አርብ፡- ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም
ታላቅ የምስራች ነው እንኳን ደስ አላችሁ!!
ኮሌጁ በአይሶ 9001፡2015 የጥራት ማናጅመንት ስርዓት ሰርቲፋይድ ሆነ!!
ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ለ4 ተከታታይ ቀናት ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት በመጡ ኦዲተሮች የጥራት ኦዲት ሲደረግ ቆይቶ አሁን ላይ የጥራት ማናጅመንቱን ስርዓት ማሟላቱ ተገልጿል፡፡
ኮሌጁን በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ ለማስደረግ ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ለ10 ወራት ያህል ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች ስታንዳደርዱን ለማስጠበቅ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡
በዚህ ሁሉን አቀፍ ቅንጅታዊ የስራ ትጋት ኮሌጁ ዓለም አቀፋዊ የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ ይህ ስኬት ኮሌጁ በ2022 ዓ.ም በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለመሆን የሰነቀውን ራዕይ እውን ለማድረግ መንገድ የጠረገ ሂደት ነው፡፡
ይህ እውቅና ይገኝ ዘንድ በተለያየ ደረጃ ላይ የምትገኙ የተቋሙ አመራር አካላት የመሪነታችሁ ሚና የላቀ ነው እና እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የኮሌጃችን አሰልጣኞችና የልዩ ልዩ ዘርፍ ባለሙያዎች ቅንጅታዊ ተሳትፏችሁ እና ያልተቋረጠ ትጋታችሁ ፍሬ አፍርቶ ይህንን ውጤት ለማየት በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡ አሁን ላይ እየሰለጠናችሁ ያላችሁ ሰልጣኞቻችን እና ከዚህ በፊት በተለያዩ ዘመናት በኮሌጃችን በልዩ ልዩ ሙያዎች ሰልጥናችሁ የነበራችሁ ቤተሰቦቻችን ኮሌጃችሁ በዓለም አቀፍ ስታዳርድ መመዘገቡን ስታውቁ የሚሰማችሁ ደስታ ታላቅ እንደሆነ ስለምንገነዘብ እናንተምን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡ በዝርዝር እና በቁጥር ገልፀን የማንጨርሳችሁ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆናችሁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የእናንተ ከፍተኛ አጋርነት ድምር ውጤት ኮሌጃችንን ወደ አንደኛው የስኬት ምዕራፍ እንዲሸጋገር አበርክቷችሁ ከቃላት በላይ ነው እና እናንተም በያላችሁበት አንኳን ደስ አላችሁ፡፡
ኮሌጁ በዚህ የጥራት አመራር ስርዓት ማለፉ የደንበኞቻችንን ፍላጎት ለማርካት፣ የተቋማችንን ገጽታ ለማሳደግ፣ ቀጣይ እና ተከታታይ ለውጥ ለማምጣት፣ የሰራተኞችን ተሳትፍ ይበልጥ ለማጎልበት፣ ስራዎችን አቀናጅቶ ለማስራት እና መረጃን መሰረት ያደረገ ውሳኔ ለመስጠት ያስችለዋል፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"

👍33
ቅዳሜ፡- ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቀቀ!!
ኮሌጁ የ2016 ዓ/ም አዳዲስ ሰልጣኞችን ለመቀበል የሚያበቃውን ሁሉን አቀፍ ቅድመ ዝግጅት አጠናቀቀ፡፡
በሰው ሀብት አቅም ግንባታ ስራ፣ በስልጠና ግብዓት ማሟላት፣ በአደረጃጀት እና በአሰራር ስርዓት መዋቅራዊ ዝግጅት እና በመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሰፊ ተግባራትን በማከናወን ዘመኑን የዋጀ ስልጠና ለመስጠት ግዙፍ ዝግጅት አድርጓል፡፡
ኮሌጁ አሁን ላይ ወደ 2000 የሚጠጉ ነባር ሰልጣኞች ሲኖሩት አጠቃላይ በሶስቱም የስልጠና መርሃ ግብሮች ማለትም በቀን፣ በማታ እና በቅዳሜ እና እሁድ በቀጣይ አዳዲስ ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስልጠን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየደረጃዎቹ የሚያስቀመጥጠውን የመቁረጫ ነጥብ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡
በኮሌጁ ስልጠና የሚሰጥባቸው የዲፓርትመንት ብዛት 12 ሲሆኑ የሙያ ዘርፎቹ ደግሞ 48 ናቸው፡፡ በአይሶ 9001፡2015 የጥራት አመራር ስርዓት ሰርቲፋይድ የሆነውን ኮሌጃችንን ፈጥናችሁ ለመቀላቀል በጉጉት እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ በርካታ አዳዲስ አመልካቾች እንዳላችሁ እንገነዘባለን፡፡ በእርግጥም ምርጫችሁ ትክክለኛ ቦታ ነው፡፡ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ፖሊ ቴክኒክ ለመሆን ራዕይን አንግቦ እየተጋ ያለ አንጋፋ የስልጠና ተቋም ነው፡፡
ውድ ደንበኞቻችን እኛም እናንተን ተቀብለን ምርጫችሁን መሰረት ያደረገ ሙያዊ ስልጠና ለመስጠት የምንጠብቀው የስልጠና መቁረጫ ነጥቡን የመጀመሪያ ደወል ነውና ወቅታዊ መረጃዎቻችንን በቻናሎቻችን ሁል ጊዜ ይከታተል፤ የመረጃ ማድረሻ ገጾቻችንንም ለሌሎች በማሳወቅ እንዲቀላቀሉ አድርጉ፡፡

