መልካም ልደት ለኤፍሬም ታምሩ
(ዮናስ ታምሩ ገብሬ)
#Waliya_Entertainment : ኤፍሬም ታምሩ 1973 ዓ.ም እስከ ዛሬ ድረስ ጾታዊ ፍቅርን፣ የአገር ፍቅርን፣ ናፍቆትን፣ ይቅርታን፣ ትዝትብን፣ ሰውኛ ባሕሪን…ወዘተ. አስመልክቶ በርካታ ሥራዎችን ሰርቷል፤ በቤቴ ቀን በቀን የኤፍሬም ልደት ነው፤
ሙዚቃን ሀ ብሎ ያስጀመረው አያሌው መስፍን ነው፤ ኤፊ ‹‹ገና ልጅ ነኝ ጋሜ›› የሚል ዘፈን አለው፤ ገና ልጅ ነኝ ጋሜ፣ ለአቅመ አዳም አልደረስኩ አላውቅም ታምሜ የሚል፤ መጀመሪያዎቹ አካባቢ ላይ የተዘፈነ፤ ከአንድ ሁነኛ ሰው እንደሰማሁት፣ እነ ሙሉቀን መለሠ ዋሊያ ሙዚቃ ቤት ሲያገኙት ‹‹ፍቅር አልጀመርሽ፣ ልጅ ነሽ እንዴ?›› እያሉ ያበሽቁት ነበር አሉ፤
ኤፍሬም በ‹‹ገና ልጅ ነኝ ጋሜ›› (1973)፣ ‹‹ጀማዬ ነይ››(1974)፣ ‹‹ሸግዬ›› (1975)፣ እና ‹‹ነዪልኝ›› (1976) አልበሞች ተወዳጅነትን አገኘ፤ እንዲህ እንዲህ እያለ 11 (ከሪምክስ ጋር) አልበሞችን ለአድማጭ አድርሷል፤ በድርሰት ረገድ ከአንጋፋዎቹ ከአያሌው መስፍን፣ ይልማ ገ/አብ፣ አበበ መለሠ፣ አክሊሉ ሥዩም፣ አበበ ብርሃኔ፣ ሞገስ ተካ፣ ጸጋዬ ደቦጭ፤ ብሎም ከወጣቶቹ ከመሠለ ጌታሁን፣ ቴዲ አፍሮ፣ አማኑኤል ይልማ፣ እንዳለ አድምቄ እና ሌሎችም ጋር ሠርቷል፤ ሮሃ ባንድ፣ ኢትዮ ስታር ባንድ እና ሌሎችም አብሮ የተጫወታቸው ባንዶች ናቸው፤
#ስጠቀልል፣ ‹‹አካሌ›› አመለ ሸጋ እና ተናፋቂ እንስትን የተዋወቅንበት ዘፈን ነው፡፡ ያ-ነኹላላ አፍቃሪ፣ ውበቷ ልቡን ሞልቶት ለውርርድ ሲበቃ እናስተውላለን፡፡ ይህቺን የመሰልሽ ሴት ከወዴት አለሽ!?
መልካም ልደት!!
Via Michael Aschenaki
Follow us on telegram
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt