Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የግርማ ተፈራ አልበም ምርቃት ዛሬ ይካሄዳል።

በቅርብ ከወጡት አልበም ውስጥ በጣም ተወዳጅንን ካገኙት አንዱ የሆነው የግርማ ተፈራ አልበም ዛሬ፣ ቅዳሜ ምሽት በማርዮት ሆቴል ሊመረቅ ነው።

በዝግጅቱም ላይ እራሱ ግርማ ተፈራን ጨምሮ ፀሃዬ ዬሃንስ፣አብዱ ኪያር፣ዳዊት ፅጌ፣ኒና ግርማ እንዲሁም ወንድሙ መሳይ ተፈራም የራሳቸውን ስራ የሚያቀርቡ ይሆናል።

አዘጋጆቹ እንደገለፁት መግቢያ ብር 2,500.00 ሲሆን በነፃ ደግሞ የአልበሙ ሲዲም እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ግርማ ተፈራ ካሳ - የአባቱ ልጅ ።
Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#waliya_entertainment #Girma_tefera
የግርማ ተፈራ የአልበም ምርቃት ዝግጅት በጥሩ ሁኔታ ተጠናቀቀ።

ከትናንት ወዲያ በተካሄደው የግርማ ተፈራ ግን የትሐገር? የሚለው የአልበም ምርቃት ዝግጅቱ በ ማሪዬት ሆቴል በአሪፍ ሁኔታ መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን።

ይህንንም አስመልክቶ ድምፃዊ ግርማ ተፈራ ካሣ በ ሶሻል ሚዲያ ገፁ ላይ በዝግጅቱ ላይ ለተሳተፉት ሁላ ምስጋና አቅርቧል።

   "በትላንትናው ዕለት ማለትም ቅዳሜ ህዳር 15 በማሪዮት በተደረገው የ "ግን የት ሀገር" አልበም ምርቃት ላይ በመገኘት አክብሮታችሁን ላሳያችሁኝ አድናቂዎቼ እጅግ ዝቅ ብዬ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ደረጃውን የጠበቀ ሙዚቃ በማቅረብ ከተሰራ አይቀር እንደዚህ ነው ያስባለ ብቃት ላሳዩት ብቁ ሙዚቀኞችን እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ። ለጆሮ የሚጥም የተዋሀደ ድምፅ ላሰማን (Sound Man) ሲሳይ ምስጋናዬ ይድረስህ። ምሽቱ ልዩ እንዲሆን ከጎኔ በመሆን ከፍ ላደረጋችሁኝ የሙያ ጓደኞቼ ፀሐይ ዮሐንስ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ፣ፍቅርዓዲስ ነቅዓጥበብ፣አብዱ ኪያር፣ዳዊት ፅጌ፣ ኒና ግርማ፣ሚካኤል በላይነህ፣ ሄኖክ አበበ፣መሳይ ተፈራ፣ተአምር ግዛውና አሸናፊ ለገሰ አመሰግናለሁ የሚለው የምስጋና ቃል ቢያንስብኝም ማለት የምችለው እሱን ነውና ከልቤ አመሰግናለሁ።

መድረኩን ለመራልኝ ከጓደኛ አልፎ ወንድሜ ለሆነው  ታምሩ ብርሃኑና ለዲጄ ዊሽ ምስጋናዬ ይድረሳችሀ።"

ሲል የምስጋና መልእክቱን አስተላልፏል።

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#waliya_entertainment #Girma_tefera
🥰1
የግርማ ተፈራ ካሳ የአልበም ምርቃት በፎቶ።

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#waliya_entertainment #Girma_tefera
👍1