016 ዓ∙ም

ቢሮው በአዲስ ስያሜና በአዲስ አደረጃጀት መቀየሩ ተገለፀ!!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በሚል ስያሜ እንደ አዲስ መደራጀቱ ተገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ እንደራሲዎች ምክር ቤት  ባካሄደው ሦስተኛ የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ ከስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራ እድል ፈጠራ እና የስራ ስምሪት ዘርፍን አካቶ በመያዝ የሥራ እና ክህሎት ቢሮ በሚል ስያሜ እንዲደራጅ የቀረበለትን አዋጅ ማፅደቁ ተሰምቷል።

ቢሮውንም እንዲመሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ የተመደቡ ሲሆን በሌላ በኩል ቢሮውን ሲመሩ የነበሩት ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት የልማት ድርጅቶች ቁጥጥር ባለሥልጣን ኃላፊ ሆነው መሾማቸው ታውቋል። 

አዲሱ ቢሮ የሰለጠነ የሰው ሀብት ከማቅረብ ባሻገር የስራ ዕድል ፈጠራ እና የስራ ስምሪት ኃላፊነት ተደርቦበታል።

         "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍11
በጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች መመዝገቢያ መመሪያ ቅደምተከተል
1. በመጀመሪያ የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በ ብሮዘራችሁ ሰርች ማደረጊያ ላይ መፃፍ (gwptc.sims.aatvetb.edu.et)
2.በመቀጠል በስተግራ ያለውን 3 ነጥብ ይጫኑ
3. በመቀጠል (registration guideline) የሚለውን በመጫን መመሪያውን በሚገባ ማንበብ
4. Application form የሚለውን መምረጥ
5.የተጠየቁትን መረጃዎች በሙሉ በጥንቃቄ እና ሳይዘሉ መሙላት። ስልክ የሚጠይቅበት ቦታ ላይ 09 ያለማለት ይልቅ 9 ብሎ መጀመር
6. በመጨረሻም Apply የሚለውን በመጫን ፎርሙን መጨረስ
8. ከዚያም ሲስተሙ admission ID በ 8465 SMS ይልካል 09 ካላችሁ ግን አይልክም።
9. በ8465 SMS የተላከላችሁን አጭር የፅሑፍ መልዕክት እያሳያችሁ በኮሌጁ registrar በአካል በመገኘት ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለ የትምህርት ማስረጃችሁን እንዲሁም ፎቶግራፍ በhard copy በመያዝ ቀሪ የምዝገባ ሂደታችሁን ታጠናቅቃላችሁ።

ማሳሰብያ:- ከላይ የተጠቀሱትን ቅደም ተከተል በመከተል መመዝገብ የማይችል ተማሪ በአካል ወደ ኮሌጁ ቢመጣ በኮሌጁ ባሉ መዝጋቢዎች ድጋፍ ተደርጎለት መመዝገብ ይችላል
👍8
ሰኞ፡- ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም

የአዳዲስ ሰልጣኞች ምዝገባ ከተጀመረ አንድ ሳምንት አስቆጠረ!!

ኮሌጁ የ2016 ዓ.ም አዳዲስ ሰልጣኞችን በበየነ መረብ /online/ መመዝገብ የጀመረው የዛሬ ሳምንት ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ∙ም ነው።

እስከ አሁን በተደረገው የወረቀት አልባ ኦን ላይን ምዝገባ በ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍልን ያጠናቀቁና ከዚያ በፊት ጨርሰው የተቀመጠውን የቅበላ መስፈርት ያሟሉ አዳዲስ ሰልጣኞች ምዝገባቸውን አከናውነዋል። በምዝገባ ሂደቱም የኔትወርክ መጨናነቅና የተመዝጋቢዎች ወረፋ እንዳይኖር ከሬጅስትራል ሰራተኞች ባሻገር በርካታ የቢሮ ሰራተኞች በምዝገባ ሂደቱ ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡ እስካሁንም ከ1400 በላይ አዳዲስ ሰልጣኞች ምዝገባቸውን አጠናቀዋል፡፡

ያልተመዘገባችሁ ውድ አመልካቾች ባላችሁበት ሆናችሁ በሞባይል ወይም ደግሞ በአቅራቢያችሁ ባለ ኢንተርኔት ቤት በመሄድ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ሂደቱም በሚከተለው መልኩ ነው፡፡