👍56
ሰኞ፡- ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም
ኮሌጁ ከትራንዚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ!!
ኮሌጁ የተለያዩ የሞባይል ዓይነቶች እና የሞባይል አክሰሰሪዎችን እያመረተ ከሚገኘው ትራንዚሽን ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት ሰነድ ባለፈው ሳምንት ተፈራረመ፡፡
ትራንዚሽን ማኑፋክቸሪንግ እንደ TECNO, itel and Infinix ያሉ ሞባይሎችን እያመረተ የሚገኝ ዓለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን በኮሌጁ ለሚገኘው የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት የስልጠና ዘርፍን ውጤታማ ለማድረግ ታቅዶ የተተገበረ ነው፡፡ በዚህ ስምምነት የኮሌጁ አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ተግባራዊ ስልጠና ለማግኘት እና ለተመራቂ ሰልጣኞች የስራ እድል ለመፍጠር ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ከድርጅቱ የመጡት የስራ ኃላፊዎች ከስምምነቱ ባሻገር በኮሌጁ ውስጥ በአዲስ ግብዓት የተደራጀውን የኤሌክትሪካል ኤሌክትሮኒክስ ዲፓርትመንት ወርክሾችን ጎብኝተዋል፡፡ ስምምነቱን የተፈራረሙት የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ መለሰ ይግዛው እና የድርጅቱ የሰው ሃብት ማናጀር ወ/ሮ ዓለምፀሐይ ንጉሴ ናቸው፡፡
ዲፓርትመንቱ በምስራቅ አፍሪካ የልህቀት ማዕከል እንዲሆን በዓለም ባንክ በኩል በርካታ መዋዕለ ነዋይ ተበርክቶለት ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ በተለያየ ጊዜ መዘገባችን ይታወሳል።

