እሁድ፡- ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም
በኮሌጁ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ተካሄደ!!
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ የተመራ ልዑካን ቡድን ዛሬ ጥር 26 ቀን 2016 ዓ.ም በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ።
በልዑካን ቡድኑ ከቢሮው ሃላፊ ባሻገር ምክትል ቢሮ ሃላፊዎች፣ የቢሮው ዳይሬክተሮች እና የሁሉም ኮሌጆች ዲኖች የተገኙ ሲሆን በኮሌጁ የተሰሩ እና እየተሰሩ ያሉ ልዩ ልዩ የስልጠና ፋሲሊቲዎችን በመጎብኘት ልምድ እንዲጋሩ ተደርጓል።
ኮሌጁን በአይ ኤስ ኦ /ISO/ የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ከማስደረግ ጀምሮ ልዩ ልዩ አስደማሚ ተግባራትን በቅንጅት ሰርቶ እምርታዊ ለውጥ ይመጣ ዘንድ የተጠቀሙበትን የመሪነት ፍልስፍና ለልዑካን ቡድኑ ያጋሩት የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው።
በሌላ በኩል የቢሮው ሃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው ለውጥ ለማምጣት በቂ ግብዓት አለን ነገር ግን ውስጣዊ ተነሳሽነት እና ቅንጅታዊ አስራር በመፍጠር ታሪክ መቀየር እንደምንችል ከዛሬው ጉብኝት ሰፊ ትምህርት አግኝተናል ብለዋል። አቶ ጥራቱ አክለውም እኛም ወደ ፊት መቀጠል የምንችለው ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ ለውጥ ስናመጣ ብቻ ነው በማለት ተናግረዋል።
በዛሬው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት ከጀነራል ዊንጊት ፖሊ ቴክኒክ ባሻገር በደጃዝማች ወንድይራድ ቅድመ መደበኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፣ በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጀንሲ በመገኘት ያሉ መልካም ስራዎችን ለመቅሰም ተሞክሯል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍15❤1
Forwarded from Teshe
ዕለተ ማክሰኞ ጥር 28/2016 ዓ.ም
በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት ተደረገ።
የጉብኝት የተደረገበት ዋና ዓላማ በኮሌጁ የተከናወኑትን ተግባራትን፣የፈጠራ ስራዎች፣የአሰራር ሂደቶች፣ እና የገቢ ማመንጫ ዘዴዎችን በጎ ልምድ በመቅሰም በእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ተቋማዊ ሪፎርም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ላይ ተጨማሪ ግብአት እንዲሆን የለመ ነው።
በጉብኝቱ የተሳተፉት የኮሌጁ ማኔጅመንት እና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላትን በመቀበል የእንኳን ደህና መጣንሁ መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ተቋማት አቅም ግንባታ ም/ዲን አቶ ሰበኸዲን በኮሌጅ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ተቋማዊ ለውጦች በኮሌጁ አሰልጣኞች መሆኑን ገልፀዋል ። በተጨማሪም የፕሮጀክቱ ባለቤትና ተሳታፊ የሆኑ አሰልጣኞች ሰለ ሰሯቸው ፕሮጀክቶች ገለፃ ያደረጉ ሲሆን በገለፃውም፦
- በኮሌጁ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን ጋር አብሮ ለመራመድ
የሚያስፈልጉ ቴክኖሎጂዎች እና ስርዕቶች እየተዘረጉ
መሆኑን
- በኮሌጁ ውስጥ ዲጅታላይዜሽንን በሁሉም ዘርፎች
ለመተግበር ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነና
በተጨማሪም በዕቅድ ለመተግበር
በdevelopment ደረጃ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች እንዳሉ
- የውስጥ አቅማቸውን በቴክኖሎጂ ከማጠንከር
ባሻገር የተመረጡ ጥቂት አሰልጣኞችን
በAI(Artifical intelligence) ፕሮግራሚንግ
እውቅና እንዲያገኙ ስልጠናዎችን ለማመቻቸት
እየተሞከረ እንደሚገኝ
- እንዲሁም በ2030 ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ለመሆን
የያዙትን ራዕይ ለማሳካት ሁሉም የሚጠበቅበትን
ሀላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በጉብኝቱ በኮሌጁ ውስጥ ያሉ የሪሶርስ ማዕከል፣ የኢንኩቤሽን ማዕከል፣ የዓሳ እርባታ ቴክኖሎጂ ማሳያ ማዕከል፣ የከብትና የዶሮ እርባታ፣ smart class room አደረጃጀትና የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ የማስጀመር ሂደት ምልከታ የተደረባቸው ሲሆን በጉብኝቱ መገባደጃ የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለስ ይግዛው በኮሌጁ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት በአሰልጣኞች መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ገልፀዋል ። ይህንን መነቃቃትና የስራ ባህል ቀጣይነት እንዲኖረው ተቋማዊ እንዲሆን ማስቻል በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም አመላክተዋል ።
በመጨረሻም አቶ ተሾመ ፈይሳ በኤስቴቲክስ የስልጠና ዘርፍ ተመራቂ ሰልጣኞች የተሰሩ የስዕል ስራዎችን ለጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስጦታ አበርክተዋል።
ኮምንኬሽን ክፍል

👍11❤2
ሐሙስ:- ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም
ከተለያዩ ኮሌጆች የመጡ አካላት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት አደረጉ!!
ከተለያዩ ኮሌጆች የመጡ አካላት በዛሬው ዕለት በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄዱ፡፡
በዕለቱ በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የኮምቦልቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት፣ የጎፋ ኢንዱስትሪያል ኮሌጁ ማናጅመንትና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት እና የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኢንዱስትሪ አድቫይዘሪ ቦርድ አባላት ናቸው፡፡
ኮሌጁ አሁን ላይ በአይ ኤስ /ISO/ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ መሆኑ፣ በዲጂታላይዜሽን ስራዎች የላቀ ደረጃ ላይ መገኘቱ፣ በኢነርጂ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል ለመሆን ዘመኑን የዋጀ ግብዓት ማሟላቱ፣ የግቢውን ፋሲሊቲ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በስፋት መታየቱ እና መሰል እንቅስቃሴዎች መኖራቸው ልምዱን ይጋሩ ዘንድ ከቅርብም ከሩቅም ያሉ በርካታ ተቋማት እየጎበኙት ይገኛሉ።
በዛሬው ቀን ጉብኝት ያደረጉ አካላትም የተሰሩ አብየት ፕሮጀክቶችን በምልከታ፣ ልዩ ልዩ ተግባራትን በገለጻ፣ እና የለውጥ አሰራሮችን በውይይት ልምድ ይቀስሙ ዘንድ ተደርጓል።
ባሳለፍነው ሳምንት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጤ ዞን የሚገኙ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ዲኖች እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር ያሉ ኮሌጆች ዲኖች በኮሌጁ ተገኝተው በመጎብኘት ልምድ የወሰዱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ የተቋማቸውን ማናጅመንት እና አካዳሚክ ኮሚሽን አባላት ይዘው በመምጣት ልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍10❤4👌2