General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
Forwarded from fikir
👍4
የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የተገልጋይ አስተያየት ማቅረብያ ፎርም
General Wingate Polytechnic College
User feedback form ወይም የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfwOsDFZhaRhaXxvyOx_yxGRr6yAoZKhP3c978BPM-UT1L8nA/viewform?usp=pp_url
👍2
ቅዳሜ፡- ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም  

                      የዲፓርትመንቶች   ቅኝት

                   ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት

በዛሬው የዲፓርትመንቶች ቅኝት ቀዳሚ እይታችን ያደረግነው የኮንስትራክሽን ስልጠና ከፍልን ነው። ኮሌጁ በሀገር አቀፍ ደረጃ በጣም ጥቂት እና በከፍተኛ ውድድር ተመርጠው የሚገቡ የ2ኛ ደረጃ አዳሪ ተማሪዎችን መቀበል አቁሞ ወደ ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ሲሸጋገር አሀዱ ብሎ የጀመረው በዚህ የስልጠና ዘርፍ ነው።

የዛሬ 43 ዓመት 1973 ዓ.ም የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ሲጀምር የኮነስትራክሽን እና ሙያ ት/ቤት በሚል ስያሜ ሲሆን ስልጠና ክፍሉ ቀዳሚውን ቦታ መያዝ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ባለቤትነትን ድርሻ ይወስዳል።  በወቅቱ በሶቬት ህብረት /ራሻያ/ የቴክኒክ ተራዲኦ ድርጅት አማካኝነት በመታገዝ እንደ ሀገር ብቃታቸው የተረጋገጠ እንቁ ባለሙያዎችን በማፍራት አኩሪ ገድሉን አጽፏል።

በጊዜው እንደ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ሲሰጡ የነበሩ ሙያዎች 6 ሲሆኑ እነሱም ኤሌክትሪክሲቲ፣ ኤሌክትሮ ጋዝ ዌልዲንግ፣ ፕላምቢንግ፣ ፔንቲንግ ፕላስተሪንግ፣ ውድ ወርክ እና ሬንፎርስመንት ናቸው። እነዚህን ስልጠናዎች ውጤታማ ለማድረግ ኢትዮጵያዊያን እና ከሩሲያ የመጡ መምህራን በትጋት ሰርተዋል።

ውሎ እየታደር ዘመን እየተቆጠረ አዲስ የትምህርት ፖሊሲ ሽግግር መፈጠሩን ተከተሎ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ተቋሙ ከኮንስትራክሽን እና ሙያ ት/ቤት ወደ ኮንስትራክሽን እና ሙያ ኮሌጅ ስያሜ ሲቀየር ስልጠና ክፍሉ በቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን፣ በሮድ ኮንስትራክሽን፣ በዲራፍቲንግ ቴክኖሎጂ፣ በሰርቬይንግ ቴክኖሎጂ እና በውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ስልጠና ሲስጥ ቆይቷል።

የስልጠና ሙያ ፍላጎት እየረቀቀ እና እያደገ መምጣቱን ተከተሎ በስሩ የነበሩ ልዩ ልዩ ሙያዎች በተለያየ ጊዜ ራሳቸውን ችለው ዋና የስልጠና ክፍል በመሆን ሲወጡ አሁን ላይ በቢውልዲንግ እና ሮድ ኮንስትራክሽን ላይ ባሉ ልዩ ልዩ ሙያዎች እያሰለጠነ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ ስትራክቸራል ኮንስትራክሽን ወርክ፣ ፊኒሽንግ ኮንስትራክሽን ወርክ፣ ፐላምቢንግ ኢንስታሌሽን እና ሮድ ኮንስትራክሽን እና ሜንቴናንስ ስልጠና ክፍሉ እየሰጣቸው ያሉ ሙያዎች ናቸው።


ዲፓርትመንቱ አሁን ላይ   55 ወንድ እና 7 እንስት በአጠቃላይ 62 አሰልጣኞች ሲኖሩት 8 ኤ ደረጃ ኢንስትራከተር፣   48 ቢ ደረጃ አሰልጣኝ፣ 2 ሲ ደረጃ ወርክ ሾፕ ቴክኒሺያን ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ለተለያዩ ደረጃዎች ስልጠና ላይ ይገኛሉ።

ዲፓርትመንቱ አሁን ላይ ለነባር መደበኛ እና የአጫጭር ጊዜ ሰልጣኞችን  ከማሰልጠን ባሻገር በከተማ አስተዳደሩ ስር ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የቢሮ እድሳት በማደረግ፣  በኮሌጁ እየተስሩ ያሉ ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች በማከናወን፣  በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የአቅመ ደካማ ቤት እድሳት በመስራት እና መሰል ተግባራትን በቅንጅት እየተገበረ ይገኛለል።

ስልጠና ክፍሉ ቀጣይም አዳዲስ ሰልጣኞችን በክብር ተቀብሎ ዘመኑ በደረሰበት የስልጠና ደረጃ ተራማጅ አመለካከት እና በተግባር የተፈተነ ክህሎት ያለው ዜጋን ለማፍራት ዝግጅቱን አጠናቆ እየተጠባበቀ ይገኛል።

ቀጣይ የሌሎች ዲፓርትመንቶችን ቅኝት እንደምንዳስስ ከወዲሁ እንጠቁማል።

               "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍14
General Wingate Polytechnic college-Official channel pinned «የመመዝገብያ ፎረማችን የነበረበት ችግር ተቀርፎዋል ይህንን ተጠቅመው ይመዝገቡ The problem with our registration form has been solved. Register using this https://docs.goo…»
የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የተገልጋይ አስተያየት ማቅረብያ ፎርም
General Wingate Polytechnic College
User feedback form ወይም የሚከተለውን ሊንክ የጫኑ https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSfwOsDFZhaRhaXxvyOx_yxGRr6yAoZKhP3c978BPM-UT1L8nA/viewform?usp=pp_url
👍2