Waliya Entertainment
288 subscribers
1.57K photos
16 videos
763 links
ሙዚቃ እና ሙዚቃ ብቻ!!!

Follow us on social medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt
Download Telegram
የታዋቂው ሙዚቀኛ (ቴዲ አፍሮ) ሚስት አርቲስት አምለሰት ሙጬ የብራንድ አምባሳደር ሆና ተሾመች።

አለም አቀፍ የጥራት ደረጃ ሽልማት ያገኘው የጀርመን ሪልእስቴት የሆነው ሮክ ስቶን ኢትዮጵያ ያለዉን ትልቅ ዓላማ ከግብ ለማድረስ ያግዘው ዘንድ ተወዳጅን ተዋናይት፣ ታዋቂ የሚድያ ባለሙያ እና ግንባር ቀደም የአረንጓዴ ልማት ተሟጋች አርቲስት አምለሰት ሙጩን የከፍታ አፓርትመንቶች ብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን ገለፀ።

አርቲስት አምለሰት በዋናነት የሮክስቶን ራዕይ በሆነው የአረንጓዴ ልማት እ ና የአካባቢ ጥበቃ ተነሳሽነቶች ላይ በመሳተፍ፣ የድርጅቱ ማስታወቂያዎችና ዝግጅቶች ላይ ፕሮጀከቱን በመወከል በኢትዮጵያ እና በሌሎችም አለም አቀፍ ሀ ገራት ላይ በማስተዋወቅ ተፅእኖ እንደምትፈጥር ይታመናል ብሏል ድርጅቱ።

አርቲስት አምለሰት ሙጩ ይህንን ፕሮጀከት እንድትወከል የተመረጠችበት ዋነ ኛው ምከንያት አረንጓዴ ዓለምን ለመፍጠር በሚደረጉ ሁለንተናዋ እውቅናዋን ተጠቅማ የተለያዩ ንቅናቄዎችን ማሳካት በመቻሏ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በከፍታ አፓርትመንቶች የቤት ባለቤት በመሆኗም ነው።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ታዋቂው ዘፋኝ (The Weekend) ከ 1000 ለሚበልጡ ህፃናት የላፕቶፕ ድጋፍ አደረገ

አቤል (The Weekend) የተባለው ትውልደ ኢትዬጲያዊው አለምአቀፍ የሙዚቃ አቀንቃኝ በአሜሪካ ሎስአንጀለስ ከተማ "School on wheels) ለተሰኘ ድርጅት በስሩ ለሚማሩ ከ1000 ለሚበልጡ ቤት አልባ ህፃናቶች የላፕቶፕ ድጋፍ አደረገ።

ከዚ በፊት አቤል (The Weekend) በሚሊየኖች የሚቆጠሩ የገንዘብ እና የቁስ ድጋፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በጋዛ ፣ በሊባኖስ እንዲሁም በተለያዩ ከተሞች ማረጉ ይታወሳል።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music #The_weekends
👍1
የአስቻለው ፈጠነ አልበም ነገ ይለቀቃል

#Ethiopia | እናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም በተሰኘው ተወዳጅ ነጠላ ዜማው የሚታወቀው አስቻለው ፈጠነ ነገ አዲስ አልበም እንደሚለቅ አስታውቋል፡፡

ድምፃዊው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አልበሙ “አስቻለ” የተሰኘ ሲሆን ሦስት አመት ገደማ እንደፈጀና በጠቅላላ 14 ዘፈኖች ተካተውበታል፡፡

አልበሙ በተለያዩ ቋንቋዎች የተሰራ ሲሆን ከነዚህም መካከል ባስኬቶኛ፣ አገውኛ፣ ጉምዝኛ፣ ትግሪኛ፣ ኦሮሚኛ እና ሌሎችም ቋንቋንዎችን ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ብዙ ባህላዊ መሳሪያዎችን በአልበሙ እንደተጠቀመ የተገለፀ ሲሆን ከ20 በላይ አጃቢዎችም እንደተካተቱበት ተጠቁሟል፡፡

የአልበሙ መታሰቢያነት በቅርቡ በህይወት ላጣነው ለአቀናባሪው እስራኤል መስፍን ይሁንልኝ ያለው አስቻለው ከ14ቱ ዘፈኖች 9ኙ በእሱ የተሰሩ መሆናቸውን አስታውሷል፡፡

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
ጋዜጠኛ የኑስ ሙሃመድ እንደከተበው
።።።።።።።።።።።።
ሁለት ገዳማውያን፣

