Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
#አድዋ የጥቁር ሕዝብ ኩራት💪💚💛

#እንኳን ለአድዋ በአል 128ኛው የአፍሪካኖች :የጥቁር ሕዝብ ኩራት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን💪💚💛

#Waliya_Entertainemnt #Adwa #Ethiopia
👍1
የዓድዋዋ እመቤት - እጅጋየሁ ሽባባው 💚💛
**
*
አንዳድደ የጥበብ ስራዎች ለባለቤቱ በሕይወት ዘመን አንዴ ብቻ ይሰራሉ ። አንዳንድ የጥበብ ስራዎች ደግሞ በአጠቃላይ ትውልዱ በዘመኑ ሁሉ እንዳይደረስበትና እንዳይተካ ሆኖ ይሰራል ። ለግጥም አፍላቂዋ ፣ ለዜማ አውጪዋ ፣ ለድምጻዊቷ እጅጋየሁ ሽባባው ( ጂጂ ) " ዓድዋ " የተሰኘው ስራዋ ሁለቱንም ነው ። እሷም ትውልዱም ደግመው አይሰሩትም ። ማንም ላይደርስበት የተሰቀለ ስራ ነው ፤ የማይደገም ። እንዲህ ያሉ ከዘመን አንድ ጊዜ የሚመጡ ስራዎች " እስቲ ግጥም ልጻፍ " ተብሎ በመቀመጥ የሚመጡ አይደሉም ። እንዲሁ የሚፈሱ ናቸው ። ፍስስስስስ የሚሉ ። ለዚያ ነው በባለቤቱም በሌላም የማይደገሙ የሚሆኑት ። የዓድዋዋ እመቤት ፣ የጥበቧ ጣይቱ ስለሰጠሽን ዘመን አይሽሬ ስራ እናመሰግንሻለን 💚💛

የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል
ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ(2)
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆሙኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር በድል እኖራለሁ
ያው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ …. አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ (3) የድል ታሪክሽኝ አውሪ
ተናገሪ…..

Follow us on
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
👍1🥰1
የዛሬው ምርጥ ፎቶ!!!

"ለሃገራቸው ታመው ለሃገር ስለሞቱት
ህይወት ዕድሜያቸውን አካል ለገበሩት
ለህልውናዋ ዘብ ሆነው ለቆሙት
ልንዘምር ይገባል ሃገርን ላቆዩት" - እሱባለው ይታየው

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Adwa
👍21
የኢትዮጵያ አይዶል አሸናፊዋ በቦንጋ አቀባበል ተደረገላት

#Ethiopia | በኢትዮጵያ አይዶል ሁለተኛ ዙር በድምፃዊያን ዘርፍ አሸናፊ የሆነችው ብዙዓየሁ ሰሎሞን በትውልድ አካባቢዋ ቦንጋ ከተማ ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016ዓ.ም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የከተማው ነዋሪ ፣ የከተማው አስተዳደር እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።

የቦንጋ ከተማ አስተዳዳሪ ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ ድምፃዊት ብዙዓየሁ ከራሷ አልፋ አከባቢውን እና የአከባቢውን ማህበረሰብ በኪነ-ጥበብ ማስተዋወቅ በመቻሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ለምታደርገው ጥረት ይሆን ዘንድ በቦንጋ ከተማ የ300 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስራያ የሚሆን የመሬት ስጦታ እንደተበረከተላት ተናግረዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው ካፋ የብዙ እውቅ ሰዎች መፍለቂያ መሆኗን በመናገር ብዙዓየሁ ሰሎሞንን ከእነዚህ አንዷ ናት ብለዋል።

አያይዘውም ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች ምስጋና አቅርበው ድምፃዊቷ ላደረገችው አስተዋጽኦ የሚያንሳት ቢሆንም በማለት የ100,000 (መቶ ሺህ ) ብር ሽልማት አበርክተውላታል።

በክብረአብ ፈለቀ
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
"ዋግ ኽምራ የጥበብ ልጆቿን ሞሸረች!

