Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
“የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ ስራዎችን የሚመርጥ እና የሚያሰባስብ ኮሚቴ ተዋቅሯል"
አቻሬ(የድምፃዊው የቅርብ ወዳጅ)

የተወዳጁ ድምፃዊ የማዲንጎ አፈወርቅ አዲስ አልበም በመሰራት ላይ እንደሚገኝ ተነገሯል::

ድምፃዊው በሕይወት ሳለ የሰራቸውን የሙዚቃ ስራዎች የመምረጥ እና የማሰባሰብ ስራን የሚያከናውኑ ኮሚቴዎች መዋቀራቸውን የድምፃዊው ወዳጅ ቸርነት አሸናፊ (አቻሬ ጫማ) ተናግሯል።

በእዚህ ኮሚቴ ውስጥም አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ ዘዓለም መኩሪያ፣ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎን ጨምሮ የማዲንጎ አፈወርቅ ቤተሰቦች እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።

በእዚሁ አልበም ስራ ላይም እስከ 10 የሚደርሱ የሙዚቃ ስራዎች እንደሚካተቱም ቸርነት አሸናፊ (አቻሬ) አንስቷል።

በግጥምና ዜማ ሂደት ውስጥ ከእዚህ ቀደም ከድምፃዊው ጋር የሰሩ ባለሙያዎች እንዳሉበት የተናገረው አቻሬ የባለሞያዎቹን ስም ዝርዝር ከመጥቀስ ተቆጥቧል::

በሌላ በኩል ደግሞ ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከድምፃዊው የቅርብ ምንጮች ባደረገው ማጣራት የአልበም ስራው ከ50 እስከ 60 በመቶ ሊጠናቀቅ ችሏል።

ከእዚህ ቀደም የክቡር ዶ/ር ጥላሁን ገሰሰ ፣ የድምፃዊ እዮብ መኮንን፣ ሚካያ በሀይሉ እና ሀጫሉ ሁንዴሳ የአልበም ስራዎች ከህልፈተ ሕይወታቸው በኋላ ለሙዚቃ አፍቃሪያን እንደደረሱ ይታወሳል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Madingo
የተወዳጁ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙ ከምን ደረሰ?

ብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን እና አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ የመጨረሻ አልበሙን እየሰራ በሚገኝበት ሰአት ላይ በህመም ምክንያት ማረፉ ቢታወቅም አጅናቂዎቹና የሙያ አጋሮቹ አልበሙን ከጥግ ሊያደርሱት ቃል መግባታቸው የሚታወስ ነው። ነገር ግን የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ እህት የሆነችው ድምፃዊ ትግስት አፈወርቅ ለታዲያስ አዲስ እንደገለፀችው የዜማ እና የግጥም ደራሲ የሆነው ዘላለም መኩሪያ ማዲንጎ በድምፅ ሙሉ በሙሉ ገብቶ ያልጨረሰውን ስራ ከማዲንጎ ድምፅ ጋር የሚመሳሰል አንድ ድምፃዊ ድምፁን በመቅዳት የማዲንጎ ስራ አስመስሎ ለመሸጥ እየሰራ እንደሆነ ቤተሰቦቹ በጭራሽ ይሄን ነገር እንደማይቀበሉትም ተናግራለች።

አልበሙን በዋናነት እየሰሩ የሚገኙት ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ እና ዘላለም መኩሪያ ሲሆኑ ለዚህ ጥያቄ ዘላለም መኩሪያ ስራችውን የጀመሩት በየስቱዲዬው ያሉትን ስራዎች በማሰባሰብ ሲሆን ስራዎቹ አሁን ላይ ያሉት የመለማመጃ ወይም Sample ብቻ እንደሆኑ ሌሎች ድምፃዊያንንም የማስገባቱ ስራ ለሙከራ ያህል የተደረገ እሱንም በሃሳብ ደረጃ የተተወ መሆኑን ገልጿል።

አያይዞም አሁን አልበሙ የማሰባሰብ የመምረጥ እና እንዴት አድርጎ የመለማመጃ ድምፁን ወደ አሪፍ ሙዚቃ መቀየር ይቻላል የሚለውን ገና የማሰብ ደረጃ ላይ እንደሆነ የሚወጣበትም ቀን ያልተወሰነ መሆኑን ገልፀዋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music  #Madingo_afewerk
2 ዓመት

ድምፃዊ ማዲንጎን ካጣነው ዛሬ ድፍን 2 ዓመት ሞላ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #madingo
ተወዳጇ ድምጻዊት ትዕግስት አፈወርቅ በሞት ባጣነው ወንድሟ ተወዳጁ ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ስም 100 ሺህ ብር የለገሰች ሲሆን አንዲሁም በየአመቱ የድምጻዊውን ሙት አመት በማስመልከት 100 ሺህ ብር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብታለች፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #madingo #tigist