ሰኞ፡- ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
ለወጣቶች የስራ ላይ ልምምድ የህይወት ክህሎት ስልጠና መስጠት ተጀመረ፡፡
የስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም ተጠቃሚ ለሚሆኑ ወጣቶች የህይወት ክህሎት ስልጠና ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም መስጠት ተጀመረ፡፡
ኮሌጁ በዚህ ዙር እንዲያሰለጥን ከተሰጠው 740 ሰልጣኞች መካከል 350ዎቹ በዛሬው ዕለት ተገኝተው መጀመራቸው ታውቋል፡፡ በስልጠናው ላይ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 የመጡ ወጣቶች ስልጠናውን መቀላቀላቸው ተገልጿል፡፡
በማስጀመሪያ መድረኩ ላይ ተገኝተው ‹‹ወጣትና ትኩስ አምራች ኃይል እንደመሆናችሁ መጠን አሁን ላይ ለምታገኙት ተራ ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ባገኛችሁት ስልጠና ላይ ተመርኩዛችሁ ነገ ላይ የምታፈሩትን ትልቅ ሀብት ማለም ይገባችኋል›› ያሉት የኮሌጁ ዲን አቶ መለሰ ይግዛው ናቸው፡፡ ዲኑ አክለውም ‹‹የእኛ ኃላፊነት ስልጠናውን በአግባቡ መስጠት ነው፡፡ እናንተም እንደማንኛውም ሰልጣኝ በኮሌጁ በምታደርጉት ቆይታ የሰልጣኝ ዲሲፕሊን ሊኖራችሁ ይገባል፡፡›› ብለዋል፡፡
ወጣቶቹ በቆታቸው መሰረታዊ የህይወት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ፣ የስራ ዝግጁነት ብቃቶችን እንዲጨብጡ እና የህይወት ልምዳቸውን እንዲያጎለብቱ ታልሞ ሲሆን ከ10 ቀናት ስልጠና በኋላ ለ6 ወራት ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ለተግባር ስራ ልምምድ ተብሏል፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍13❤1👏1
ሰኞ፡- ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ ከቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ!!
የጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የቻይናው ሻንሲ ፖሊ ቴክኒክ ኢንስቲትዩት ስልጠናን በትብብር አብሮ ለመስራት የሚያስችል መግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ኃላፊዎች ባለፈው አርብ ታህሳስ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝት እና የስራ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከመግባቢያ ስምምነት መፈራረም ባሻገር የ2 ዓመት የስራ እቅድ በጋራ ማቀድ ተችሏል፡፡
ከዚህ በፊት 11 የቻይና የቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች የመጡ የስራ ሃላፊዎች በኮሌጁ ተገኝተው የወርክ ሾፖች ጉብኝትና የስራ ውይይት መደረጉን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

👍26
ማክሰኞ፡- ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም
የ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ!!
በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2016 ዓ.ም ላይ ለመሰልጠን ያመለከቱ አዲስ ገቢ መደበኛ የቀን ሰልጣኞች ዛሬ ታህሳስ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ስልጠና ጀመሩ፡፡
በዚህ የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ የኮሌጁ ዲኖች በመድረኩ ተገኝተው ለአዳዲስ ሰልጣኞች ስለ ስልጠና አሰጣጡ ሂደት እና በስልጠና ሂደቱ ማድረግ የሚገባቸውን የስልጠና ዲሲፕሊን አስገንዝበዋል፡፡
በዚህ የስልጠና በጀት ዓመት ከ3300 በላይ መደበኛ አዳዲስ ሰልጣኞች በ3ቱም የስልጠና መርሃ ግብራት ለመሰልጠን ያመለከቱ ሲሆን ከባለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በሁለት እጥፍ መጨመሩ ታውቋል፡፡
"በላቀ አገልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍34❤11👏4🏆3