General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ሐሙስ፡- ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም                                                                                                                  
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት አመራር አካላት በኮሌጁ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ!!

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዛሬ ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡

‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደ  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማቱ እና የኮሌጁ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ግቢውን በልዩ ልዩ እጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

የዚህ ዓመት ሀገራዊ የአረንጓዴ አሻራ ማስቀመጥ መርሃ ግብር አካል በሆነው የችግኝ ተከላ ንቅናቄ መሰረት በዛሬው ዕለት በኮሌጁ ከ6000 በላይ ችግኞች መትከል የተቻለ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 4ሺው /66.6 በመቶው/  ቡና፣ አቡካዶ፣ አፕልና ሌሎችን ጨምሮ የአትክልት እና ፍራፍሬ  እፅዋት ናቸው፡፡

‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍184👌1
አርብ፡- ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም                                                                                                                 

‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል በኮሌጁ ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄደ!!

በዛሬው ዕለት ‹‹የምትተክል ሀገር፣ የሚያፀና ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል በተያዘው ዕቅድ መሰረት የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችና ሰራተኞችም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ፡፡ 

በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የጥላ ዛፎች፣ የውበት አበባዎች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ዕጽዋቶች በኮሌጁ ቅጽረ ግቢ ተተክለዋል፡፡

በተያየዘ ዜና በትናንትና ዕለት ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም  የስራና ክህሎት ሚኒስቴር  እና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄደዋል፡፡

በተካሄደው  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን ጨምሮ ሌሎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ፣ የተጠሪ ተቋማቱ እና የኮሌጁ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እንዲሁም የኮሌጁ ተመራቂ ሰልጣኞች በቦታው በመገኘት ግቢውን በልዩ ልዩ እጽዋት የማልበስ ስራ ላይ ተሳትፈዋል።

         ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍5
#Happeningnow

#አሁን

ቅዳሜ፡- ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም

በኮሌጁ እንደ ክላስተር ግምገማዊ ስልጠና ለአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች እየተሰጠ ነው!!

በጀነራል ዊንጌት ክላስተር ስር  ባሉ ኮሌጆች ለሚገኙ የአስተዳደር ዘርፍ ሠራተኞች በዛሬው ዕለት ግምገማዊ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በዚህ መድረክ ላይ የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ የኮልፌ ኢንዲስትሪያል ኮሌጅ እና የአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪል ኮሌጅ ሰራተኞች እየተሳተፉ ሲሆን ግምገማዊ ስልጠናው ህብረ ብሄራዊ አንድነትና ወንድማማችነት ለጋራ ብልፅግና በሚል መሪ ሀሳብ የቀረበ ነው፡፡ 

የግምገማዊ ስልጠናው መሠረታዊ ዓላማ የሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር፣ ብልሹ አሰራርን ለመከላከልና የሃገርን ዘላቂ ሰላምና ዕድገት ለመፍጠር እንዲሁም ከትርክት የዘለለ በምክንያት እና በእውነት የሚያምን ፐብሊክ ሰርቪስ ለመፍጠር ነው ተብሏል፡፡

ለግምገማዊ ስልጠናው  የመወያያ ሰነድ በማቅረብ እና በቡድን ውይይት እንዲዳብር በማድረግ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር መታሰቡን ከመድረኩ ሰምተናል፡፡

ለሰራተኞቹ እየተሰጠ ባለው ግምገማዊ ስልጠና የቡድን ውይይቱ በከተማ አስተዳደሩ እና በክፍለ ከተማ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች  እየተመራ ይገኛል፡፡
  
‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍92