General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ለተመራቂ ሰልጣኞች ማስታወቂያ

ለ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ!! እያልን የምረቃ መጽሔትና ባይንደር ህትመትን በተመለከተ የክፍያ መጠንና የአከፋፈል ሂደትን የያዘ መረጃ በሚከተለው መልኩ አያይዘናል።
ረቡዕ:- ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

ለስፓርት አፍቃሪያን ቤተሰብ የተላለፈ ማስታወቂያ

እንደ ሀገር ለ4ኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ እየተካሄደ ያለውን ከተማ አቀፍ የቴክኒክ እና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ በነገው ዕለት የኮሌጃችን አሰልጣኞች ከአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አቻቸው ጋር 3:00 ላይ በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስፓርት ሜዳ ግጥሚያ ስለሚያደርጉ በቦታው ተገኝታችሁ ብርታት ሁነን ተብላችኋል።

መረጃውን በሚከተለው መልኩ አያይዘናል።
ሐሙስ:- ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

የኬንያ ልዑካን ቡድን በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አደረገ!!

ከኬንያ ኪሲሙ ናሽናል ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመጣ ልዑካን ቡድን በዛሬው ዕለት በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ አካሄደ፡፡

ልዑካኑ የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ሽግግር እና ቀጣናዊ ትስስር ፕሮጀክት /EASTRIP/ ከሚተገበርባቸው 5ቱ የኬንያ ተቋማት መካከል በጋርመንትና ቴክስታይል ዘርፍ እንደ ምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሌጅ ፕሮጀክት አስተባባሪዎችና ስፔሻሊስቶች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖችና የተለያየ ዘርፍ ባለሙያዎች ናቸው፡፡

ልዑካኑ በቆይታቸው ተቋማዊ የልምድ ልውውጥ ውይይት፣ የወርክሾፖች ጉብኝትና አብሮ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም ስራ ተከናውኗል፡፡

በመግባቢያ ስምምነት ሰነዱ መሰረት በቀጣይ የሰራተኞች ልምድ ልውውጥ፣ የጋራ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ እና የጥናትና ምርምር ስራ ለማከናወን ታቅዷል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ሐሙስ:- ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ለውጦችና በተፈጠሩ ተግዳሮቶች ዙሪያ ላይ ወይይት ተካሄደ!!

ሀገራዊ ለውጡን ተከተሎ በተመዘገቡ ዘርፈ ብዙ ለውጦችና በተከሰቱ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ዙሪያ ከኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

"ብቃት ያለው ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ብልፅግና!" በሚል መሪ ቃል የተደረገው የሰራተኞች ውይይት እንደ ሀገር የመጡ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስኬቶችን እንዲሁም ለሀገራዊ ለውጡ ተግዳሮት የሆኑ ፈታኝ ጉዳዮች ተብራርተዋል፡፡

ከዚህም ባሸገር የውይይት ሰነዱ የሲቪል ሰርቪሱን ሚና በገለፀበት መነሻ ላይ የአመራሩን፣ የሰራተኛውን እና የተገልጋዩን አሁናዊ ሁኔታ በጥንካሬና በድክመት አስቀምጣሉ፡፡

በቀረበው የሰነድ ገለፃ መሰረት ከኮሌጁ አስተዳደር ሰራተኞች ዘርፈ ብዙ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ተነስተው በኮሌጁ ዲኖች ምላሽና ማብራሪያ ተስጥቷል፡፡

በመጨረሻም ለአንዳንድ ጥያቄዎች ደግሞ ለሚመለከተው አካል ቀርበው ምላሽ እንደሚሰጥባቸው ተገልፆ የዕለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ሐሙስ፦ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ∙ም

          "ኢድ ሙባረክ''

ለኮሌጃችን የእስልምና እምነት ተከታይ ሰራተኞች፣ ሰልጣኞች እና አጋሮቻችን በሙሉ እንኳን ለ1446ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የዕድገት እና የበጎነት ይሆን ዘንድ እንመኛለን::

 ጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ሐሙስ:- ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም

#ማስታወቂያ

#ለኮሌጁ #ማኅበረሰብ #በሙሉ

ከሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ቃል 15ኛው የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ፣ በፋሽን ሾው ትርኢት እና በሌሎች አዝናኝ እና አስተማሪ መርሃ ግብራት ይከበራል።

ስለሆነም ተጠባቂው የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ፋሽን ሾው ትርኢትን ጨምሮ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የሚቀርቡት እሁድ ሰኔ 8 ቀን 2017 ዓ.ም ከሰዓት በመሆኑ ሁላችሁም የኮሌጃችን ሰራተኞችና ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት እንድትጎበኙና እንድታበረታቱ እየገለጽን
6:30 ላይ ለትራንስፖርት የተዘጋጁ ባሶች ከግቢ የሚነሱ መሆኑን እንገልፃለን።

የጀነራል ዊንጌት ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበት ደረጃ የግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡

ሰኔ 5/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ የ15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደርዕይ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች የደረሰበትን ደረጃ ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች ጋር በጋራ ገምግሟል፡፡

በግምገማ መድረኩ በቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ የሚካሄዱ ሁነቶች የደረሱበት ደረጃ እና የሚካሄዱበት አግባብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዚህም የኮሌጆችን የመልማት ጸጋ መሰረት በማድረግ በተካሄደው የዞኒንግና ዲፈረንሼን መሰረት በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሰልጣኞችና ሰልጣኞች የተቀዱ ቴክኖሎጂዎች ተግባራዊነት ፍተሻና ልየታ መካሄዱ ተነስቷል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ ህብረተሰቡ ለዘርፉ ያለውን አመለካከት በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ መርሃ ግብሩ የታለመለትን ዓላማ እንዲያሳካ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ዲኖች በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡

የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ የዘርፉን እሳቤ በማስረጽ የ2018 ዓ.ም ሰልጣኞች ቅበላ በማሳደግ ሂደት ሚናው የጎላ መሆኑንም አቶ ጥራቱ ተናግረዋል፡፡

ከቴክኖሎጂ ውድድሩ ጎን ለጎን ዘርፉን በሚያልቁ የተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የፓናል ውይይት እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን የፋሽን ሾው እና ስፖርታዊ ውድድሮች በተቀመጠላቸው መርሃ ግብር መሰረት እንደሚካሄዱ ተጠቁሟል፡፡

15ኛው ከተማ አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ሳምንት "ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች" በሚል መሪ ሃሳብ ከሰኔ 7 እስከ ሰኔ 11 ቀን 2017 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽንና ገበያ ልማት ማዕከል እንደሚካሄድ ይጠበቃል፡፡