Waliya Entertainment
287 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የማይክል ጃክሰን ጃኬት በጨረታ 306 ሺህ ዶላር ተሸጠ።

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ22 ዓመታት በፊት ሕይወቱ ያለፈው አሜሪካዊው የፖፕ ሙዚቃ ንጉሥ ማይክል ጃክሰን ጃኬት ለጨረታ ቀርቦ 306 ሺህ ዶላር መሸጡ ተሰምቷል፡፡

ጃኬቱ በ1980ዎቹ ማይክል ጃክሰን ፔፕሲ ኮላን ሲያስተዋውቅ ለብሶት እንደነበር ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲልም “ሙን ዎክ ዳንስ” የተባለውን የእግር ዳንስ በፓሪስ ባሳየበት ወቅት የለበሰው ኮፍያ ለጨረታ ቀርቦ 67 ሺህ ዶላር መሸጡን አስታውሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሌላ በኩል የማይክል ጃኬት ለጨረታ በቀረበበት መድረክ የቀድሞዋ እንግሊዛዊት አቀንቃኝ ኤሚ ወይንሃውስ የፀጉር ጌጥ በ22 ሺህ 900 ዶላር ተሽጧል፡፡

የፀጉር ጌጡ በመጨረሻ አልበሟ “ደኅና አይደለሁም” (I’m not good) በተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮዋ ላይ የተጠቀመችው መሆኑም ተመላክቷል፡፡

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment
1
#roba_junior #ALBUM
የሮባ ጁኒየር ደቦል የተሰኘው የመጀመሪያ አልበሙ የምርቃት መርሀ ግብር#በምስል

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment
👍1
ነዋይ ደበበ : ሃመረ ድምፅ

ነዋይ ደበበ በሐመር ባኮ የተወለደ ሲሆን እድገቱ ግን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ነው። በአሰላ፣ አዋሳ እና ወላይታ ሶዶ የኖረ ሲሆን ንዋይ ለሙዚቃ ያለው ፍቅር የጀመረው አሰላ ከተማ በሙገኘው በራስ አንዳርጌ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ እያለ ነው። መምህራኑ ነዋይን ለሙዚቃ ፍቅር እንዲኖረው በተለያየ መንገድ ድጋፍ አድርገዋል። በውጤቱም ነዋይ በከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ባንድ ውስጥ ጥሩ ውጤት እንዲያሳይ ሆኗል።

ነዋይ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዉስጥ ችሎታውን ካዳበረ በኋላ የሙዚቃ ህይወቱን ለማሳደግ ወደ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ሄደ። በአዲስ አበባ የአምባሳደር ቲያትር እና የራስ ቴአትር ባህላዊ ባንድን ተቀላቀለ።

እ.ኤ.አ. 1970ዎቹ ነዋይ ደበበ ማበል ነዉ የተሰኘዉን በህዝቡ ዘንድ ብዙ ተወዳጅነትን ያተረፉ "እሸት በላሁኝ" ፣ "የጥቅምት አበባ" እንድሁም እኛዉ እንታረቅ የተሰኙ ሙዚቃዎችን ያካተተው የመጀመሪያ አልበሙን ለህዝብ አደረሰ። ነዋይ ከዛ በኋላ አምስት የስቱዲዮ አልበሞችን ለህዝቡ ያደረሰ ሲሆን ከሌሎች አርቲስቶች ጋር ደግሞ በተለያዩ አልበሞች ላይ ተባብሯል።እነዛም ስራዎቹ በብዙ ተመልካቾች ዘንድ ታላቅ ዝናን አስገኝተውለታል።


Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment #neway_debebe
2👍1
የዳዊት ፅጌ በ አሜሪካ DMV አካባቢ ይዘጋጃል ተብሎ የሚነገረው ወሬ ከአርቲስቱ እውቅና ውጪ መሆኑን ተናገረ።

ዳዊት ፅጌም በራሱ በኢንስታግራም ገፁ ላይ እንዲህ ሲል መልክት አስተላልፏል።
"ውድ በ DMV አካባቢ የምትገኙ የሙዚቃ አድናቂዎቼአሜሪካን ሀገር ካሉ የሙዚቃ አድናቂዎቼ ጋር ለመገናኘት የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይስተካከሉ ያለእኔ እውቅና እና ፈቃድ November 24, 2023 በ ዋሺንግተን ዲሲ የሙዚቃ ስራዬን እንደማቀርብ ተደርጎ የተለቀቀው ማስታወቂያ ትክክል ያልሆነ መሆኑን እየገለፅኩ ወደ አሜሪካን ለመምጣት ሙሉ ዝግጅቴን ሳጠናቅቅ በዚሁ ገፄ ላይ የማሳውቃችሁ መሆኑን በትህትና አሳውቃለሁ"

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment #dawit_tsige
👍1
ኦላን ይዤ አላፍርም ይህንን አውቃለሁ
ወደ ፍቅር ልሂድ ምን እጠብቃለሁ?

