Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
ትናንት ከተለቀቁት አልበሞች ውስጥ የቱን ይበልጥ ወደዱት?
Anonymous Poll
42%
ቴዲ ዮ - ይለያል
31%
የማ - የደጋ ሰው
27%
አስቻለው ፈጠነ - አስቻለ
👍2
ድምፃዊ ኤፍሬም አማረ እና ተዋናይት ፍርያት የማነ የመጀመሪያ ልጃቸውን ካገኙ በኋላ ከመላው አድናቂዎች ለተሰጣቸው የደስታ መልዕክት እናመሰግናለን ብሏል። በተለይ ተዋናይት ፍርያት የማነ ባለፉት ሶስት አመታት የደረሰባትን በዝምታ ለምን እንዳለፈች በቅርቡ ሁሉንም ይፋ እንደምታደርግ ገልጻለች።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
Waliya Entertainment
ትናንት ከተለቀቁት አልበሞች ውስጥ የቱን ይበልጥ ወደዱት?
የደጋ ሰው ፤ የጂጂ ደቂቅ 

የባለቅኔዋ ቃል 'እምዬ እናት ዓለም እስቲ አንቂኝ ከእንቅልፌ' የሚል ነው፡፡ የባለቅኔዋን ልመና እና የእምዬን አደራ ዝቅ ብለው የተቀበሉ ጎበዛዝት መጥተዋል፡፡

ስማችሁ ማን ነው ቢባሉ ፤ የደጋ ሰው የተባሉ በጎ ወራሽ ናቸው፡፡

በባዶ ቤት የሸፈትን ÷

መለኞቹ ደግ ነገር ሲያዩ ÷ ታጠቅ የአገር ልጅ ይህ ነገር የኛ ነው ይላሉ፡፡
የደጋ ሰው ምልምል የኛ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ንዋይ ከማትነጥፈዋ እመቤት እያለበ የሚያጠጣ ግት ነው፡፡

ጋሽ ብርሃኑ ድንቄ ስለራሷቸው ትውልድ ሲናገሩ ÷ የኔ ትውልድ 'በባዶ ቤት የሸፈተ' ነው ይላሉ፡፡

ይህ የዘመናይ ሽፍታነት የአገርን የልብ ተክልን ካለማወቅ ፣ ነብስ የሚነበብበትን ባለአገርን ካለመረዳት ፣ የፍቅር ገት የሆነውን አድባርን ከመናቅ የተገኘ ትእቢት ነበር፡፡

ዘመናይ ሁነው በባዶ ቤት የሸፈተው ትውልድ እና ዘመን 'የኢትዮጵያን መንፈስ' ቀላዋጭ አድርጓል፡፡ በጀነራል አቢይ አበበ ቋንቋ አገር የምትኖርበትን ዘዴ አጥብቆ ካለማወቅ ማጥ ውስጥ ከቶናል፡፡ (Poverty of the spirit)

የታላቁ የሀዲስ ዓለማየሁ የጠራ እውቀት ኢትዮጵያዊ መንፈስ እና ስርዓተ ማኅበር የተጎዳበትን መንገድ ከስር እስከ ራሱ ተናግረውት ነበር፡፡ 'የራስን የኑሮ ልማድ እየተው ባእድ ስራተ ማህበር ይዞት የመጣው መንፈስ ውርሱ ውሎ አድሮ አደገኛ ነው ብለው ነበር፡፡

የሆነብን ይህ ነው ÷

የአገሩን ዜማ የማያውቅ ፣ የወንዙን ገደላ ገደል የማይረዳ ÷ የእናቱን ጉርሻ ባእድ የሆነበት ÷ የወንድሙ ልሳን የሚያቀረሸው ÷ የባለአገሩን ሙያ የረሳ ከርስቱ ፤ ከግርማው የተሰደደ ትውልድ እና ዘመን ላይ ደረስን፡፡ (Shared Nationhood in crisis)

የጋሽ ብርሃኑ ድንቄ ኑዛዜ እና የጋሽ ሀዲስ ዓለማየሁ ፍርሃት እኛ በብሌኑ አየነው፡፡ (Syndrome circle) 

የማየው ወጋገን ምንድን ነው?