ይኸውም፡- ብራውዘራችሁ ላይ gwptc.sims.aatvetb.edu.et የሚለውን ሰርች ማድረግ፣ በስተግራ ያለውን 3 ነጥብ መጫን፣ በመቀጠልም registration guideline የሚለውን በመጫን መመሪያውን ማንበብ፣ Application form የሚለውን መምረጥ፣ የተጠየቁትን መረጃዎች በሙሉ መሙላት። ስልክ የሚጠይቅበት ቦታ ላይ 09 ሳይሆን 9 ብሎ መጀመር፣ ከዚያም Apply የሚለውን በመጫን፣ በመጨረሻም ሲስተሙ admission ID በ 8465 SMS ይልካል።
- በ8465 SMS የተላከላችሁን አጭር የፅሑፍ መልዕክት እያሳያችሁ በኮሌጁ registrar በአካል በመገኘት ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለ አጠቃላይ ዋናው የትምህርት ማስረጃችሁን እና የማይመለስ ኮፒ እንዲሁም 2 ጉርድ ፎቶ በመያዝ ቀሪ የምዝገባ ሂደታችሁን ማጠናቀቅ ይኖርባችኋል፤ ተብላችኋል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍23😢3
ረቡዕ፡- ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም

ሰዓቱ እየቆጠረ ነው!!

ኮሌጁ አዳዲስ ሰልጣኞችን መመዝገብ ከጀመረ እንሆ ሁለተኛ ሳምንት ተቆጠረ፡፡ በዚህ ምዝገባ ላይ ኮሌጁ ካለው የስልጠና ግብዓት መጠን እና እንዲቀበል ከተጣለበት ኮታ አንፃር አሁን ላይ 50 ፐርሰንት ያህሉ ምዝገባቸውን አጠናቋል፡፡

ውድ ምዝገባችሁን ያጠናቀቃችሁ አዳዲስ ሰልጣኞች!!

ኮሌጃችን በISO 9001:2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ የሆነ ብቸኛ ተቋም መሆኑ፣ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመሆን አቅዶ እየተጋ መገኘቱ፣ በኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን ብዙ ስራዎች እየተከወኑ መገኘቱ እና የተቋሙን አጠቃላይ ስነ ምህዳር ውብ እና ማራኪ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አይታችሁ እኛን መርጣችሁ በመምጣታችሁ እናመሰግናለን።

እኛን መርጣችሁ ስትመጡ በምክኒያት እንደሆነ እንረዳለን፣ አስር ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከሃምሳ ጊዜ በላይ ለክታችሁ እኛ ጋር ቆርጣችሁ እንደመጣችሁ እናምናለን፡፡ የነገውን ትውልድ የመጠነ እና ዓለም የደረሰበትን የስልጠና ስማርት ቴክኖሎጂ ግብዓት ለመጠቀም ለሁሉም ዲፓርትመንቶች ኢንተራክቲቭ ቦርድ የተገጠመላቸው የሙያ ዘርፎችን መርጣችሁ በመመዝገባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የእያንዳንዱ ዲፓርትመንት በከፍተኛ መዋለ ንዋይ የተገዙ ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ ግብዓትን ከብቁ አሰልጣኞች ጋር አሟልቶ ይጠብቃችኋል፡፡

ውድ እስከ አሁን ምዝገባ ያላደረጋችሁ ደንበኞቻችን!!

ለምዝገባ እንደርሳለን በማለት የተዘናጋችሁ ወይም ጀነራል ዊንጌት ልመዝገብ አልመዝገብ በማለት ያመነታችሁ ቤተሰቦቻችን ሰዓቱ እየቆጠረ ነው፡፡ ዓላማችን እናንተን ብቁ ባለሙያ ማድረግ ስለሆነ ቦታ ሳይሞላ እና የምዝገባ ጊዜ ሳይጠናቀቅ በፈለጉት የሙያ ዘርፍ እና በሚመችዎት የስልጠና መርሃ ግብር ማለትም በቀን፣ በማታ፣ እና በቅዳሜ እና እሁድ ተመዝግበው እንዲሰለጥኑ እንመክራለን፡፡ የሚከተለውን ማስፈንጠርያ ተጭነው ይመዝገቡ=- http://gwptc.sims.aatvetb.edu.et

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍18👎1😢1