Waliya Entertainment
289 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ታሜ እንደዋዛ 6 ዓመት ሞላው

የዛሬ 6 ዓመት በዚች ቀንና በዚች ስአት ነበር ድምፃዊ ታምራት ደስታ ከዚህ አለም በሞት የተለየን:: ድምፃዊ ታምራት ደስታ ቀኑ ረቡዕ እለት ሚያዚያ 10 ቀን 2010 ዓ.ም ነበር ። ታሜ በተወለደ በሰላሳ ዘጠኝ (39) አመቱ በህክምና ስህተት ከዚህ አለም በሞት የተለየው:: ታሜ ሃያ አንድ (21) አመታት በቆየበት ስኬታማ የሙዚቃ ታሪኩ አራት (4) ያህል አልበሞችን እና ከዘጠኝ (9) ያላነሱ ነጠላ ዜማዎችን አበርክቷል::

የምንጊዜም ምርጡ ድምጻዊ ታምራት ደስታ ከድምጻዊነቱ ባሻገር ቤተሰቡን (ልጆቹን) አክባሪ ማህበራዊ ህይወትን የሚያውቅ: ቁም ነገረኛ እና አስተዋይ ነበር::ታምራት ለብዙዎቻችን አረፈ እንጂ አልሞተም ዘመን በማይሽራቸው ተወዳጅ ስራዎቹ ሁሌም ሲታወስ ይኖራል::ነፍስህን ከደጋጎቹ ያድርግልን ታሜ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
መልካም ልደት ዲጄ ቤቢ🎉

በተለያዩ የመድረክ ፣ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች የምናውቀው እንዲሁም የአዲስ ሙዚክ የሬዲዮ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው ዲጄ ቤቢ ዛሬ ልደቱ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዝክረ ጥላሁን ገሠሠ
፨ ፨ ፨ ፨ ፨
በዛሬው ዕለት ታሪክ ሲወሳ ሚያዚያ 11 : 2001 ክቡር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየበት ቀን ነበር፡፡

በወሊሶ ከተማ መስከረም 17 ቀን 1933 ዓም የተወለደው ጥላሁን ገሠሠ በ1949 በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ ተቀጥሮ መስራት ጀመረ ፡፡
ከ1950ዎቹ የመጀመሪያ ዓመታት እስከ 1960ዎቹ አጋማሽ ድረስ በክብር ዘበኛ ኦርኬስትራ አጃቢነት አያሌ ድንቅ ዘፈኖችን በመጫወት እውቅናን አትርፏል ።

ያልዘፈነበት ጉዳይ የለም የሚባልለት ጥላሁን ገሠሠ ድንበር የማይገድበው ፍቅር፣ የሀገር ክብር ገላጭ እንዲሁም መካሪ ስራዎቹ ለዚህ ተጠቃሽ እንደሆኑ ይነገራል ።

ጥላሁን በሚያዘያ ወር 1985 አንገቱ ላይ በስለት የመወጋት አደጋ ደርሶበት እንደነበር ነገር ግን ይህ በድምጻዊነት ከመቀጠል አላገደውም ።

በኢትዮጵያ የዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ደማቅ ታሪክን ያሳለፈ፣ ትውልድ ተሻጋሪ፣ ተደማጭ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎችን ያበረከተው ድምጻዊ የክቡር ዶክተር አርቲስት ጥላሁን ገሠሠ በተወለደ በ68 አመቱ በዛሬው ዕለት ማለፋን ታሪክ ይዘክራል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምጻዊ ሳሚ ዳን ዘመናዊ የሙዚቃ ስቱዲዮ ገነባሁ አለ::

በሬጌ ሙዚቃ ተጫዋችነቱ የሚታወቀው ሳሚ ዳን ስቱዲዮ አስገንብቶ ወደ ስራ መግባቱን አሳውቋል።

ድምፃዊው የስቱዲዮና የቪዲዮ ቀረፃዎችን ማድረግ የሚያስችል ሩፍታፕ ሚውዚክ ሲል የሰየመውን ስቱዲዮ ግንባታውን አጠናቅቆ ማስመረቁን ገልጿል።

ድምፃዊ ሳሚ ዳን ስቱዲዮውን ለመገንባት ቀድሞውኑ ፍላጎት የነበረው ቢሆንም አዳዲስ ሙዚቀኞች ዘርፉን ለመቀላቀል በሚያደርጉት ሂደት ውስጥ እነርሱን ለመርዳት መንገዱ አስቸጋሪ መሆኑ በይበልጥ እንዳነሳሳው ይገልፃል።

የስቱዲዮ መገንባት ስራው የኮቪድ ወረርሽ በተከሰተበት ወቅት ቤት ውስጥ ተሞክሮ ጥሩ ውጤት እንዳገኘበት የሚናገረው ሳሚ ዳን ግንባታውን በፈጣሪ እርዳታና በመልካም ስዎች ትብብር እውን ሊሆን እደቻለም ያብራራል ።

አዲሱ ስቱዲዮ ሙከራ ተደርጎለት ሪከርድ ማድረግ የጀመረ ሲሆን በሁሉም የሙዚቃ ዘርፍ ስራዎችን እየከወነ ይገኛል።

ድምፃዊ ሳሚ ዳን አያይዞም ሌላኛው መልኬ የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም በመስራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
የኮራ አዋርድን በሰፊ ልዩነት በመምራት ላይ እንደሚገኝ ድምፃዊ አስቻለው ፈጠነ አስታወቀ::

በቅርብ አሸናፊው በሚታወቀው የኮራ የሙዚቃ ውድድር አስቻለው በ47% ከመቶ ድምፅ እየመራ ይገኛል::

