General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሰኞ፡- ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

ከተለያዩ የቻይና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ ልዑካን ቡደን አባላት ኮሌጁን ጎበኙ!!

ከ13 የቻይና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች የተውጣጡ ዲኖች እና የዘርፉ ባለሙያዎች የተካቱበት ከ40 በላይ አባላት ያሉት ልዑካን ቡደን ዛሬ ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ኮሌጁን ጎበኙ፡፡

ይህ በቻይና አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ልምድ ልውውጥ አካል በሆነው መርሃ ግብር ላይ በኮሌጁ ተገኝተው ምልከታ ያደረጉት የተቋማቱ መሪዎች የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማጠናከር ባሻገር ቀጣይ በሰው ሀብት ልማት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ስልጠና እና በተቋማዊ አመራር ዙሪያ ከኮሌጁ ጋር በትብብር ለመስራት ታቅዶ የተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ የማሰልጠኛ ወርክ ሾፖችን፣ የተቋሙን አጠቃላይ ስነ ምህዳር፣ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ምልከታ አደርገዋል፡፡

ለቻይና አሁናዊ ዕድገት የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትልቅ ሚና ስለነበረው ተቋማዊ ትብብሩ ለእኛም እንደ ሀገር በኢኮኖሚ እድገትና በዜጎች የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ በሚያበረክት መልኩ ትብብር ለማድረግ ታቅዶ እንደተካሄደ ተነግሯል፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና በመሰረተ ልማት፣ በግብርናው መስክ፣ በቴክኖሎጂዎች ማሸጋገር እና በተለያዩ ስልጠናዎች በጋራ ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍10
በስልጠና ላይ ለሚኖር ቅሬታ እንዲሁም ጥቆማ ካለ @Gw2016bot ማሳወቅ ትችላላችሁ።
👍61
ማክሰኞ፡- ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

የአሰልጣኞች ኢንዱስትሪ አታችመንት ቆይታ ግምገማ ተደረገ!!

ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ሄደው የነበሩ አሰልጣኞች የአታችመንት ቆይታ ግምገማ ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2016 ዓ.ም በጋራላይ ሆቴል ተደረገ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ የEASTRIP ፕሮጀክት ጽ/ቤት ሰራተኞች፣ አታችመንት የተወጣባቸው ኢንዱስትሪዎች ተወካዮች እና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።

የአሰልጣኞች ኢንዱስትሪ አታችመንት ዓላማ አሰልጣኞች በጽንሰ ሀሳብ የሚያውቁትን ሙያ በኢንዱስትሪዎች ካዩት የስራ ባህል፣ ልምድ፣ ከሚጠቀሙት ቴክኖሎጂ እና ከአዳዲስ አስራር ስርዓት አንጻር ሰልጣኞቻቸውን ከገሀዱ የስራ ዓለም ጋር በተግባር አገናኝተው ስልጠና እንዲሰጡ ታቅዶ መሆኑን የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ተናግረዋል።

በዚህ የኢንዱስትሪ አታችመንት ላይ ከ11 ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ 20 አሰልጣኞች በተለያየ ምርት እና አገልግሎት በሚሰጡ 12 ኢንዱስትሪዎች ለአንድ ወር ያህል ቆይታ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ካፒታል ሆቴል፣ ሆለታ አግሪካልችር ሪሰርች ኢንስቲተዩት፣ አዲስ አበባ ከተማ አወቶቢስ አገልግሎት ድርጅት፣ አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን፣ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት፣ ሳልማ ፈርኒቸር፣ ዎሲ ጋርመንት፣ ሲምቦል ቴክኖሎጂ፣ ጽጌ በየነ ሌዘር ፕሮዳክት ፋብሪካ፣ ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፐ፣ LTF ኮንሱልቲንግ እና ኤሊያና ሆቴል አሰልጣኞቹ በኢንዱስትሪ አታችመንት የቆየባቸው ድርጅቶች መሆኑ ተገልጿል። በመርሃ ግብሩ ላይ አሰልጣኞቹ በእያንዳንዱ ኢንዱስትሪ የነበራቸውን አጠቃላይ ቆይታ የሚያሳይ ሪፓርት አቅርበዋል።