👍24❤1
ረቡዕ፡- ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም
የቴክኒክና ሙያ የመግቢያ ነጥብ ይፋ ተደረገ።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በ2016 ዓ.ም ወደ ቲክኒክና ሙያ መግቢያ ነጥብ ይፋ አድርጓል።
ሚኒስቴሩ የመግቢያ ነጥቡን ይፋ ያደረገው ዛሬ ረቡዕ ኅዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን መግለጫውን የሰጡት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ናቸው። በዚህም የተፈጥሮ ሳይንስ ለደረጃ 5 የመቁረጫ ነጥብ ወንድ ከ218፣ ሴት 199 በላይ፣ የታዳጊ ክልል (የአርብቶ አደር አካባቢዎች) ወንድ ከ192፣ ሴት 187 በላይ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ (ሁሉንም ክልሎች ታሳቢ ያደረገ ነው) ብለዋል።
ደረጃ 3 እና 4 ወንድ ከ173፣ ሴት 163 በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ ከ157፣ ሴት 156 በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ነው ተብሏል።
ተፈጥሮ ሳይንስ ደረጃ 1 እና 2 ወንድ 172፣ ሴት 162ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 156፣ ሴት 155ና ከዚያ በላይ ነው።
ማኅበራዊ ሳይንስ ለደረጃ 5 ወንድ 179፣ ሴት 170ና ከዚያ በላይ፣ ታዳጊ ክልሎች ወንድ 166፣ ሴት 162፣ አካል ጉዳተኞች 147ና ከዚያ በላይ ነው።
ደረጃ 3 እና 4 በማኅበራዊ ሳንይንስ ወንድ 149፣ ሴት 147፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 138፣ ሴት 137ና ከዚያ በላይ፣ አካል ጉዳተኞች 130ና ከዚያ በላይ ሆኗል።
ደረጃ 1 እና 2 በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 148፣ 146፣ ታዳጊ ክልል ወንድ 137፣ ሴት 136፣ አካል ጉዳተኞች 129ና ከዚያ በላይ መሆኑን አስረድተዋል።
ሚኒስትሯ አክለውም፣ "በ2016 ዓ.ም 844 ሺሕ 384 የሚሆኑ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ወስደዋል። ከእነዚህ ውስጥ በእኛ ምልከታ 632 ሺሕ 587 የሚሆኑት ወደ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ይመጣሉ የሚል ግምት አለን" ነው ያሉት።
የሰው ሃይል ለመቀበል የተሻለ ዝግጁነት አላቸው ያልናቸውኝ የመንግሥትና የግል የቴኪኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማትን ፈትሸናል ያሉት ሚኒስትሯ፣ እስካሁን ባለው ከ28 ሺህ በላይ የሚሆኑ አሰልጣኞች፣ ወደ 1ሺሕ 400 ገደማ የተሻለ ብቃት ያላቸው ማሰልጠኛ ኮሌጆች አሉ ብለዋል።
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
Credit: መረጃውን ሰማሁ ብሎ እወቁልኝ ያለው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው።

👍28
ሐሙስ፥- ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ∙ም
በዚህ ዓመት በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊስ መሠረት እስከ ደረጃ 6 ቅበላ ይደረጋል ተባለ!!
ከባለፈው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው አዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ መሰረት ከዚህ ቀደም እስከ ደረጃ 5 ብቻ ተገድቦ የነበረው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የእድገት መሰላል እስከ ደረጃ 8 ድረስ እንዲሆን መደረጉ ይታወሳል፡፡
ይህም ፖሊሲው ደረጃ ስድስትን ከመጀመሪያ ድግሪ፣ ደረጃ ሰባትን ከማስተርስ እንዲሁም ደረጃ ስምንትን ከዶክትሬት ዲግሪ /PhD/ ጋር ትይዩ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ስለሆነም በዚህ ዓመት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎች ወደ ቴክኒክና ሙያ መግባት ቢፈልጉ በደረጃ 6 ገብተው መሰልጠን እንደሚያስችላቸው ተመላክቷል፡፡
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ በደረጃ 6 የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች እንደሚስተናገዱ የጠቆሙት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያት ካሚል ሲሆኑ በዚህ ዓመት በተቀመጠው መስፈርት መሰረት በክልሎች አማካኝነት የሰልጣኞች ምደባ ይካሄዳል ብለዋል፡፡
በዚህም በተያዘው የሥልጠና ዘመን 632 ሺህ በላይ ተማሪዎች የሥራ ገበያውን የሰው ሀይል ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ከደረጃ 1-ደረጃ 5 እንደ ውጤታቸው ተመድበው እንደሚሰለጥኑም ነው ክብርት ሚኒስትሯ የገለጹት፡፡
በወጣው መቁረጫ ነጥብ መሰረትም ደረጃ አንድ እና ሁለት 110,015 ፤ በደረጃ ሦሰት እና አራት 412,557 እንዲሁም በደረጃ አምስት 110,015 እንደሚሳተፉ የጠቆሙት ክብርት ሚኒስትር በደረጃ ስድስት ደግሞ 2000 የሚሆኑ ሰልጣኞችን ለቀመበል ዝግጅት መደረጉን አመላክተዋል፡፡
የ2016 የስልጠና ዘመን የተዘጋጀው መቁረጫ ነጥብ የ2015 ትምህርት እና የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12 ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
ከ2014 ዓ.ም በፊት ለነበሩ የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ደግሞ በስልጠና ዘመኑ በነበረው መቁረጫ ነጥብ መሰረት ይስተናገዳሉ፡፡
"በላቀ አግልግሎት የመረጃ ተደራሽነት"
Credit: መረጃውን እወቁልኝ ብሎ በማኀበራዊ ትስስር ገጹ ያጋራው የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።

👍24