በፍሩድ ቋንቋ የተጨቆነው ኢትዮጵያዊ መንፈስ ተመልሷል፡፡ ይህ መንፈስ የአባታችሁን ተው ተብሎ የተዘመተበት ÷ ራስን በራስ የማዳን ጸጋ የለህም የተባለውም ነው፡፡ (Return of the repressed)

የደጋ ሰው አልበም ምርቃቱ የተጨቆነውን እና የተዘመተበትን ኢትዮጵያዊ መንፈስ አድባር መቆሚያው አድርጎ ፣ ቅጥ ባለው ቃል ልሳንኑ እያሰፈረ ፣ እመቤቴ ኢትዮጵያ ሆይ ተመለሺ ÷ ተመለሺ እያለ ሰርግና ምላሽ ላይ አደረሰን፡፡

አልበሙ እንደ አገሬ ሰው የደራ ፍቅርን ከጀግንነት ጋር የሚያጋባ ፣ ጠበቅ ያለ የአእምሮ ግጥሚያን በቅኔ እና በወርቅ የሚያቆም ፣ ባእድ የሆነውን ድምጽ እና ባሕልን በኢትዮጵያዊ መንፈስ አጥምቆ ለዓለም የሚንጠራራ ክፍት መሆኑ ከእህህ ወዲያ ያለውን አገራችንን እንድንተልም ያነቃል፡፡ (The narrative tone)

ፈረንጁ ዶናልድ ዶናሃም ይህን የመዳን እና ክፉ ቀንን የማሸነፍ ትግልን Spiritual Hibernation ብሎታል፡፡ ክፉ ቀን እንዳይመታህ ከመሸሸግ ይልቅ መዳኛውን ከባሕልህ ማህፀን ፣ ከሕብረተሰብህ ምንጭ እና ከተራራህ ውስጥ ፈልገህ ማግኘትን ይጠይቃል፡፡

ይህ ተጋድሎ በፕ/ር ማእምር እንዲህ ይሉታል 'Epistemic resistance creates the intellectual and cultural grounds for the emergence of Ethiopia'

ለዛ ነው ወደ አገርህ ስትቀርብ ፣ ወደ ባለአገርህ አንገትህን አዙረህ ስትመለከት መዳኛውን ቅጠል ፣ መቆሚያውን እግር ይገኝበታል፡፡ ይህን የመዳን ቀን ተጋድሎ ፕ/ር አበበ ዘገየ Close to the source ይሉታል፡፡

የደጋ ሰው አልበም ÷

የኢትዮጵያ መንፈስ መገኛ የሆነችው እምዬ እናት ዓለም አንቅታው ÷
ሐብታቷን ዳሶ በዜማ ፣ በድምጽ እና በሕይወታዊ እሙንነት ጠርቶ የኛ ሁኗል፡፡ (Maximizing Indigenous Values)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
እጅግ አሳዛኝ ዜና

ተወዳጁ የEbs የመዝናኛ ክፍል ባልደረባ አስፋው መሸሻ አረፈ

ተወዳጁ ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በሚዲያው ዘርፍ ረጅም ግዜ ኢትዮጵያንን በራዲዮ እያዝናና ቁምነገር በማስተማር ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን ከሀገር ውጭ ከወጣም በኃላ ኑሮ በአሜሪካ የተሰኜ አስተማሪ ፕሮግራም ለኢትዮጵያን ሲያቀርብ የነበረ ተወዳጅ ጋዜጠኛ ነበር

ከውጭ ሀገር ተመልሶም በEbs የእሁድ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ዝግጅቶችን በማቅረብ እጅግ ተወዳጅነትን ማትረፍ የቻለ የጋዜጠነትን ስነ ምግባር በአግባቡ የተላበሰ በሳል ጋዜጠኛ ነበር

ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ በአሜሪካ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ በዛሬው እለት ማረፏ ተስምቷል

ለዘመድ ወዳጅና ለአድናቂወቹ መፅናናትን እንመኛለን ከ ዋልያ ኢንተርቴይመንት

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
አስፋው መሸሻ ትናንትና መሞቱን አስመልክቶ የተለያዩ አርቲስቶች የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን እየፃፉ ይገኛሉ።

"እምናከብርህ አንጋፋው አስፋው መሸሻ እግዚአብሄር አምላክ ነብስህን ከደጋጎች ጎን ያሳርፋት ለወዳጅ ለዘመድ ለቤተሰብም መፅናናትን ይስጥ 🙏🏾🕊️" - ልጅ ማይክ

"በጣም የምንወደው አንጋፋው ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ህይወቱ አልፋለች:: እግዝያብሔር ነፍሱን ይማርልን:: ለቤተቦቹ እና ወዳጆቹ መፅናናትን ከልብ እመኛለሁ!!!" - ዳዊት ፅጌ

"የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻን ህልፈት መርዶ በቅርብ ሆኖ ጉዳዩን ከሚከታተል ወዳጄ ሰማሁ 😪 ለልጁ ለቤተሰቡና ለአድናቂ አክባሪዎቹ ሁሉ መጽናናትን እመኝላችኋለሁ ...
  
  ጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ ሆይ እንደ መረጃ አቀባይ ጋዜጠኛ በህይዎት ዘመንህ ስላደረግክልን መልካም ነገሮች ሁሉ እናመሰግንሃለን 🙏
ነፍስህ በሰላም ትረፍ 🙏" - ያሬድ ነጉ

"ነብስ ይማር ወንድሜ!!! ካንተ ጋር ያለኝ ትውስታ በተገናኘንባቸው ቀናቶች ሁሉ መልካም ድባብህ የማንኛውንም ሰው ስሜት ወደ መልካም የሚቀይር ነበር። ትናፈቃለህ!!!
ኢትዮጵያንም በበጎ ስላገለገልካት እናመሠግናለን!!" - ሳሚ ዳን

"በጣም ያሳዝናል አስፋዬ መሸሻ ወንድሜ የኔ ደግ እግዚአብሄር አምላክ ነብስህን ከደጋጎች ጎን ያሳርፋት ለወዳጅ ለዘመድ ለቤተሰብም መፅናናትን ይስጥልን 🙏🏾🕊️" - ብርሃኑ ተዘራ

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
በተወዳጁ የራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ እና አቅራቢ በነበረዉ አስፋዉ መሸሻ ህልፋተ ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ በደረሰዉም ሐዘን ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለመላዉ አድናቂዎቹ መጽናናትን እየተመኘዉ ፋጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት እንዲያኖርልን ከልብ እመኛለው።

ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #Asfaw_Meshesha
😢1
አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ምሽት ...!

#Ethiopia | በታላቁ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሚዘጋጀው የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ሰባተኛ ምሽቱን ከፍ ባለ ዝግጅት ዕረቡ ጥር 8 ያካሂዳል። በዕለቱም ድምጸ መረዋው ጎሳዬ ተስፋዬ በመሀከላችን ይገኛል! እንዲሁም ግጥሞች ፣ ወግ ፣ ሙዚቃና ሞኖሎግ ተሰናድተው እናንተ ውድ ታዳሚዎቻችንን በባህል ማዕከል አዳራሽ ከቀኑ በ 11: 30 ጀምሮ ይጠብቃችኃል ።

#ማስታወሻ :— ፕሮግራሙ ላይ ለመታደም የምትፈልጉ በአሁን ሰዓት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ያልሆናችሁ የስነ ጽሑፍ አፍቃሪያን መግቢያው በ5ተኛ በር በኩል ነው ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ዛሬ የምርጥ ድምፃዊው የአዲስ ለገሰ ልደት ነው።
🎂🎂Happy Birthday🎂🎂

ከአዲስ ለገሰ ስራዎች የቱን ትወዱታላችሁ?

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Addis_legesse #Album  #Waliya_Entertainemnt
🎉3
Attention

የአስፋው መሸሻ የሽኝትና የጸሎት መርሃግብር
ረቡዕ ጃንዋሪ 17፣ ከቀኑ 2PM ጀምሮ፣
ቨርጂኒያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ECDC) አዳርሽ የሽኝት መርሃግብር
901 S Highland St,
Arlington, VA 22204

ሃሙስ፣ ጃንዋሪ 18
ከጠዋቱ 10 AM ጀምሮ የጸሎት ስነስርዓት በደብረገነት መድሃኒአለም ቤተክርስትያን
4401 Old Branch Ave.,
Temple Hills, MD 20748
ከጸሎተ ፍታቱ በኋላ ከ1 PM ጀምሮ ጸበል ጸዲቅ ቨርጂኒያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ECDC) አዳርሽ
901 S Highland St,
Arlington, VA 22204

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Asfaw_Meshesha #music  #Waliya_Entertainemnt
😭1
🍋ልዩ የጥምቀት ፕሮግራም ከ ሃይማኖት ግርማ ጋር በ ዋልያ ኢንተርቴይመንት!!!

ሁሌም ለናንተ አሪፍ አሪፍ ስራዎችን ይዞ በመቅረብ የሚታወቀው ዋልያ ኢንተርቴይመንት እነሆ ለጥምቀት በአሉን በአል የሚያስመስል ልዩ የበአል ዝግጅት ከ ባላገሩ ቲቪ ጋር በመተባባር ወደናንተ ሊያደርስ ነው።

ቅዳሜ ከምሽቱ 2:00 ሰአት በዋልያ ኢንተርቴይመንት የዩቲዩብ ቻናል እና በባላገሩ ቲቪ ይጠብቁን። በደንብ ያተርፉበታል!!!!

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Haymanot_girma
👍1