ይድረስ ለድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ (ሔዋን አልበም)
(ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
ወደ ኃላ ትውስታ አልበም ላስቃኛችሁ በዛውም ሁለተኛ አልበምዋ እንዲናፈቅ ያደረጉኝ ምክንያቶችን ነግራችኃለሁ፡፡ ይህ አልበም እንደ ተሰራው ልክ ያልተደመጠ ለድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ የምንጊዜም ማስተርፒስ የሆነ አልበም፡፡ እኔ በግሌ ይህ አልበም ከጥግ እስከ ጥግ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ አልበም ነው ባይ ነኝ፡፡
ሄዋን ገብረወልድ "ሄዋን'' አልበም በስሟ የሰየመችሁ የበኩር አልበሟን የዛሬ ሶስት አመት ገደማ እለተ ሐሙስ ግንቦት 25/2014 ነበር የተለቀቀው በዚህ አልበምዋ በውስጡ 11 ክሮች የያዘ ሲሆን ምን ይጠቅምሀል ፣ ሄዋን ፣ እንደኔ እንደኔ ፣ ሙነይ፣ ትፈለጋለህ ፣ ሼሙና ፣ አለም ፣ አስብበት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ በዛ ያሉ ስልተ ምቶች የተቃኙበት ሲሆን የሙዚቃ ጣዕም(ቴስት) እንድናጣጥመው ይረድቶናል፡፡ ሲ ሂፕሆፕ ፣ አፍሮ ቢት፣ ውሎ ቢት ፣ ዋልዝ ፣ ሬጌ-ሮክ ፣ አር ኤንቢ እና የመሳሰሉት ተሰርተዋል፡፡ ከሁሉም የደነቀኝ የፈጣራ ችሎታዋ እና ቫልዩ አድ(ከነበረው ዘፈን ላይ ፈጠራዊ ጭመራ) ማድረጓ ነው፡፡ በተጨማሪም ስሜቶች በአልበሙ ተንፀባርቀዋል ፍቅርን፣ ታሪክን፣የውስጥ ህመምን ፣መወደድን፣አብሮነትን፣መተሳሰብን ፣ ትውስታን ፣ ትዝታ ፣እነዚህን እና የመሳሰሉት ተንፀባርቀዋል፡፡እስኪየተወሰኑትን እንመልከት
#ምን ይጠቅምሀል…
"ሸርተት አለ ጎኔም ከዳው
ጎዳኝ መምሰል እንዳልተጎዳው
ሸፋፈንኩት እየተቀጣው
አንተን ላተርፍ ብዬ እኔን አጣው"፡፡