የቶኪቻው ሙዚቃ በሲዳማ ክልል በየትኛውም አከባቢ እንዳይከፈት የሲዳማ ክልል መንግስት ትዕዛዝ መስጠቱ ተሰማ
አርቲስት ቶኪቻው(ዮሐንስ በቀለ) በሲዳማ ክልል የተንሰራፋውን የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የተደራጀ ሌብነት፣ የሙስና ቅሌት እንዲሁም አፈና በተመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ጠንከር ያለ ትችት በተከታታይነት መሰንዘሩን ተከትሎ የክልሉ መንግስት ትችቱን መቋቋም ተስኖት በገፅታ ስራ ላይ ተጠምዷል የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች ተበራክተዋል።
የዘንድሮው የሲዳማ ብሐረ ዘመን መለወጫ ፍቼ ጨምበላላ ላይ የአርትስቱ ሙዝቃ እንዳይከፈት የክልሉ ፕሬዘዳንት አቶ ደስታ ሌዳሞ ትዕዛዝ መስጠቱንና ትዕዛዙም ሀዋሳ ከተማ ጨምሮ ለሎች አከባቢዎችም ተግበራዊ እየሆነ እንደሆነ የማለዳ ምጮች አንስተዋል።
ሚዲያችን ያነጋገራቸው የሀዋሳ ከተማ ንግድ ተቋማት የአርቲስቱ ሙዚቃ እንዳይከፍቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ ጭምር እንደተነገራቸውና የሚከተላቸው ቅጣት በመስጋት የቶኪቻውን ዘፈን ከመክፈት መቆጠባቸውን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል በሀዋሳ ከተማ በክልሉ መንግስት ሴራ በደበዘዘው የፍቼ ጨምበላላ በዓል ዋዜማ ላይ የመንግሥት ሹመኞች በየክፍለ ከተማ ድንኳን በመትከል ትዕይንት በሚያሳዩበት መርሃግብር ላይ አንድም ቦታ የአርቲስቱ መዚቃ ሳይሰማ መዋሉን ከየአከባቢው ማህበረሰብ ለሚድያችን የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #tokichaw