የቴዲ አፍሮ አዲስ ሙዚቃ (ቤዛ) ግጥም
ቤዛ (ኅብረ ዝማሬ)
ይህቺ ሰንደቅ ዓላማ የክብር ምልክት
ሥፋት እና ምልዓት ርቀት አላት
በዓላማ አንድ ሆና ሦስት ናት በመልክ
ሆ …..
ላላ ….
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ብለን ተነስተናል ተስፋ አርገን ኹላችን
እኔ ለኔ ሳንል ቅድሚያ ለሀገራችን
እንደ ሐራሴቦን (ወጥተን ከሐራሴቦን) አንድ ዓላማ ይዘን
እንገባለን ከነዓን በፍቅር ተጉዘን
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
የጸና ነው በአንድነት ላይ መሠረታችን
አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ነው ባንዲራችን
ማነው ደፍሮ በዘር ቋንቋ የሚነጣጥለን
እኛ እንደሆን እማንለያይ አንድ ነን
በዘር በሃይማኖት በማሰብ አንሰናል
ይብቃ በኛ ዘመን ታሪክ ይወቅሰናል
እንቁም ተያይዘን በአንድነት
በኢትዮጵያዊነት
ቤዛ ለሀገር ቤዛ ሆነው አርበኞቹ
ያቆዩሽ ሀገር ጀግኖቹ
እናት ኢትዮጵያ
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
የአንድነት ኃይል ጨለማን ድል ነሥቶ
ጨለማን ድል ነሥቶ (x2)
እናያለን አዲስ ፀሐይ ወቶ
አዲስ ፀሐይ ወቶ (x2)
በዝምታ ብንመስልም የተኛን
ብንመስልም የተኛን (x2)
ከተነሣን ማን ሊያቆመን እኛን
ማን ሊያቆመን እኛን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
ቀልድ አናውቅም እኛ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን (x2)
ዓላማ ነው
ዓላማ ነው አንድ ያረገን እኛን
አንድ ያረገን እኛን (x2)
ቤታችን ናት አትንኳት ኢትዮጵያን
አትንኳት ኢትዮጵያን (x2)
ከሷ በፊት ይፈሳል ደማችን
ይፈሳል ደማችን (x2)
አትምጡብን በቃ በሀገራችን
በእናት ሀገራችን
―———————————————
ዜማ እና ግጥም — ቴዎድሮስ ካሳሁን ( ቴዲ አፍሮ)
ተጨማሪ የመግቢያ ዜማ — ቆየት ካለ ኅብረ ዝማሬ የተወሰደ
ሙዚቃ ቅንብር፣ ሚክሲንግ እና ሊድ ጊታር — በረከት ተስፋዝጊ (ቤኪ)
ቴነር ሣክስ — ዘሪሁን በለጠ
ማስተሪንግ — ማሩ ዓለማየሁ (ማርቨን ስቱዲዮ)
ተቀባዮች ፤
1. ምኞት ኃይሉ (ዲጄ ዊሽ)
2. ልዑል ሲሳይ
3. ግሩም ታምራት
ምስጋና፥ ይህ ሥራ የተሳካ እንዲሆን አስተዋፅዖፆ ላደረጋችሁ ወገኖች
በሙሉ
የሐራሴቦን ትርጓሜ
―――――――――
ሐራሴቦን የቦታ ስም ነው። እጅግ በረኃማ ነው።
ታሪክ : - እግዚአብሔር እሥራኤልን ከግብጽ ነጻ አውጥቶ መና ከሰማይ እያወረደ፣ ውኅ ከጭንጫ እያፈለቀ ሲመግባቸው ሰለቸን ብለው በእግዚአብሔር ላይ በማንጎራጎራቸው ሐራሴቦን ወደተባለው በረሃ እንዲወርዱ አዘዛቸው። በዚያም በእባብ እየተነደፉ አለቁ። በንስሐ ሲመለሱ ራርቶላቸው ሙሴን ከነሐስ የእባብ ምስል ሰርቶ በመስቀል ላይ እንዲሰቅለው ያን የሚያዩ እንዳይነደፉ፣ የተነደፉ እንዲድኑ፣ ማየት የማይችሉ የነሐሱ እባብ ሲደበደብ ድምፁን ሰምተው እንዲድኑ መድኃኒት ሠራላቸው።
ተምሳሌታዊ ትርጉም ፦
ሐራሴቦን = የሲዖል
ተናዳፊው እባብ = የሰይጣን
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music

👍1
በዛሬው እለት ከተለቀቁት የሙዚቃ ስራዎች የማንን ወደዳችሁት?
Anonymous Poll
44%
ቴዲ አፍሮ - ቤዛ (ህብረ ዜማ)
44%
ዳኜ ዋለ - ወንድ ልጅ ቆረጠ
13%
ቴዲ-ዮ - ይለያል
#አድዋ የጥቁር ሕዝብ ኩራት💪💚💛❤
#እንኳን ለአድዋ በአል 128ኛው የአፍሪካኖች :የጥቁር ሕዝብ ኩራት በሰላም አደረሳችሁ/አደረሰን💪💚💛❤
#Waliya_Entertainemnt #Adwa #Ethiopia

የዓድዋዋ እመቤት - እጅጋየሁ ሽባባው 💚💛❤
***
አንዳድደ የጥበብ ስራዎች ለባለቤቱ በሕይወት ዘመን አንዴ ብቻ ይሰራሉ ። አንዳንድ የጥበብ ስራዎች ደግሞ በአጠቃላይ ትውልዱ በዘመኑ ሁሉ እንዳይደረስበትና እንዳይተካ ሆኖ ይሰራል ። ለግጥም አፍላቂዋ ፣ ለዜማ አውጪዋ ፣ ለድምጻዊቷ እጅጋየሁ ሽባባው ( ጂጂ ) " ዓድዋ " የተሰኘው ስራዋ ሁለቱንም ነው ። እሷም ትውልዱም ደግመው አይሰሩትም ። ማንም ላይደርስበት የተሰቀለ ስራ ነው ፤ የማይደገም ። እንዲህ ያሉ ከዘመን አንድ ጊዜ የሚመጡ ስራዎች " እስቲ ግጥም ልጻፍ " ተብሎ በመቀመጥ የሚመጡ አይደሉም ። እንዲሁ የሚፈሱ ናቸው ። ፍስስስስስ የሚሉ ። ለዚያ ነው በባለቤቱም በሌላም የማይደገሙ የሚሆኑት ። የዓድዋዋ እመቤት ፣ የጥበቧ ጣይቱ ስለሰጠሽን ዘመን አይሽሬ ስራ እናመሰግንሻለን 💚💛❤
የሰው ልጅ ክቡር
ሰው መሆን ክቡር
ሰው ሞቷል ሰው ሊያድን ሰውን ሲያከብር
በደግነት በፍቅር በክብር ተጠርቶ
በክብር ይሄዳል
ሰው ሊኖር ሰው ሞቶ(2)
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት
ሰው ተከፍሎበታል ከደምና ካጥንት
ስንት ወገን ወደቀ በነፃነት ምድር
ትናገር አድዋ ትናገር ትመስክር
ትናገር አድዋ ትናገር ሀገሬ
እንዴት እንደቆሙኩኝ ከፊታችሁ ዛሬ
በኩራት በክብር በደስታ በፍቅር በድል እኖራለሁ
ያው በቀን በቀን
ደሞ መከራውን ያን ሁሉ ሰቀቀን
አድዋ ዛሬ ናት አድዋ ትላንት
መቼ ተነሱና የወዳደቁት
ምስጋና ለእርሱ ለአድዋ ጀግኖች
ለዛሬ ነፃነት ላበቁኝ ወገኖች
የጥቁር ድል አምባ …. አድዋ
አፍሪካ እምዬ ኢትዮጵያ
ተናገሪ (3) የድል ታሪክሽኝ አውሪ
ተናገሪ…..
Follow us on

👍1🥰1
የዛሬው ምርጥ ፎቶ!!!
"ለሃገራቸው ታመው ለሃገር ስለሞቱት
ህይወት ዕድሜያቸውን አካል ለገበሩት
ለህልውናዋ ዘብ ሆነው ለቆሙት
ልንዘምር ይገባል ሃገርን ላቆዩት" - እሱባለው ይታየው
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
#Waliya_Entertainemnt #Music #Adwa