የአታችመንቱ መርሃ ግብር የአሰልጣኞችን አቅም ከማጎልበት አንጻር ከሚከወኑ ተግባራት አንዱ ሲሆን አሰልጣኞች የስራ ገበያውን ስርዓት በአካል ልምድ ቀስመው እና ስልጠናውን ከነባራዊ የኢንዱስትሪ ፍላጎት ጋር አዛምደው እንዲተገብሩ ቀጣይም ከኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ይህንን ስራ በስፋት ለማከናወን ዕቅድ መያዙን የኮሌጁ የተቋማት ልማት እና አስተዳደር ጉዳዮች ምክትል ዲን ቢሮ አሳውቋል።

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍9
Forwarded from Omry 💛
👍1
በስልጠና ላይ ለሚኖር ቅሬታ እንዲሁም ጥቆማ ካለ @Gw2016bot ማሳወቅ ትችላላችሁ።
ረቡዕ- ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

የአሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ!!

በማሰልጠን ስነ ዘዴ ላይ ትኩረት ያደረገ የአሰልጣኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ዛሬ ጥቅምት 14 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ተካሄደ። 

መርሃ ግብሩ ሁሉንም አሰልጣኞች ወደ ተቀራራቢ የማሰልጠን ስነ ዘዴ ብቃት ለማምጣት ታቅዶ የተዘጋጀ ሲሆን ዘመኑ የደረሰበት የስልጠና ምጥቀትን ተረድቶ እና በዚህ የውድድር ዓለም የደንበኞችን ፍላጎት በውል ተገንዝቦ የሚሰራ ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት ነው።

ለመድረኩ ዝግጅት ገፊ ምክኒያት የሆነው በሱፐርቪዥን ቡድን የተደረገ የክፍል ውስጥ ምልክታ፣ በተለያየ ጊዜ በተቋሙ አመራር የተደረገ ቅኝት እና ሰልጣኞች በተለያየ መንገድ የሚሰጡት አስተያየት ተዳምሮ የኮሌጁን ራዕይ የሚያሳካ እና ተልዕኮውን የሚያፋጥን አፈጻጸም እንዲተገበር ለማድረግ ታስቦ መሆኑን የተናገሩት የኮሌጁ የስልጠና እና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን አቶ አድማሱ በቀለ ናቸው። ም/ዲኑ አክለውም ነባር ሰልጣኞች ስልጠና መጀመራቸው እና አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅት መጠናቅቁን ተከትሎ ከጅምሩ መካሄዱ የበጀት ዓመቱን ስልጠና ውጤታማ ለማድረግ ይረዳል፤ ብለዋል።          

የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ ከተግባራዊው የማሰልጠን ስነ ዘዴው ባሻገር ማይንድ ሴት /የልቦና ውቅር/ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።     

"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍13
ቅዳሜ ፡- ጥቅምት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ እየተደረገ ነው!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ አንድ ዓመት እቅድ ውይይት በቢሾፍቱ ከተማ ፕራሚድ ሆቴል እየተደረገ ነው፡፡

በዚህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና እቅድ ውይይት  ላይ የኮሌጁ ዲኖች፣ የአዲስ አበባ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ተወካይ፣ የክላስተር ኮሌጆች ዲኖች፣ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት እና ከተለያዩ ዲፓርትመንት የተውጣጡ አሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡

አሁን ላይ በኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው የእንኳን ደህና መጣችሁ መግቢያ ንግግር ከተደረገ በኋላ የፕሮጀክቱን የስራ እንቅስቃሴ የሚያሳይ ገለጻ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የፕሮጀክት ሞኒተሪንግ እና ኢቫሊዎሽን ኤክስፐርት በሆኑት አቶ ለሜሳ ደሜ አማካኝነት እየቀረበ ይገኛል፡፡  

ውድ የቻናላችን ተከታታዮቻች ሌሎች ቆይታዎችን እየተከታተልን ዝርዝር ዘገባዎችን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ከቢሾፍቱ
👍6