General Wingate Polytechnic college-Official channel
9.96K subscribers
3.37K photos
43 videos
204 files
198 links
ራዕይ:- በ2022 በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሆን።

የአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርተፍኬት ባለቤት።
Download Telegram
አርብ፦ ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

    የጽሑፍ ዝግጅት ውድድር ማስታወቂያ


     ውድ የኮሌጃችን  ማህበረሰብ በሙሉ!

በኮሌጁ የተለያዩ የህትመት ስራዎች እንደሚዘጋጁ ይታወቃል። ስለሆነም ለሚዘጋጁ ቡክሌቶች ጥሩ አርቲክሎችን ያዘጋጁ አካላትን አወዳድሮ #ለመሸለም የተዘጋጀ በመሆኑ በመወዳደሪያ መስፈርቱ ይዘት እና በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት አዘጋጅታችሁ እንድታቀርቡ ይጋብዛል።

መልካም ዕድል እያልን አጠቃላይ መረጃውን ከላይ አያይዘናል።

      የኮሌጁ #EASTRIP ፕሮጀክት ጽ/ቤት
👍31
አርብ:- ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

ለሦስት ሳምንታት ቆይታ የነበረው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ!!

ከተለያዩ ዲፓርትመንቶች የተውጣጡ አሰልጣኞች የተሳተፉበት የአሰልጣኞች ስልጠና #ኬፕለር በተሰኘ ግብረሰናይ ድርጀት አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን መሠረታዊ ዓላማው ለተመራቂ ሰልጣኞች ከስራ ገበያው ጋር አዎንታዊ ምልከታ እና በጎ ተጽዕኖ እንዲናራቸው የሚያስችል የሶፍት ስኬል ስልጠና እንዲሰጡ ታቅዶ መሆኑን ሰምተናል።

ስልጠናው በሙያው ብዙ ልምድን ባካበቱ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን 20 የሚሆኑ የኮሌጁ አሰልጣኞች እና ከጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የተቀላቀሉ 3 አሰልጣኞች ተሳትፈዋል።

በሌላ ዜና ብቃት የወጣቶች ስልጠናን ወሰደው በኢንዱስትሪዎች ላይ የስራ ልምምድ እያደረጉ የነበሩ 400 ወጣቶች 3ኛ ወራቸው ላይ ወደ ኮሌጁ በመመለስ ለ5 ቀናት የዲጂታል ስኪል ስልጠና ሲወስዱ ቆይተው በትናንትናው ዕለት አጠናቀዋል።

               "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👍11
ቅዳሜ :- ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

ሰልጣኛኞች የላብ አደሮች ቀንን አከበሩ!!

የዛሬዎቹ ሰልጣኞችና የነገዎቹ ሰራተኞች በትናንትው ዕለት የላብ አደሮች ቀን /ወርከርስ ደይ/ በሚል መነሻ በልዩ ልዩ ትርዒት አከበሩ።

በእኛ ሚያዚያ 23 በጎርጎሮሳዊያኑ ደግሞ ግንቦት /ሜይ/ 1 ተከብሮ እና ታስቦ የሚውለውን የላብ አደሮች ቀን ምክንያት በማድረግ ሜይ 31 ወይም የወሩ መጨረሻ ቀን ላይ አስበውታል።

በዚህ ዝግጅት የእሳት እና ድንገተኛ አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችን ጭምር በመጠቀም ልዩ ልዩ አዝናኝ እና አስተማሪ ትርኢቶች አሳይተዋል።

ግቢ ውስጥ በየዓመቱ በሰልጣኛኞች ለተዝናኖት እና ለትምህርት ከሚከበሩ መካከል አንዱ የሰራተኞች ቀን ነው።

የላብ አደሮች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲከበር ገፊ ምክንያቱ የቀን የስራ ሰዓት ከ10 እስከ 16 የነበረው 8:00 እንዲሆን፣ የስራ ቦታ ለህይወት ደህንነት አደጋ አጋላጭ ከሆኑ ነገሮች እንዲስተካከል፣ ቅዳሜም እንደ እሁድ የእረፍት ቀን እንዲቆጠርና መሰል ጥያቄዎች በጊዜው ለነበሩ አሜሪካዊ አሰሪ ከበርቲዎችና ባለ ስልጣናት በተለያየ ጊዜ በአመፅ ቀርቦና መሰዋትነት ተከፍሎ የመጨረሻ መልስ ያገኘው ሚያዝያ 23/ሜይ 1 ቀን 1880 ሲሆን አሁን ላይ ቀኑ ኢትዮጵያን ጨምሮ በ66 አገራት ሲከበር በሌሎች ደግሞ ታስቦ እንደሚውል ይታወቃል።

               "በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
👎7👍3👌2
ቅዳሜ ፡- ግንቦት 24 ቀን 2016 ዓ.ም

የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት ተካሄደ!!

የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ EASTRIP ፕሮጀክት የ9 ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ በአዳማ ከተማ ሂልሳይድ ሆቴል ተካሄደ፡፡

በዚህ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ውይይት  ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ እና ክህሎት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ የከተማው ኮንስትራክሽን ቢሮ ተወካዮች፣ የአስተዳዳሩ ፋይናንስ ቢሮ ተጋባዦች፣ ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተውጣጡ የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት እና የኮሌጁ ዲኖች ተገኝተዋል፡፡

በዕለቱ በኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው አማካኝነት የእንኳን ደህና መጣችሁ የመግቢያ ንግግር ከተደረገ በኋላ ተቋማዊ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የስራ አፈፃፀም ሪፓርት በፕሮጀክት ጽ/ቤቱ አስተባባሪ አቶ ጀማል ሐሰን አማካኝነት ቀርቧል፡፡  

አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራው ሂደት ምን ይመስላል የሚለው መረጃ ደግሞ በኮንስትራክሽን አማካሪ ድርጅቱ መሀንዲስ ቢኒያም አለማየሁ አማካኝነት በዝርዝር ቀርቧል።

በሌላ በኩል ለኮሌጁ አመራር እና ባለሙያዎች በተለያየ ጊዜ የተሰጡ ልዩ ልዩ ስልጠናዎች በተቋሙ ላይ ያመጡት ፋይዳና የነበረባቸው ክፍተቶችን የሚያሳይ ጥናታዊ ጽሑፍ በዶ/ር ፍስሐ ማሞ ቀርቧል።

በመጨረሻም በቀረቡት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና ጥናታዊ  ጽሑፍ ሰነዶች መሠረት ከተሳታፊዎች ጥያቄ ተነስቶ እና ገንቢ አሰተያየት ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
 
     ‹‹በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት››
👍13