👍2❤1
የኢትዮጵያ አይዶል አሸናፊዋ በቦንጋ አቀባበል ተደረገላት
#Ethiopia | በኢትዮጵያ አይዶል ሁለተኛ ዙር በድምፃዊያን ዘርፍ አሸናፊ የሆነችው ብዙዓየሁ ሰሎሞን በትውልድ አካባቢዋ ቦንጋ ከተማ ዛሬ የካቲት 24 ቀን 2016ዓ.ም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።
በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የከተማው ነዋሪ ፣ የከተማው አስተዳደር እና የሀገር ሽማግሌዎች ተገኝተዋል።
የቦንጋ ከተማ አስተዳዳሪ ከንቲባ አቶ አስማማው አደመ ድምፃዊት ብዙዓየሁ ከራሷ አልፋ አከባቢውን እና የአከባቢውን ማህበረሰብ በኪነ-ጥበብ ማስተዋወቅ በመቻሏ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ወደፊትም ለምታደርገው ጥረት ይሆን ዘንድ በቦንጋ ከተማ የ300 ካሬ ሜትር የመኖሪያ ቤት መስራያ የሚሆን የመሬት ስጦታ እንደተበረከተላት ተናግረዋል።
የካፋ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው ካፋ የብዙ እውቅ ሰዎች መፍለቂያ መሆኗን በመናገር ብዙዓየሁ ሰሎሞንን ከእነዚህ አንዷ ናት ብለዋል።
አያይዘውም ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች ምስጋና አቅርበው ድምፃዊቷ ላደረገችው አስተዋጽኦ የሚያንሳት ቢሆንም በማለት የ100,000 (መቶ ሺህ ) ብር ሽልማት አበርክተውላታል።
በክብረአብ ፈለቀ

"ዋግ ኽምራ የጥበብ ልጆቿን ሞሸረች!
* 1 ሚሊዮን ብር እና ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል
#Ethiopia | "የዋግ ኽምራዎቹ ጥበበኞች! በባለ አገሩ አይዶል በዓለም አደባባይ ምርጥ ብቃታቸውን ያስመሰከሩት አሸናፊዎች ባለ ልዩ ተሰጥኦ ድምፃዊያን ውድድሩን በ1ኛነት ያሸነፈው አክሊሉ አስፋው፣ በ2ኛነት ያሸነፈው ብሩክ ሙሉጌታ እና ተማረ ሳሙኤል በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሠቆጣ ከተማ የደመቀ አቀባበል ተደርጓላቸዋል።
የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ተቀዳሚ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኃይሉ ግርማይ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የዛሬዋ ቀን ለዋግ ህዝብ ልዩ ነው። እኛ ኽምራዊያን የጥበብ ሰዎች መሆናችንን ያዬነበት ዕለት ነው ብለዋል።
ወጣቶቹ እንዲበረታቱና እዚህ እንዲደርሱ አስተዋፅኦ ያበረከታችሁ አካላትን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ጀማሪ የኪነ ጥበብ ሰዎችም እንዲበረታቱና እንደ ዛሬው ሁሉ የጥበበኞቹ ልጆች መሆናችን ከፍ ብሎ እንዲታይ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።
በመጨረሻም እንደ ብሔረሰብ አስተዳደር ከወረዳዎችና ጋር በመተባበር 1ሚሊዮን ብር እና የሠቆጣ ከተማ አስተዳደር ደግሞ ለሦስቱም ድምፃዊያን 150 ካ.ሜትር መኖሪያ ቦታ ሽልማት በማበርከት መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ስለ ቴዲ አፍሮ ቤዛ ስለተሰኘው (ህብረ ዜማ) ያልተሰሙ መረጃዎች
ዋልያ ኢንተርቴይመንት ከተለያዩ የውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት
1, ሙዚቃው ከዛሬ 5 አመት በፊት የተሰራ ሲሆን አሁን ላይ ግን እንደአዲስ ትናንሽ ማስተካከያዎች እንደተደረጉለት።
2, ቤዛ (ህብረዜማ) በተሰኘው በአጠቃላይ ከ 30 የሚበልጡ ባለሙያዎች እንደተሳተፉስ ያውቃሉ።