ሐሙስ፡ - ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለኮሌጁ ማህበረሰብ በሙሉ
የወደቁትን አንሱ የነደያን በጎ አድራጎት ማህበር ጧሪና ቀባሪ የሌላቸውን አዛውንቶች፣ የአዕምሮ ህሙማን እና አሳዳጊ የሌላቸው ልጆችን እየሰበሰበ ከሚንከባከቡ ጥቂት ድርጅቶች አንዱ ነው፡፡
ይህንን ሰብዓዊ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ደግሞ ከማህበረሰሰቡ፣ ከድርጅቶችና ከተለያዩ ለጋሽ አካላት በማሰባሰብ ነው፡፡
ስለሆነም ወድ የኮሌጃችን ማህበረሰብ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ማህበሩ እገዛ የሚሆን ሁለችንም በምንችለው አበርክቷችንን እናድርግ እያለን ይኸውም ተሰብስበው የሚሰጡ ስጦታዎች በጥሬ ገንዘብና በቁሳቁስ /በአልባሳት/ ነው፡፡
ስለሆነም አገልግሎት የሚሰጡና በሁሉም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ አካላት ሊሆኑ የሚችሉ አልባሳትን እና በጥሬ ገንዘብ የበኩላችሁን ድጋፍ እንድታደርጉ እየገለጽን የበጎነት ስጦታችሁን በኮሌጁ የሰው ሃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮና በቴክኖሎጂ ልማት እና ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን አገልግሎት ም/ዲን ቢሮ ማድረስ እንደምትችሉ እናሳውቃለን፡፡
ሌላም መንገድ አለ የኮሌጁ ሰራተኞች ለሆናችሁ ደግሞ ከሚያዚያ 6 ቀን እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም ያለውን የምሳ ድጎማ ኩፖን ለድጋፉ ይዋልልኝ ካላችሁ ካፌ ሄዳችሁ ማሳወቅ ትችላላችሁ፡፡
ድጋፋችንን ለሚሹ አካላት በምንችለው ስናበረክት በውስጣችን የሚታተመው የበጎነት ደስታና የመንፈስ እርካታ እጅግ የላቀ ነው፡፡
የኮሌጁ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ

ቅዳሜ፡- ሚያዝያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም
የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ተካሄደ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በሐዋሳ ከተማ ተካሄደ፡፡
በዚህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበራ ብሩን ጨምሮ ሌሎች የቢሮው የስራ ኃላፊዎች ፣ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት፣ የተለያዩ ኮሌጆች ዲኖች እንዲሁም የኮሌጁ ዲኖች፣ ማናጅመንት አባላትና የዲፓርትመንት ተጠሪዎች ተገኝተዋል፡፡
በዕለቱ በኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው እና ዶ/ር አበራ ብሩ አማካኝነት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ተቋማዊ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፓርት በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ጀማል ሐሰን አማካኝነት ቀርቧል፡፡
አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራው ሂደት ምን ይመስላል የሚለውን ደግሞ በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የኮንትራክት አዲሚኒስትሬሽን ኤክስፐርት በሆኑት ኢ/ር ዘውዴ ሽፈራ አማካኝነት ገለፃ ተደርጓል።
በሌላ በኩል ተቋሙ የዉስጥ ገቢውን ለማሳደግ ይረዳ ዘንድ የተቋቋመው ኃላ/የተ/የግል ድርጅት ለቀጣይ ያሉት ተስፋዎች፣ ያመጣው ፋይዳና ያሉበት ክፍተቶችን የሚያሳይ ጥናታዊ ቀርቧል።
በመጨረሻም በቀረቡት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ጥናታዊ ጽሑፍ ሰነዶች መሠረት ከተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቶ እና ገንቢ አሰተያየት ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››

ማክሰኞ፡- ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
ለኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች በፕሮጀክት ቤዝድ አሰጣጥ ስልጠና ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ተሰጠ!!
ከሁሉም ኮሌጆቸ ለተወጣጡ የኮንስትራክሽን ዘርፍ አሰልጣኞች በፕሮጀክት ቤዝድ ስልጠና አሰጣጥ ዙሪያ ትናንት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ የጋራ ግንዛቤ ተሰጠ።
በከተማ አስተዳደሩ ስር በሚገኙ 15ቱ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ውስጥ ኮንስትራክሽን ዲፓርትመንት ላይ ያሉ አሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸውን እንዲያሻሽሉና ፕሮጀክትን መሰረት ያደረገ እውቀት እንዲያገኙ ታሳቢ በማድረግ ለተዘጋጀው ስልጠና ግንዛቤ እንዲኖራቸው በትናንትው ዕለት ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በዚህ ገለፃ ላይ ከሁሉም ኮሌጆች 583 አሰልጣኞች ተገኝተዋል።
ኮሌጁ የቴክኒክ እና ሙያ ስልጠናን ሲጀምር የኮነስትራክሽን ዘርፍ ማሰልጠኛ ት/ቤት የነበረ መሆኑና በቀጣይም የአካባቢን ጸጋ መሰረት ያደረገ ስልጠና ለመስጠት በያዘው ዕቅድ ኮንስትራክሽንን ቀዳሚ ምርጫ ያደረገ መሆኑ ለተዘጋጀው ስልጠና ተመራጭ አድርጎታል።
ስልጠናው ለ26 ቀናት የሚሰጠ ሲሆን መሰረታዊ ዓላማው የዘርፉ አሰልጣኞች የክህሎት ክፍተታቸውን በመሙላት የሙያ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡና የሚሰጡትን ስልጠና ፕሮጀክትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ ታቅዶ ነው ተብሏል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

#ማስታወቂያ
ለኮሌጃችን የውስጥ ሰራተኞች እና ለውጪ የተቋማችን አጋር ማኅበረሰብ በሙሉ
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተቋማዊዩ የግል ኢንተርፕራይዝ ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ እያለ ለበዓል ያደለባቸውን ምርጥ #በሬዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ለመሸጥ እንሆ ይላል፡፡
ስለሆነም በተዘጋጀው ጥቂት የመሸጫ ቀናት ውስጥ ፈጥነው በመምጣት የመረጡትን ሰንጋ በተመጣጣኝ ዋጋ መሸመት የሚችሉ መሆኑን ስንገልጽልዎት በታላቅ ደስታ ነው፡፡
ስለዚህ ለመግዛት ከፈለጉ ይምጡ ለበዓል ይሸምቱ ተብላችኋል።
#አድራሻ፡- ቦታ - ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ
ስልክ - 0991824160
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