የ Alemayehu Demeke ን ሀቅ ሊቀማም ይችላል?
የግጥም እና ዜማ ዓለማየሁ ደመቀ ወደ ሙዚቃ የመጣበትን 25ኛ ዓመት እና የ " ዮቶር ፪ " መጽሐፍን ሕትመት ምክንያት በማድረግ ሰኔ 15/16 በማርዮት ሆቴል ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት መዘጋጀቱ ይታወቃል ። ይኸው ኮንሰርት የተካሄደው ( በደብዳቤው እንደተገለጸው )በይገረም ስንታየሁ ( ዲጄ ቤቢ ) ድርጅት " አዲስ ሚዩዚክ መልቲ ሚዲያ " ነበረ ። በዕለቱ ከስፖንሰር እና ከቲኬት ገቢ የተሰበሰበው ገንዘብ ለባለመብቱ ሊሰጥ ሲገባ እስካሁን የውሀ ሽታ ሆኖ ቀርቷል ።
የዝግጅት ኮሚቴው ሰብሳቢ ተስፋዬ አለነ ( ዶ/ር ) " ይህ እንዳይሆን ነበረ ለ10 ወራት የለመንነው " ሲል እንደገለጸው በመጨረሻ ላይ ይህን ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደዋል ። የማንም ሀቅ መቀማት የለበትም ። ግን እንዴት ሰው ከዓለማየሁ ደመቀ ላይ ይህን ሊያደርግ ይችላል ? ምኑ ነው 10 ወራት የሚያመላልስ ? ዓለማየሁ ደመቀ ላለፉት 25 ዓመታት በሚያውቁት ዘንድ የከበረ ስም ያለው ነው ። " ዮቶር " ን የጻፈ ነው ። ለድርሰት ሳይሆን ለሕይወት የሚጽፍ ደራሲ ነው ። ዲጄው ወደ አሜሪካ ሄዷል ። እዚህ መጥቶም ሆነ እዚያው ባለበት አፋጣኝ ምላሽ ይሰጣል ብለን እንጠብቃለን ።
ለሁሉም ሚዲያ አካላት ግልባጭ ተደርጓል ።
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #alemayehu_demeke