ድምፃዊው በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፁ ስለ ሆነው ሲገልፅ "ክቡራን የጥበብ ወዳጆቼ እጅግ አድርጌ አመሰግናለሁ ሁለተኛውን ዙር የኮራ ዉድድርም በአንደኝነት በሰፊ ልዩነት እየመራን ነው" ሲል ፅፏል።

አስቻለው በቅርብ በሰራቸው ባህላዊ ሙዚቃዎቹ ከፍተኛ አድናቆት እያገኝ ነው::

ድምፃዊዉን ለመምረጥ https://www.koraawards.com/top40 መጠቀም ትችላላቹህ::

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
ታዋቂው የሙዚቃ አቀናባሪ ሱልጣን ኑሪ (ሶፊ) የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት 120ኛ ዓመት ክብረ በዓልን በማስመልከት በልዩ ሁኔታ የተቀናበረ ሙዚቃን ለአምባሳደር ማሲንጋ አስረከበ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዳዊት ፅጌ 100ሺ ብር ለገሰ

ትናንት በሰይፉ ሾው ላይ ቀርበው ለነበሩት መንታ ልጆች አይናቸውን ለማብራት አጠቃላይ 400ሺ ዶላር ያስፈልጋል የተባለ ሲሆን ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር 500ሺ ብር  እንዲሁም በብዙዎች ዘንድ የድምፅ አቅሙንና ችሎታውን ያሳየው ዳዊት ፅጌ ወደ 100ሺ ብር ለእርዳታ ሰጥተዋል።

ሼር በማድረግ እንጀምር!

አካውንታቸው ይህው እባካችሁ
ሼር አድርጉት

* СВЕ 1000622473872
* Dashen Bank 5563671317021
* Abyssinia bank 91613069
* ኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ 1023500172828
* አዋሽ ባንክ 013471254339600

ትግስት ካሳ ቀፀላ

ስልክ
* 0911868306
* 0911137097

go fund me
* https://gofund.me/42557274

ይህን ሼር ማድርግ መልካም ነገር መስራት ነውና እባካችሁ ሼር አድርጉላቸው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍4
የክብር ሽልማት የአመቱ ምርጥ አምስት የወፈን ግጥም ተለይተዋል

1, አብነት አጎናፍር - አትከልክሉኝ
2, ዮሃና - ገላጋይ
3, ዳን አድማሱ - ላይለ ኩሉ
4, ኤልያስ መልካ - ማንነቴ
5, ዘሩባቤል ሞላ - እርፍ በይ

በዚህ ሊንክ ገብተው የእርስዎን ምርጥ ይምረጡ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://kibershilemat.com

ለርሶስ የአመቱ ምርጥ ግጥም የቱ ነው?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ድምፃዊ አብዱ ኪያር 5ኛ አልበሙን መጨረሱን ይፋ አድርጓል።

መርካቶ ሰፈሬ የተሰኘውን አልበም ቀ1995 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ አድርሶ ወደ ሙዚቃ ኢንዱስትሪው የተቀላቀለው አብዱ ኪያር ፍቅር በአማርኛ ፣ ምነው ሸዋ እና ጥቁር አንበሳ በተሰኙ አልበሞቹ የተለያዩ ተወዳጅ ስራዎችን ማቅረቡ ይታወሳል ።

በአልበሙ ያሉ እና ከአልበሙ ውጭ በነጠላ የተለያዩ የሙዚቃ ክሊፖችንም አቅርቧል ።

አዲስ አልበሙን ስማገኘው ሳሙኤል አቀናብሮታል ። የመውጫው ቀንን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ኢቭንቶችን በማሰናዳት የሚታወቀው ፒሜጂ ይፋ ለማድረግ ተፍተፍ እያለ ይገኛል ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
🔥1
ደርሷል ሰዓቱ !

#Ethiopia | የአንጋፋዋ የበጎ ፈቃድና የሰላም አምባሳደር ፤ የአርቲስት ቻቺ ታደሰ "ደርሷል ሰዓቱ ! " የተሰኘው ነጠላ ዜማ ከአስር ዓመት በኃላ ዛሬ ማምሻውን ተለቀቀ።

የአንጋፋዋ የበጎፈቃድና የሰላም አምባሳደር ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ "ሰማያችን ሊጠራ ጉም ተኖ ከአድማስ ማዶ እየተፍለቀለቀች እንደምትወጣ የፈካች ውብ ጸሀይ ልትወጣ ይሄው "ደርሷል ሰዓቱ " ምርታችን ሊያብብ አዝመራችን ሊያጠግበን ሰላማችን ሊበዛ ይሄው "ደርሷል ሰዓቱ" እንድንል የሚያስችለን ብሩህ ዘመን ለሁላችንም እንዲመጣልን ሁላችንም ለሰላምና ለፍቅር እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን"ብላለች።

የድምጻዊት ቻቺ ታደሰ "ደርሷል ሰዓቱ " ነጠላ ዜማ ዛሬ ይፋ የተደረገ ሲሆን ግጥምና ዜማውን ራሷ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ እና ወንድሟ ጳውሎስ ታደሰ የሰሩ ሲሆን ሚክሲንግና ማስተሪንጉን ኬኒ አለን ሰርቶላታል።

አምስት የሙዚቃ አልበም ያላት ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ ይህ "ደርሷል ሰዓቱ" የተሰኘው ሙዚቃዋ ሶስተኛው ነጠላ ስራዋ ሲሆን ሙዚቃ የሚያጠነጥነው የሰላምን ጥሪ እና ወደ ፈጣሪ የምማልድበት የምንጮኽበት ተስፋን ፍቅር የምንመኘበት እንዲሆን ተደርጎ በሶስት ቀናት ውስጥ እንደተሰራ ድምጻዊት ቻቺ ታደሰ ገልጻለች።