Waliya Entertainment
296 subscribers
1.57K photos
15 videos
758 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
👉 «አልበም እፈልጋለሁ ግን እንዴት ነው የሚሰራው?  ሲል ጠየቀኝ። ከአይድል የሚመጡ ብዙዎቹ  ዘፋኞች የሚጠይቁት ጥያቄ ነው።አንተ አትጨነቅ እየሞከርን እናየዋለን ብዬ አልጣሽ አልበም ጥንስሱ ተጀመረ፡፡»

👉« በስሟ እየማልኩ የተሰኘውን ሙዚቃ የሰራነዉ ማንጁስ ብዙ ጊዜ  አሚና ትሙት እያለ ሲምል ሰማቼ የሰራሁት ነው።አሚና እናቱ መስላ ነበር  የታየችኝ ነገር ግን ኮምቦልቻ ለስራ ስንሄድ እህቱ እንደሆነች ነገረኝ ።የዚህ ሙዚቃ መነሻ ይህ ነው፡፡»

👉 «አልጣሽ ሙዚቃ ለዳዊት ፅጌ የተሰራ ዜማ ነበር።ጎሳዬም ድንገት ደውሎልኝ  ይህን ዜማ ሰምቶት ወዶት ነበር።በአጋጣሚ ማንጁስ ከኮምቦልቻ መልስ ሞባይሌ ውስጥ ለማሳያ(ሳምፕል) ከተቀረፁ  ዜማዎች ውስጥ አልጣሽን ሰምቶ ወደደው እና ተሰራ፡፡»

👉 «ከግጥምና ዜማ ደራሲው ይልማ ገ/አብ ጋር በተለያዩ አጋጣሚዎች አብረን ሰርተናል። አሁንም እየሰራን ነው።ለይልማ ዜማ መስጠት አቅቶን ይሆናል እንጂ ዜማ ሰተህው ብዕሩ የሰላ አይደል? በዚህ እድሜው ያለዉ ብስለት ያስገርማል፤ እኔ እንደውም እችላለሁ ወይ ለእሱ የሚመጥን ስራ ብዬ እጨነቃለሁ፤''አልጣሽን፤በስሟ እየማልኩ''ን ጨምረን ሰጠነው ከይልማ ጋር መስራት መባረክ ነው፡፡»

👉 «የፍቅር አዲስ  አልበም እየተዘጋጀ ነው። አዲስ ሁላችንንም ምሳ አብላታ ተንከባክባ፤ይቅናችሁ ብላ፤ለስራ ምቹ ሁኔታ ፈጥራ የተሳኩ ስራዎች እንዲሰሩ ታግዘናለች፤ከራሷ ስራ በላይ፤የምታርመው እርማት፤የምትሰጠው አስተያየት ጠብ አይልም።»

አበበ ብርሀኔ በብዙዎች የሚባለውን ''አመለሸጋነት፤ትሁት፤ሩህሩህ'' መሆንህ መነሻው ምን ይሆን?  ተብሎ ሲጠየቅ ይህን በሏል፡፡

👉« ዜማ ማለት በጣም ረቂቅ ነገር ነው፤ ከወጣ በኃላ ዝም ብለን ስንሰማው ያለው ስሜት ነዉ እንጂ ያንን ዜማ ለማምጣት የተደረገው ጎንበስ ቀናን ልነግርህ አልችም እና ለዜማ ፣ለቅኔ ቤት ዝቅ ማለት ተገቢ ነው።እንደዛ ካልሆነ ዜማውን አታገኝም፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Ahmedmanjus #abebebirhane