#Ethiopia | ግፎችን መዘንጋት ቀላል አይደለም። በደልን በበደል ከማወራረድ ይልቅ በደልን ሆን ብሎ መተው እንደ ምላስ ጂምናስቲክ ቀለል ያለ የቃላት ጥምዛዜ አይደለም። የቃላት ወገብን እንደማሠራት ቀሊል አይደለም። ለምጣዱ ሲባል አይጧን ለማሳለፍ፥ የምጣዱን ዋጋ ማወቅ ይፈልጋል። አይጧ በነባር ጥፋቷ ያልተቀጣችው፥ የትክክለኛነት ካባ አስደርቧት እንዳልሆነ የሚያውጠነጥን እሳቤ ይፈልጋል። ይህ እሳቤ ሊሰርጽ የሚሞከረው፥ ለአይጧ እና የቅጣት በትር ለጨበጠው አካል ነው። ዱላ ተይዞ ከአይጧ ሞት በላይ የምጣዱ ሕልው እንደሚልቅ ማሰብ ደግሞ እጅግ በጣም አዳጋች ነው። እንኳን “በደል ያሰለለው የተገዘገዘ አንጀት” ተሸክሞ ይቅርና እንዲያው ያለምንም ምክንያት መዶሻ የያዘ ሰው ሚስማሩን ለመሰመር እጁን ይከረክረዋል።

ፈረንሳዊው ሊቅ ሬኒ፦ "ሰዎች ሀገር ለመገንባት ከፈለጉ በታሪክ ውስጥ የተፈፀሙ አንዳንድ ግፎችን ለመርሳት ዝግጁ መሆን አለባቸው" ይላል። ለመርሳት መሞከር ደግሞ ሁነኛ የማስታወስ መንገድ ስለሆነ ግፎችን መርሳት ይበልጡኑ የማይቻል ያደርገዋል። ይህንን ተቃርኖ ማረቅ የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው። ለተበዳዩ የመበደሉን ዕውቅና መስጠት የሚችለው ፍቅር ብቻ ነው። ፍቅር ራሱ የበደል ካሳ ነው።

#ወደ ፍቅር ጉዞ
©ቢኒያም አበራ

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment #teddy_afro
ሙዚክ ሪቮሊሽን ክለብ የቲቪ ፕሮግራም ሊጀምር እንደሆነ ተገለፀ

#Ethiopia | ሙዚክ ሪቮሊሽን ክለብ ከአርትስ ቲቪ ጋር በመተባበር በአዲስ አቀራረብ ፕሮግራም ሊጀምር እንደሆነ የአርትስ ቲቪ እኔ ሙዚክ ሪቮሊሽን ክለብ በጋራ ዛሬ ኅዳር 4 /2016 በክለቡ በጋራ በሰጡትጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።

አርትስ ቴሌቪዥን በቴሌቪዥን በሚሠራቸው የመዝናኛ ፕሮግራሞቹ እስከ ዛሬ በሃገራችን ከነበሩት የመዝናኛ ፕሮግራሞች በአይነቱ ልዩና ተመራጭ የሆኑ ፕሮግራሞቹን እየሠራ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ ከMusic revolution club በጋራ በመሆን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአይድል ፕሮግራም ሊጀምሩ እንደሆነ ገልጸዋል ።

ሙዩዚክ ሪቮሊሽን ክለብ ከተመሠረተ 6 አመታት የሆነው ሲሆን እስካሁን ምንም አይነት ነውር ነገር የሌለበት

👉በየቀኑ ኮንሰርት የሚደገስበት፣የሙዚክ ሪከርድስ ባለቤት፣ከአንጋፋዎቹ ጋሽ መሃሙድ ጀምሮ እስከ አሁን ወጣት ድምፃዊያን ድረስ በዚህ ክለብ የሙዚቃ ሥራውን ያላቀረበ አርቲስት አይኖርም

በዚህ አይድል ዳኛ ሆነው የቀረቡት
👇👇👇
👉ክብረት ዘኪሮስ
👉ሮቤል መሐሪ
👉ዲጄ ዳኒ ናቸው

በሙዩዚክ ሪቮሊሽን አይድል የውድድር መሥፈርት

👉እድሜ ከ16 አመት በላይ
👉ለመመዝገብ 500 ብር
👉የቆይታ ጊዜው ለአንድ አመት ሲሆን በዘንድሮው የገና በአል ተጀምሮ ለቀጣዩ አመት የገና በአል ይጠናቀቃል ሲሉ ገልፀዋል ።

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaent
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaent
Telegram - https://www.t.me/waliyaent

#Ethiopia #waliya_entertainment
1