General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
ማክሰኞ:- ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም

በክላስተር ደረጃ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተደረገ!!

ከተለያዩ ኮሌጁች ተውጣጥተው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር በቡድን የሰሩ አሰልጣኞች የጥናት ውጤት ሰነዳቸውን በዛሬው ዕለት ለውውድር አቀረቡ።

በዚህ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ በአዲስ ከተማ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ እና በኮልፌ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ አሰልጣኞች የተሰሩ 3 የጥናትና ምርምር ሰነዶች ለባለሙያዎች ቀርበው ተወዳድረዋል፡፡

በውድድሩ ርዕሰ ጉዳዩ አንገብጋቢ ችግር መሆኑ፣ ከችግሩ ጋር የተሰናሰለ ዓላማ መቀረጹ፣ ችግሩን ለመፍታት የተደረገው ርቀት፣ በምርምር ሂደቱ የተገኙ ውጤቶች፣ ወዘተ የሚሉ መስፈርቶች ተካተዋል።

በዚህ ውድድር በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ አሸናፊ ሆኖ በከተማ ደረጃ ለሚደረገው ውድድር አልፏል፡፡

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አሰልጣኞች የተሰራው ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ሰነድ የአዳዲስ ሰልጣኞችን መጠነ ማቋረጥና ማቆራረጥን ለመቀነስ የተነሳ እንደሆነ መዘገባችን ይታወቃል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍18
ረቡዕ:- ግንቦት 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Unite in the fight against HIV/Aids!

ከኤች አይ ቪ/ ኤድስ መከላከያ ጋር በተያያዘ የግንዛቤ መድረክ ተደረገ!!

ለኮሌጁ ሰራተኞች እና ሰልጣኞች ከኤች አይ/ ኤድስ መከላከያ ጋር በተያያዘ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ትናንት ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተደረገ፡፡

በአሁኑ ሰዓት ከሰዎች መዘናጋት ጋር ተያይዞ እንደ አዲስ ብዙ ሰዎችን ማጥቃት የጀመረው የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ያስችል ዘንድ መድረኩ መዘጋጀቱን ሰምተናል፡፡

በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ላይ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በመጡ ባለሙያ ወቅታዊ የቫይረሱን የስርጭት አድማስ እና በሽታውን የመከላከያ ስልቶች ገለፃ እንዲደረግባቸው ተደርጓል፡፡

መድረኩን በሁለት ዙር /ጧት እና ከሰዓት/ ያዘጋጁት የኮሌጁ ጤና ባለሙያዎች እና የሚኒስትሪሚንግ ኮሚቴ አባላት ሲሆኑ ዋና ዓላማው ለኮሌጁ ማህበረሰብ ግንዛቤ በመፍጠር በቫይረሱ ጉዳይ ላይ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ነው ብለዋል፡፡ TEST OFTEN, TREAT EARLY, STAY SAFE.


"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍4
ሐሙስ:- ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የሰልጣኞች የስምግባር ክበብ አባላት በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ አደረጉ!!

በኮሌጁ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የተዘጋጀው የሰልጣኞች ስነ ምግባር ክበብ አባላት ልምድ ልውውጥ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ የተሰሩ የሰልጣኞች ስነምግባር ልምዶችን እንዲጋሩ ተደርጓል፡፡

በልምድ ልውውጡ ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንፃር፣ የድሲፕሊን ግድፈቶችን ከማረም ረገድ፣ የግብዓት ብክነትን ከማስተካከል አኳያ ወዘተ የተሰሩ ተግባራትን የአቻ ለአቻ ተሞክሮ እንዲካፈሉ ተደርጓል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
2👍2
ሐሙስ:- ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

የ14ኛ ቴክኒክና ሙያ ሳምንት አካል የሆነ የስፖርት ውድድር መክፈቻ ተካሄደ!!

ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚከበረውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ የተዘጋጀው የስፖርት ውድድር መክፈቻ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት ሳርቤት በሚገኘው ተስፋ ሜዳ ተካሄዷል፡፡

በመክፈቻ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራ እና ክህሎት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ተወካዮች እንደሁም የ15ቱም ኮሌጆች ዲኖችና የስፖርት ቤተሰቡ ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት የመክፈቻ መልዕክት ያስተላለፉት በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መክብብ ወለደ ሃና ናቸው፡፡

ኃላፊው በንግግራቸው የዝግጅቱ ዓላማ ኮሌጆች እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉና ከስልጠና ባሻገር በስፖርት ልማቱና በማህበረሰብ አገልግሎቱ አበርክቷቸውን እንዲያረጋግጡ ነው ብለዋል፡፡ አቶ መክብብ አያይዘውም ለቴክኒክና ሙያ ሳምንት ዝግጅት ከስፖርት ባሻገር የክህሎት ውድድር እየተካሄደ እንደሚገኝ እና ከሰኔ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርዕይ በኢግዚቪሽን ማዕከል እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡

በዛሬው መክፈቻ ዝግጅት ላይ አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ከአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር የአሰልጣኞች ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከአቻው ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር ቀጣይ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም 3፡00 ላይ በእንጦጦ ሜዳ ግጥሚያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡

"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍8🏆31👏1👌1
Forwarded from FELEKE WAKE
👍3👎1
አርብ፦ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

ውድ የኮሌጃችን ሰራተኞች እና ሰልጣኞች!

14ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ የኮሌጃችን የአሰልጣኞች የእግር ኳስ ቡድን ነገ ቅዳሜ 3:00 ላይ በእንጦጦ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሜዳ ከአቻ ተጋጣሚው ምስራቅ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር ጨዋታውን ስለሚያደርግ በዕለቱ በቦታው በመገኘት የሞራል ድጋፋችሁን እንድትለግሱት እንገልፃለን።

በተመሳሳይ የኮሌጁ የሰልጣኞች የእግር ኳስ ቡድን ደግሞ በዚሁ ቀን 4:30 ላይ በየካ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ከአቻው ተግባረ ዕድ ጋር ግጥሚያ ስለሚያደርግ ተገኝታችሁ ብርታት እንድትሆኑት እናሳውቃለን።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
👍81
አርብ፦ ግንቦት 16 ቀን 2016 ዓ.ም

ማስታወቂያ

የቀን ለውጥ ማስተካከያ

ውድ የኮሌጃችን ሰራተኞች እና ሰልጣኞች!

14ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት ምክኒያት በማድረግ የኮሌጃችን የአሰልጣኞች እና የሰልጣኞች የእግር ኳስ ቡድን ነገ ቅዳሜ ውድድር እንዳለ መግለፃችን ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ቅዳሜ ግንቦት 17 ቀን 2016 ዓ.ም የነበረው ጨዋታ ወደ እሁድ ማለትም ግንቦት 18 ቀን 2016 ዓ.ም የተቀየረ መሆኑን ዘግይቶ በደረሰ መረጃ አረጋግጠናል።

ስለሆነም ሁሉም ጨዋታዎች በተቀያሪው ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ስለሚካሄዱ ተገኝታችሁ ቡድኖቹን ድጋፍ እንድትሰጡ ከይቅርታ ጋር ደግመን እናሳውቀለን።

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
🏆11👍83👎1
Forwarded from Sol
👏50👍215