General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ:- የካቲት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

           በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ተካሄደ!!

በኮሌጅ ደረጃ የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተካሄደ።

እንደ ሀገር ለ4ኛ እንደ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ የሚካሄደው የዘንድሮው የሰልጣኞች የክህሎት ውድድር " ብሩህ አዕምሮዎች፣ በክህሎት የበቁ ዜጎች!" በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

እንደ ኮሌጅ የክህሎት ውድድር የተደረገባቸው ዲፓርንመንቶች ኮንስትራክሽን፣ ኤሌክትሪክሲቲና ኤሌክትሮኒክስ፣ ቴክስታይል ሌዘር ጋርመንት፣ ሜታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ሆቴልና ሆስፒታሊቲ እና ውድ ወርክ ቴክኖሎጂ ናቸው፡፡

በዚህ ውድድር 42  ሰልጣኞች በ13 ሙያዎች በኮሌጅ ደረጃ የክህሎት ውድድር ላይ ተሳትፈዋል፡፡

ከሁሉም ዘርፎች 1ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ተወዳዳሪዎች ቀጣይ በክላስተር ደረጃ በሚደረገው ውድድር ይካፈላሉ፡፡
 
በዚህ ዓመት የአሰልጣኞች እና አንቀሳቃሾች ክህሎት ውድድር እንደማይደረግ ታውቋል፡፡
       
         "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
To All 2017 Graduating Trainees

First of all, congratulations to all 2017 graduating trainees! We are pleased to announce that the training period for this year is coming to an end, and the graduation day is approaching. Therefore, the Trainee Council has made various plans to enhance the graduation atmosphere. One of our main plans is to create GC (Graduation Class) T-shirts for the graduating trainees.

Therefore, all graduating trainees who wish to order a T-shirt are requested to deposit the payment into the bank account from today, Monday, July 1, 2017, to July 7, 2017. Bring the bank deposit slip to the Council office to register your T-shirt size and name. Price: 450 Birr, Bank Account: Commercial Bank of Ethiopia 1000667783554 Yisak Seifu & Elias Mulugeta & Dibora Kiflu

For more information, please call: 0904738226 or 0985265461.
-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
ለ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ

በቅድሚያ የ2017 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ሰልጣኞች እንኳን ደስ አላችሁ እያልን የዘንድሮ አመት የስልጠና ጊዜ እየተገባደደ እንዲሁም የምርቃት ቀን እየተቃረበ መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም የምርቃት ድባቡን ለማምጣት በሰልጣኝ ካውንስል የተለያዩ እቅዶች ተይዘዋል። ከነዚህም አንዱ ለተመራቂ ሰልጣኞች የGC ቲሸርት ማሰራት ዋነኛው እቅዳችን ነው።

ስለዚህ ተመራቂ ሰልጣኞች በሙሉ ቲሸርት ማሰራት የምትፈልጉ ሰልጣኞች ከዛሬ ሰኞ 1/07/2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ 7 / 7 /2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ ብሩን በባንክ አስገብታችሁ ደረሰኙን በመያዝ ካውንስል ቢሮ መጥታችሁ የ ቲሸርት ልኬታችሁን እና ስማችሁን እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን ።

የአንድ ቲሸርት ዋጋ 450 ብር ብቻ ሲሆን የባንክ አካውንት : የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000667783554 Yisak Seifu & Elias Mulugeta & Dibora Kiflu

ለበለጠ መረጃ : በ0904738226 ወይም 0985265461 ላይ መደወል ይችላሉ።
ማክሰኞ፡- መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም  

   ማርች 8 የሴቶች ቀን በኮሌጁ ተከበረ!!

በኢትዮጵያ ለ49ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ114 ጊዜ የሚከበር ማርች 8 የሴቶች ቀን የኮሌጁ ሰራተኞችና ሰልጣኞች በተገኙበት ተከበረ፡፡

ማርች 8 እንደ ጎርጎሮሳዊያን የዘመን ቀመር 1908 ላይ ኗሪነታቸው በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ የሆኑና በተለይ ደግሞ በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ሰራተኞች የነበሩ 15,000 ሴቶች በአደባባይ ወጥተው የሥራ ሰዓት እንዲሻሻል /እንዲያጥር/፣ የደመወዝ ክፍያ እኩልነት እንዲፈጠር እና የመምረጥ መብታቸው እንዲከበር ለጥያቄ የወጡበት ታሪካዊ ቀን እንደሆነ ይነገራል፡፡

በ1975 ዓ.ም ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ቀንን ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ በይፋ እንዲከበር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

‹‹የሴቶች ቀን ሲከበር ለመድረክ ፍጆታ ብቻ ሳይሆን ሴቶች ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸው እንዲያዲግ እንዲሁም ተጠቃሚነታቸውና አበርክቷችሁ የጎላ እንዲሆን መሆን አለበት፡፡ ይህንን ተነሳሽትና ትጋት እንደ ኮሌጅ ስንመለከት በተዘጋጀው ተቋማዊ የልማት ስራዎች ላይ ሴቶችም በእኔ እችላለው መንፈስ ተሳትፏችሁ የበለጠ ጎልቶ መታየት ይኖርበታል›› ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡         

በሌላ በኩል ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት የመጡ የስርዓተ ፆታ ባለሙያዎች ስለ ማርች 8 ምንነትና በህይወት ክህሎት ላያ ያተኮረ ሙያዊ ገለፃ ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም ለኮሌጃችን ሴት ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ለማርች 8 እንኳን አደረሳችሁ እያልን መልካም የስኬት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡ 

  "በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ማክሰኞ:- መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም

የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ ጉብኝት አደረጉ!!

የአዲስ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡

በዕለቱ ከ150 በላይ የሚሆኑ እና ከ11ኛ ክፍሎች የተውጣጡ ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን ተቋማዊ ስነ ምህዳር እና አጠቃላይ የስራ እንቅሰቃሴ ገለፃ ተሰጥቷቸው የልዩ ልዩ ዲፓርትመንቶችን ወርክሾፖች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡

የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ ቀጣይ የ12 ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱ በኋላ ወደ ቴክኒክና ሙያ ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች ስለ ሙያ ስልጠና ከአሁኑ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው እና ለምርጫ እንዳይቸገሩ ለማድረግ ነው ተብሏል፡፡

ከዚህ ባሻገር አሁን ላይ እስከ ደረጃ 2 ያለውን የሙያ ስልጠና ከቀለም ትምህርት ጋር አቀናጅተው ስለሚማሩ ወርክሾፖችን በመጎብኘት መሰረታዊ መረጃ ለማሰጨበጥ ይረዳል መባሉንም ሰምተናል፡፡

ተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም እንደተደሰቱ ገልፀው የሙያ ትምህርት ለመማር ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ምስክርነትን ሰጥተዋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››