* 1 ሚሊዮን ብር እና ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል

#Ethiopia | "የዋግ ኽምራዎቹ ጥበበኞች! በባለ አገሩ አይዶል በዓለም አደባባይ ምርጥ ብቃታቸውን ያስመሰከሩት አሸናፊዎች ባለ ልዩ ተሰጥኦ ድምፃዊያን ውድድሩን በ1ኛነት ያሸነፈው አክሊሉ አስፋው፣ በ2ኛነት ያሸነፈው ብሩክ ሙሉጌታ እና ተማረ ሳሙኤል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሠቆጣ ከተማ የደመቀ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይሉ ግርማይ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የዛሬዋ ቀን ለዋግ ህዝብ ልዩ ነው። እኛ ኽምራዊያን የጥበብ ሰዎች መሆናችንን ያዬነበት ዕለት ነው ብለዋል።

ወጣቶቹ እንዲበረታቱና እዚህ እንዲደርሱ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ አካላትን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

ጀማሪ የኪነ ጥበብ ሰዎችም እንዲበረታቱና እንደ ዛሬው ሁሉ የጥበበኞቹ ልጆች መሆናችን ከፍ ብሎ እንዲታይ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

በመጨረሻም እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር ከወረዳዎችና ጋር በመተባበር 1ሚሊዮን ብር እና የሠቆጣ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት በማበርከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ስለ ቴዲ አፍሮ ቤዛ ስለተሰኘው (ህብረ ዜማ) ያልተሰሙ መረጃዎች

ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከተለያዩ የውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት

1, ሙዚቃው ከዛሬ 5 አመት በፊት የተሰራ ሲሆን አሁን ላይ ግን እንደአዲስ ትናንሽ ማስተካከያዎች እንደተደረጉለት።

2, ቤዛ (ህብረዜማ) በተሰኘው በአጠቃላይ ከ 30 የሚበልጡ ባለሙያዎች እንደተሳተፉስ ያውቃሉ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እማማ አፍሪካ ~ ማሪያ ማኬባ

#Ethiopia | የነጻነት ታጋይዋና አፓርታይድን በሙዚቃ ሥራዎቿ በመታገል የምትታወቀው ማሪያ ማኬባ 92ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ሥራዋን በመዘከር እየታሰበ ነው

እማማ አፍሪካ በሚል ድንቅ ዘፈኗ የምታወቀው ማሪያ ማኬባ ከኢትዮጵያዊቷ ሜሪ አርሚዴ ጋር እንዳቀነቀነች የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ።

የሩሲያ ዜና አገልግሎት የስፑትኒክ አፍሪካ ጋዜጠኛው ማሐመድ ኖህ ሁስማን የማሪያ ማኬባ 92ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ሥራዋን በመዘከር አክብሯል።

ማሪያ የፓርታይድን በመታገልና ለጥቁሮች ነፃነት ድምጽ በመሆን በርካታ የጥበበብ ሥራዎችን ያቀረበች የአፍሪካ የነፃነት ታጋይ ነበረች። በብዙ ኢትዮጵያውያንም እማማ አፍሪካ በሚለው መዝሙር አከል ዘፈኗ ትታወቃለች።

በ72 ዓመቷ ሕይወታ ያለፈው ማሪያ ማኬባ የእሷ ተወዳጅ ዘፈን "ፓታ ፓታ" (1967) የነጻነት ዜማውን በመያዝ በደቡብ አፍሪካ መዝሙር ሆነ።

ከእውቁ አሜሪካዊው ዘፋኝ በላፎንቴ “ Evening with Belafonte/Makeba” ጋር በትብብር በሠሩት አልበማቸው የግራሚ ሽልማት አግኝታለች።

ይህች እውቅ የአፍሪካ ፈርጥ የነፃነት ታጋይ ዛሬ 92 ዓመታ በሥራዎቿ እየተሰበ ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍2