Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
በ2024 የ አፍሪካ ኢንተርቴይመንት ሽልማት በ አሜሪካ ድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ የአመቱ ምርጥ ሴት አርቲስት በሚል ዘርፍ ታጭታለች።

በዚህ ዘርፍ  እጩዎች
- Spice Dianna
- Haidy Mousa
- Kiin Jamac
- Hewan Gebrewold
- DJ Uncle Waffles
- Nandy
- Nadia Mukami
- Kenza Morsli
- Mampi
- Feli Nandi

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - http://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #hewan_gebrewold
የራስን ህመም ደብቆ ለሌላው ድህሎት መመኘት በጉዳት ውስጥ ሌላን የማፍቀር ጥበብ ይገለጣል ስሜቶቹ በሙሉ የሚሄዱበት አቅጣጫ ለየቅል መስሎ መዳረሻው ግን አንድ ይሆናል፡፡ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ዜማ አንተነህ ወራሽ ቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) የሙዚቃ ስልቱ ዋልዝ የተረጋጋ ቀልብን ሰብሰብ የሚያደርግ ነው፡፡

#ሔዋን

"ያጣሁት ያን ጎብል የገፋኝ ወጣቱ
ከፍቶ አይደለም በኔ ነው በልጅነቱ
ዞር በይ ዞር በይ ያለኝ የገፋኝ ከቤቱ
ማደጉን ፈርቶ ነው ወዶ ልጅነቱ"

ይህ የሙዚቃ ክር ሁለት ነገሮችን ተሸክሟል የመጀመርያው በአልበም ደረጃ የኔ ያለችውን በስሟ ሰይማ መምጣትዋ ነው ፡፡ ሁለተኛው 1830 ዓ.ም በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት በጉራጌ ብሔረሰብ ትልቅ ገድል የፈፀመችሁ "ቃቄ ውርዶት" በሴቶችን ላይ የሚፈፀመው ጭቆና እና ግፍ ነፃ ያወጣች ድንቅ ሴት እሷን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ እንደሆነም ድምፃዊቷ ገልፃለች፡፡ የሙዚቃው ገጣሚ ዮሐና አሸናፊ ዜማ ሄዋን ገብረ ወልድ ቅንብር ዲጄ ሚላ በጉራጌ ቢት ከሽኖ ሰርቶታል፡፡

#ያምራል #ልጁ

ስመኝ ኖሬ እንኳን ስመኝ
በዓመት በዓል አገጣጥመኝ

ይህ ሙዚቃ ክር አንድን በህላዊ ስሜትን ይዞ አመት በአልን የሚያስታውስ ትውስታ ይዞ የመጣ ሲሆን የድምፃዊትን አስናቀች ወርቁን የሚያስታውስ የሙዚቃ ቅንብር አሰምታናለች የሙዚቃ መግቢያ እንደ እየሩስአሌም የተሰኘ የሙዚቃ ቅንብር ቅንጭቡን ወስደዋል፡፡ አንድም ታሪክን ለመግለፅ ባህላዊ የሙዚቃ ስልት ማስተዋወቅን የያዘ ነው፡፡ ግጥም ወንደሰን ይሁብ ዜማ አንተነህ ወራሽ ቅንብር ዲጄ ሚላ፡፡

በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን ታሪካዊ አልበም ላይ ተሳትፈዋል፡፡ አብዛኛውን ግጥም በናትናኤል ግርማቸው የተሰሩ ሲሆን በቅንብሩ በኩል ዲጄ ሚላ አብዛውን ሰርቷል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በቅንብሩ ዲጄ ሚላ ፣አቤል ጳውሎስ ፣ ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ ተቀባ እና ታምሩ አማረ (ቶሚ) ተሳትፈዋል፡፡ በግጥም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ዮሐና ፣ ምረት አብደስታ ፣ ሄዋን ገብረወልድ ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ ወንደሰን ይሁብ ፣ ይልማ ገብረዓብ ፣  በማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ ናቸው፡፡

ሁለተኛ አልበምሽን እንድንጠብቅ አድርጎናል፡፡ ስለ ሰጣችሁን ይንን የመሰለ አልበም እናመሰግናችኃለን፡፡

የሙዚቃ ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #hewan