General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.95K subscribers
3.35K photos
43 videos
204 files
196 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፡- መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሌጁ የስራ  አፈፃፀምና የሪፎርም ትግበራ ግምገማ ተካሄደ!!

ሁሉም የኮሌጁ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የኮሌጁ የ8 ወር ዕቅድ አፈፃፀም እና የስራና ክህሎት ቢሮ የሪፎርም ትግበራ ሂደት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት፡፡

በውይይቱ  ላይ በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ አካማሪ አቶ ቸርነት በላቸው፣ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚና የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ከበደ እና የኮሌጁ አመራሮች ተገኛተዋል፡፡

እንደ ኮሌጅ ከአዲሱ የቴክኒክና ሙያ እሳቤ አተገባበር ጋር በተያያዘ ያለውን አፈፃፀም ያቀረቡት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ሲሆኑ በተቋሙ ከ11 የቴክነክና ሙያ ዘረመሎች /DNA/ አንፃር የተከናወኑ አበየት ተግባራትን በየዘርፉ አቅርበዋል፡፡

በዚህም ተቋሙን ለሰራተኞችና ሰልጣኞች ምቹ ከማድረግ ረገድ፣ የኢንዱስትሪዎችን ገበያ ፍላጎት ያደረገ ስልጠና ከመስጠትና ከግሉ አልሚ ጋር በአጋርነት ከመስራት አንፃር፣ በአካባቢ ፀጋ ለይቶ ከማሰልጠንና ተቋማዊ ኢንተርፕራይዞችን ፈጥሮ የሀብት ማግኛ ከማድረግ አኳያና መሰል ሀሳቦች በአፈፃፀሙ ተገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል የከተማ አስተዳደሩ ስራና ክህሎት ቢሮ የሰራቸውንና እያከናወናቸው ያሉትን የሪፎርም ትግበራ ያቀረቡት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የቢሮ አካማሪ አቶ ቸርነት በላቸው ሲሆኑ አሰራሩን ማስተካከል፣ አመራሩን መልሶ ማደራጀት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት፣ የስራ አካባቢን ለአገልግሎት ምቹ ማድረግ፣ የዲሲፕሊን ክፍተቶች ላይ የእርምት እርምጃ መውሰድ የሚሉት ሲተገበሩ በቀጣይ መረጃዎችን በቴክኖሎጂ አጠናክሮ መቀጠል፣ የተቋማት አካባቢያዊ ፀጋ ልየታን መተግበር፣ የኮሌጆችን ኢንተርፕራይዞች አጠናክሮ ማስቀጠል የሚሉት ተግባራት ይገኙበታል፡፡
     
በመድረኩ ላይ የተገኙ ተሳታፊዎችም በቀረበው ተቋማዊ አፈፃፀምና ቢሮው እየተገበረው ባለው የሪፎርም ስራ     ጠንካራ አቅሞች ናቸው ያሏቸውን አድንቀው፤ ማስተካከያ ቢደረግባቸው የሚሏቸውን ደግሞ ገንቢ አስተያየቶች አቅርበዋል፡፡ በመጨረሻም ከመድረኩ የማጠቃለያ ምላሾች ተሰጥተው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
ኮሌጁ ከአዳስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ቅዳሜ በአንድ ገፅ አምድ ላይ ልዩ ልዩ ሳምንታዊ መረጃዎችን የሚያሰራጭ ሲሆን የነገ መጋቢት 6 እትም ላይ ደግሞ ከቴክኖሎጂ ፈጠራል እስከ ተቋማዊ ማምረቻ የደረሰውን የእንሰሳት መኖ ማቀነባበሪያ ማሽን ነገረ ተረክን ይዛ ትወጣለች።

መልካም ንባብ!!
ኮሌጁ ከአዳስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ቅዳሜ በአንድ ገፅ አምድ ላይ ልዩ ልዩ ሳምንታዊ መረጃዎችን የሚያሰራጭ ሲሆን የዛሬዋ መጋቢት 13 ዕትም ላይ ደግሞ የአካባቢ ፀጋን መሠረት ያደረገ ስልጠና አሰጣጥ ትግበራ ጋር የተያያዘ መረጃን በ16ኛው ገጿ ላይ ሀተታ ይዛ ወጥታለች።

     መልካም ንባብ!!
ረቡዕ:-  መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

      የመስከረም 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በኮሌጁ የሚሰጠውን የሙያ ስልጠና ምልከታ አደረጉ!!

በአራዳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መስከረም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የ7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2017 ዓ.ም በኮሌጁ ትምህርታዊ ጉብኝት አደረጉ፡፡
 
በዕለቱ 135 የሚሆኑ ተማሪዎች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን ተቋማዊ ስነ ምህዳር እና አጠቃላይ የስራ እንቅሰቃሴ ገለፃ ተሰጥቷቸው  የተለያዩ ዲፓርትመንቶችን ወርክሾፖች እንዲጎበኙ ተደርጓል፡፡

የጉብኝቱ መሰረታዊ ዓላማ አሁን ላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናዎች በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፉ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ላይ በተጓዳኝነት የሚሰጥ በመሆኑ ስለሙያ ስልጠና አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ ነው፡፡

ተማሪዎቹ እየተማሯቸው የሚገኙትን የሙያ ዘርፍ ስልጠና ወርክሾፖች የተመለከቱ ሲሆን እነሱም ኮንስትራክሽን፣ ጋርመንት /ልብስ ስፌት/፣ ከተማ ግብርና እና ሆቴል / ምግብ ዝግጅት/ የተግባር ስልጠና መስጫዎችን ተመልክተዋል፡፡

ተማሪዎቹ በተሰጣቸው ማብራሪያ እና በጉብኝት ወቅቱ ባዩት የስራ እንቅስቃሴ በጣም መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሰሞኑን የአዲስ ከተማ እና የጀ/ ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተማሪዎች በተመሳሳይ በተቋሙ ትምህርታዊ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን የኮሌጁን የሙያ ስልጠና ሂደት የተለያዩ ት/ቤቶች ጉብኝት እንዲያደርጉ የሚያስተባብረው በኮሌጁ የስልጠናና አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲን ቢሮ ስር የስራ ትስስርና ካውንስሊንግ የስራ ክፍል ነው፡፡   

   ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
አርብ:- መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

በኮሌጁ አሰልጣኞች የተሰራ ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ቀረበ!!

ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቡድን የሰሩ አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በትናንትናው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።

በዚህ ውድድር 5 የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ምዘና የተደረገባቸው ሲሆን በሁሉም ዘርፎች የተሰሩ የምርምር ተግባራት የኮሌጁን አገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ይረዳሉ ተብሏል።

የተግባራዊ ጥናትና ምርምሩ ዓላማ እንደ ተቋም የራስን ችግር በራስ አቅም ለመፍታት ያቀደ ሲሆን ሁሉም ጥናቶች የተነሱበትን ክፍተቶች ለመሙላት የሚችሉ ናቸው ተብሏል።

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።

እንደ ተቋም 9 ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እየተሰራ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው ለግምገማ የቀረቡት 5ቱ ናቸው።

አሸናፊው ሰነድ እንደ ከተማ በቴክኒክና ሙያ ሳምንት ከአቻ ተቋማት ስራ ጋር ውድድር የሚጠብቀው ሲሆን ባለፈው ዓመት በኮሌጁ የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በከተማ ደረጃ አንደኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ አይዘነጋም፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
ኮሌጁ ከአዳስ ሚዲያ ኔትወርክ አዲስ ልሳን ጋዜጣ ጋር በመተባበር በየሳምንቱ ቅዳሜ በአንድ ገፅ አምድ ላይ ልዩ ልዩ ሳምንታዊ መረጃዎችን የሚያሰራጭ ሲሆን የዛሬዋ መጋቢት 20 ዕትም ላይ ደግሞ በተቋሙ የሚተገበሩ የዲጂታላዜሽን ስርዓተ ትግበራ ጋር የተያያዘ መረጃን በ19ኛው ገጿ ላይ  ሀተታ ይዛ ወጥታለች።

     መልካም ንባብ!!