በኪነጥበቡ ዓለም አሉ እንጂ የሉም። ሁለቱም ስለባህል፣ ስለታሪክ፣ ስለፍቅር፣ ስለአንድነት፣ ስለሰብዓዊነት ነው ሚጨነቁት። ይሄን የምለው የአብሮ አደግ ያህል ስለማውቃቸው ነው።

አስቼ ሙዚቃውን ለቅቆ ሰው በደስታ እብድ ሲልለት እሱ ግን ወዲያው ስልኩን አጥፍቶ ወደ ገዳም ይሄድና ንሰሃና ጸሎቱን ይጀምራል። ከእናትዋ ጎንደር በኋላ መድረክ ላይ እንዲዘፍን በመላው ዓለም ያልዘነበለት የሚሊዮን ብር ጋጋታ  አልነበረም። ወይ አምስት! አስቼ እንደ ዱሮው ወደ ገዳሙ፣ ወደ ሕሊና ሰላሙ፣ ቅድሚያ ለሰላም እንኑር ወደሚል ብሂሉ ... ከገዳም ሲመለስም ከዛችው ድሮ ከሚመገብባት ምግብት ቤት... ከዛው ድሮ ሻሂ እየጠጣ ከሚጫወታቸው ሰዎች ጋር... ነው።

ሶሚክ ለጥበብ የተፈጠረ ነው። አንድ ጥሩ ነገር ካየባችሁና ሥራ ወዳድ እንደሆናችሁ ካመነ ገንዘብ ባይኖራችሁም ሌላ ቦታ ሚሊዮን ብር የምትጠየቁትን ፕሮዳክሽን በነፃ ሠርቶ ያስረክባችኋል። በፈጠራችሁ አስደንቁት እንጂ ከናንተ የሚያገኘው ቅድመ ክፍያ ጉዳዩ አይደለም። በዛ ላይ እርጋታው፣ የተግባር ሰውነቱ፣ ብልጭልጭ አለመውደዱና እዩኝ እዩኝ አለማለቱ ... ብዙ ባህሪዎቹ ከሱ ጋር ስትሆኑ ምቾት ይሰጣችኋል።

ነገ ሁለታቸውም (ከአቀናባሪዎችና ገጣሚዎች ጋር) ለዓመታት የለፉበትን የአልበም ሥራን "አስቻለ"ን ለህዝብ ያቀርባሉ። ሁለቱም አዲስ እይታን፣ አዲስ ጣዕምን፣ ለማሳየትና እናንተን ለማስደሰት እንጂ ለሥምና ለዝና እንዲሁም ለጥቅም የሚያወጡት አልበም አይደለም። ከአልበሙ አንዳንዱ ሙዚቃ በጥልቅ ጥናት የተሠራና አጀብ የሚያሰኝ ነው። ቁጭ ብድግ የሚያደርጉ ድንቅ ዜማና ግጥሞች ከአስገራሚ የአዘፋፈን ስልት ጋር የተካተቱበት ነው። በዛ ላይ ድንቅ ህብራዊነትና ሁለንተናዊነትን የተላበሰ ራሱ ኢትዮጵያዊ የሆነ አልበም ነው!

አስቼ ሚሊዮን ብሮችን እየገፋ ቆይ የህሊና ሰላም ይቅደም እያለ እንዲህ የሚብሰለሰለው በእናንተ ልብ የሚቀር አንዳች ነገር ለማስቀረትና ለመጨመር በማሰብ ነው። ሁለቱም ጋ ሥግብግብነትና ራስወዳድነት የለም። እኔ የጥበብም ይሁን የኑሮ ገዳማውያን ብያቸዋለሁ። ሁሌም በዚህ ከፍታቸው እንዲፀኑ በጎውን ሁሉ እመኝላቸዋለሁ።

Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Waliya_Entertainemnt #Music
👍1
👤 Yema | የማ
🎵 Yedega Sew | የደጋ ሰው
━━━━━━━━━━━━━━
➠ RELEASED: 2024
➠ GENRE: #Ethiopian
➠ TYPE: #Album
➠ TRACKS: 12
➠ FORMATS: #Mp3
➠ CHANNEL: @Waliyaentmt
━━━━━━━━━━━━
Follow us on Social Medias
Youtube - https://www.youtube.com/@waliyaentmt
Facebook - https://www.facebook.com/Waliyaentmt
Tiktok - https://www.tiktok.com/@Waliyaentmt
Telegram - https://www.t.me/waliyaentmt

#Yema #Album #Ethio_albums #Waliya_Entertainemnt
1👏1